TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በራዝ ገዟ ሶማሊላንድ ይፋዊ መግለጫ ወጥቷል። በዚህም መግለጫ ስምምነቱ ታሪካዊ ነው ተብሏል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ኢትዮጵያ ለሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እውቅና በመስጠት በሊዝ የባህር በር / ለባህርኃይሎቿ የባህር መዳረሻ እንደምታገኝ መግለጫው ይገልጻል። " ስምምነቱ የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ ነው " ያለው መግለጫው ለኢትዮጵያ የባህር ኃይል ተጠቃሚነት 20 ኪሎሜትር የባህር በር እንደሚሰጥ…
#Ethiopia #Seaport

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከሶማሊለንድ ጋር ስለተፈረመው ስምምነት ምን አሉ ?

- ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቃሚ እንድትሆን በምክክር፣ በሰላማዊ መንገድ ብቻ በሰጥቶ መቀበል መርህ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።

- ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጋር ብዙ ሞክረን ያልተሳካው ከሶማሊላንድ ጋር በተመሳሳይ መንገድ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

- መንግሥት አቋሙን ይፋ ካደረገ በኃላ ያሉ ሃብቶችን ከመጋራት አንፃር የነበረው ጉዳይ ጥርቶ ከወጣ በኃላ ዝርዝር ውይይት ሲካሄድ ነው የቆየው።

- ጉዳዩ መልክ እስኪይዝ በተወሰነ በጠባብ ቡድን፣ በመሪዎች ደረጃ እና በተወሰኑ አካላት ደረጃ እንዲያዝ እየበሰለ ሲሄድ ደግሞ ሁለቱም አካላት የየራሳቸውን አመራር እያሳተፉ የሚሄዱበት ሁኔታ እንዲፈጠር ተደርጓል።

- የወደብ ስምምነት ተጠቃሚነት በሊዝ አማካኝነት የሚፈፀም ነው።

- ይህ የስምምነት ማዕቀፍ ሶማሌለንድ እና ኢትዮጵያ አንዳቸው ጋር ያለውን ሃብት ለመጋራት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እድል የሚያሰፋበት፣ በመከላከያና ደህንነት ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን አቅምና ልምድ ለሶማሊላንድ የምታጋራበት ፤ የጋራ ጥቅማቸውን ማስጠበቅ የሚችሉበት አቅም ይገነባል።

- የስምምነቱ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ ሶማሌላንድ ውስጥ Military base እና Commercial maritime ሰፈር እንዲኖራት ይፈቅዳል። ይህ #በሊዝ የሚታሰብ ይሆናል። ለ50 ዓመት እና ከዛ በላይ #በማራዘም የሚካሄድ እንዲሆን ያደርጋል።

- ኢትዮጵያ አማራጭ ወደብን እድል ለማግኘት በርበራ ኮሊደርን የምታሰፋበት ፣ የመከላከያ አቅሟን አዲስ በምትከራየው ቦታ የምታጠናክርበት እድል ይሰጣል።

- ኢትዮጵያ ለሊዝ ተጠቃሚነቷ ቴሌኮም ይሁን፣ አየር መንገድ ይሁን ጥቅም በሚያስገኙ መሰረተ ልማቶች ላይ ድርሻ ትሰጣለች። ምን ያህል ነው ? የሚለው የሚከፈለው ሊዝም ምን ያህል ይሆናል ? የሚለው በዝርዝር ውይይቶች ይወሠናል።

- በጤና፣ በትምህርት ፣ በመከላከያ የሚሰሩት ዝርዝር ስምምነቶች በተናጠል ውይይት ይካሄድባቸዋል። ወደ ፓርላማ ሄደው የሚፀድቁ በርካታ ስምምነቶች ከዚህ ይፈልቃሉ።

- የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ አጠቃላይ ማዕቀፍ ሁለቱ አካላት በጋራ ተባብረው የሚያድጉበትን ማዕቀፍ ነው የሚያስቀምጠው። ዋና ዋና አንጓዎች ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን ዕድል በተጨባጭ ወደመሬት ለማውረድ እድል ይሰጣል።

- ስምምነቱ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ሂደቱ ያልቃል / ወደ ተግባር / ስራ ይገባል።

- ከሌሎች ሀገራት ጋር የጀመርናቸው አሉ #ከኤርትራ ጋር በዝርዝር ውይይት ተጀምሮ የሆነ ቦታ ላይ ነው የቆመው።

- ኢትዮጵያ አንድ ወደብ ፣ ሁለት ወደብ ፣ ሶስት ወደብ ሳይሆን ፤ ኢትዮጵያ አሁን ባለው ሁኔታ እያደገች ከሄደች ሁሉም ቀጠናዎች የሁሉም ጫፎች የኢትዮጵያን ምርቶች የሚያስገቡበት በር ያስፈልጋል።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማብራሪያቸው በስምምነቱ ሶማሊያ ልዓላዊ ግዛቴ ናት ለምትለው ራስ ገዟ #ሶማሌላንድ በይፋ የነፃ ሀገርነት እውቅናን ትስጠ እንደሆነ የተናግሩት አንዳች ነገር የለም።

@tikvahethiopia