TIKVAH-ETHIOPIA
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ። 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ…
#TPLF
የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአሸባሪነት የሰየመውን ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሽብርተኝነት ስያሜ #ይነሳ #አይነሳ በሚለው ጉዳይ ላይ ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።
በምክር ቤቱ ውስጥ የብልፅና አባላት ሕወሓትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ያለመ ዝግ ስብሰባ ትናንት መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም. የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔን ጨምሮ፣ የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በተገኙበት ሲያካሂድ እንደዋለና በውይይቱም በርካታ መግባባት ያላስቻሉ ጠንካራ ሐሳቦች መሰንዘራቸውን ጋዜጣው ከምንጮቼ ሰምቻለሁ ብሏል።
ይሁን እንጂ በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን የ2014 በጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት ላይ ለመምከር ለመጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ለጠዋት ጠርቶት የነበረውን ስብሰባ ወደ ከሰዓት በማጠፍ፣ በዚሁ ቀን ጠዋት አስቸኳይ ስብሰባ ለፓርላማ አባለቱ መላኩ ተገልጿል፡፡
ፓርላማው ሕወሓትንና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ድርጅት ወይም በመንግሥት ‹" ሸኔ " ተብሎ የሚጠራውን ታጣቂ ቡድን በአሸባሪነት የፈረጀው በሚያዚያ በ2013 ዓ.ም. ነበር፡፡
#ሪፖርተር_ጋዜጣ
@tikvahethiopia