TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢህአፓ⬆️

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) አመራሮች ከ40 አመታት በላይ የውጪ አገር ቆይታ በኋላ #ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ በውጪ ያሉ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር ግንባታ ወደ አገር እንዲገቡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ይህን ጥሪ ተከትሎ ነው የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ከነበራቸው የብዙ አመት የውጪ ቆይታ በኋላ ዛሬ ወደ አገር ቤት የገቡት።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ በላይነህ ንጋቱ፣ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም፣ አቶ መሃመድ ጀሚል እና ኢንጂነር ሰለሞን ገብረስላሴን የያዘ ከፍተኛ አመራር አባላት ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ተቀብለዋቸዋል።

ሊቀመንበሩ አቶ በላይነህ ንጋቱ እንዳሉት፤ ፓርቲው በአገሪቱ አሁን የተጀመረውን ለውጥ መሰረት እንዲይዝ የሚችለውን ያደርጋል።

በተፈጠረው እድል ህጋዊ ሆኖ ለመንቀሳቀስ ፓርቲው ዝግጁ መሆኑን የገለፁት ሊቀመንበሩ ከአሁኑ የለውጥ አመራር ጎን በመሆን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠር #በትጋት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ሚናቸውን በአግባቡ ለመወጣትም ከቀድሞ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ከወጣቱ ጋር የጋራ ምክክር እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

የህግ የበላይነት እንዲከበርና ዴሞክራሲ የበለጠ እንዲሰፋ ፓርቲያቸው ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር #ተቀራርቦ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የፓርቲው አመራሮች ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥና ሻማ የማብራት ስርዓት ያከናውናሉ ተብሏል።

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia