TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የፌዴራሉ መንግሥት የ2017 ጠቅላላ የወጪ በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። ለክልል መንግሥታት የበጀት ድጋፍ የተመደበው 236.7 ቢሊዮን  ብር ነው። አጠቃላይ የ2017 በጀት (971.2 ቢሊዮን) በ2016 በጀት ዓመት ከጸደቀው የወጪ በጀት አንጻር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው  ተገልጿል። ዛሬ ከሰዓት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ምክር…
#ብር #ዶላር

የፌዴራል መንግሥት #የ2017_በጀት ሲዘጋጅ ብርን ከዶላር አኳያ ያለውን የምንዛሬ ተመን #የሚያዳክም ውሳኔ ተግባራዊ ይደረጋል በሚል ታሳቢነት እንዳልሆነ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ለተወካዮች ም/ ቤት ተናግረዋል።

በኢ-መደበኛው እና በባንኮች በሚደረግ ይፋዊ ምንዛሬ (official exchange) መካከል ያለውን ልዩነት የሚያጠብ እርምጃን አስመልክቶ  " ምንም የቀረበ ነገር የለም "  ብለዋል።

አቶ አህመድ ፥ የፌዴራል መንግሥት በጀት የተዘጋጀው " የነበረው አካሄድ #እንደሚቀጥል ታሳቢ ተደርጎ " ሲሉ ገልጸዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ " ዘንድሮ የነበረውን ይፋዊ የውጭ ምንዛሬ መጠን (official exchnage rate) ታሳቢ አድርጎ ነው በጀቱ የቀረበው " ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህን ማብራሪያ የሰጡት በም/ቤቱ የኢዜማ ተወካይ ዶ/ር አብርሃም በርታ ፥  " ህጋዊውን እና ኢ-መደበኛውን የውጭ ምንዛሬ ገበያ እኩል ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች እንዳሉ ከአንዳንድ ወገኖች እየሰማን ነው ፤ ... የውጭ መንግስታት #በብድር_ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ ጫና በመፍጠር ይህንኑ ለማስፈጸም እንደሚንቀሳቀሱ የሚገልጹ መረጃዎችም አሉ ፤ እንዲህ አይነቱ እርምጃ የማንወጣው ችግር ውስጥ ይከተናል የሚል የባለሙያዎች ትንታኔ አለ " በማለት ላነሱት ሀሳብ ነው።

#EthiopianInsider #HoPR #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia