TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከሜቴክ ሰራተኛ‼️

"ሰላም ፀግሺ ስሜ E ይባላለሁ። የምፅፍልህ ከደ/ዘይት ነው፡፡ የሜቴክ ሰራተኛ ነኝ ከደጀን አቭዬሺን ኢንዱስትሪ ነገር ግን ሰሞኑን ከተያዙት የሜቴክ ሃላፊዎች ጋር ሰራተኞችን እንደ #ሌባ ማየት ጥሩ አይደለም። በወረደ ደሞዝ ነው እየሰራን ያለነው ነገር ግን ሌላ መ/ቤት እንኳን እንዳንወዳደር የስራ ልምዳችንን እያዩ የሜቴክ ስለሆነ አይጠሩንም፡፡ እዚጋ መታወቅ ያለበት በጣም ትልቅ አቅምና የስራ ዲሲፒሊን እንዲሁም የፈጠራ አቅምና የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸው ምርጥ ሰራተኞች ነው ያሉት ስለዚህ አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ የሚለው አባባል እየደረሰብን ስለሆነ ማንም የበላይ አመራርና ሃላፊ በፈፀመው ሌብነት ታቺ ያለው የኔ ቢጤ ሰራተኛ 15 ቀን የማያቆይ ደሞዝ እየተከፈለው ስማችን አይጥፋ ወንጀለኛን ወንጀለኛ ስንል እየለየን ይሁን እባክህ ለሁሉም አድርስልኝ፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#በቆጂ

በቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጂ ከተማ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት 4 ሰዎች መገደላቸውን እና ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ እስረኞችን ማስመለጣቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ጋዜጣው ቃላቸውን ሰጡኝ ያላቸው የአይን እማኞች ፤ አርብ ዕለት ከምሽት 4 ሰዓት እስከ ለሊት 8 ሰዓት ከፍተኛ ተኩስም ከተማ ውሥጥ ይሰማ እንደነበር ገልጸው ፤ በማግስቱ ግን የፌዴራል ፖሊስ ወደ ከተማው መግባቱን ተከትሎ ተኩስ እንደቆመ አመልክተዋል።

የአይን እማኞቹ ተኩስ የከፈቱት መንግሥት " ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸው የታጠቁ ቡድኖች መሆናቸውን ገልጸው ፤ ለሊት በነበረው ተኩስ አንድ የአካባቢው የሚሊሻ አሰልጣኝን ጨምሮ ነዋሪዎች መገደላቸውን አሳውቀዋል።

አንድ የሚሊሻው አሰልጣኝ የቅርብ ጓደኛ ነኝ ያሉ የአይን እማኝ ፤ ታጣቂዎቹ " ይህንን ቤት ከምናፈነዳው አንተ ብትወጣ ይሻላል " በማለት በለሊት ከመኖሪያ ቤቱ አስወጥተው እንደገደሉት ጠቁሟል።

ታጣቂዎቹ በከተማው ተኩስ የከፈቱት በእስር ቤት ያሉ ታራሚዎችን ለማስፈተት መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎች የሚሊሻ አባሉንና ከነዋሪዎችን ሰው ከገደሉ በኃላ በከተማው ወደሚገኝ አንድ የፖሊስ ጣቢያ ሰብረው በመግባት ታሳሪዎችን ከእስር አስወጥተው መውሰዳቸውን ነዋሪዎች ለጋዜጣው ገልጸዋል።

ጋዜጣው ከከተማው ከንቲባ ምላሽ ለማግኘት የድምፅ እንዲሁም ፅሁፍ መልዕክት በመላክ ሙከራ ቢያደርግም ምላሽ ለማግኘት እንዳልቻለ አሳውቋል።

የበቆጂውን ጥቃት በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የበቆጂ ቤተሰብ አባላት ተመሳሳይ መልዕክቶች መላካቸውን ተመልክተናል።

ጆ የተባለ የቤተሰባችን አባል አርብ ከምሽቱ 5:30 ጀምሮ ከተማው ውስጥ ከባድ የተኩስ ድምፅ እንደነበር እና ተኩሱ ቢያንስ ከ1 ሰዓት በላይ እንደቆየ ጠቁሟል።

ሌላ ኤቢ የተባለ የቤተሰባችን አባል በበኩሉ ፤   በአርሲ ዞን በቆጂ ከተማ መንግስት " ሸኔ " ብሎ የሚጠራው አካል በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመክፈት 20 የሚደርሱ የህግ ታራሚዎችን አስለቅቋል ሲል ገልጿል።

የተኩስ ልውውጡ ከበድ ያለ እንደነበር የገለፀው ይኸው የቤተሰባችን አባል ከበቆጂ ከተማ ወጣ ባለ ስፍራ በከተከፈ ድንገተኛ ጥቃት ሁለት የኦሮሚያ ፖሊስ አባላት መገደላቸውን ጠቁሟል።

ከዚህ በተጨማሪ ስሜ ፥ የተባለ የበቆጂ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በቆጂ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ የታጠቀ ኃይል ፖሊስ ጣብያ ሰብሮ እስረኞችን ማስመለጡንና ወዳልታወቀ ቦታ እንደወሰዳቸውን ጠቁሟል። በጥቃቱ ወደ ሶስት ፖሊሶችን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችም መገደላቸውን አመልክቷል።

የበቆጂ ከተማን በተመለከተ ስለተከፈተው ጥቃት እና ስለደረሰው ጉዳት በመንግስት በኩል የተሰጠ መረጃ የለም።

ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ፣ እንዲሁም በወለንጪቲ ከተማ የታጠቁ ኃይሎች ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ተኩስ በመክፈት ሰዎችን መግደላቸውና እስረኞችን ከማስመለጥ ሙከራ ማድረጋቸው መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበቆጂ ጨምሮ በቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ ስለተፈፀሙት ጥቃቶች ከሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው  " የተባለውን ዓይነት የተደራጀ ጥቃት በየትኛውም አካባቢ አልተፈፀመም " ያሉ ሲሆን " አልፎ አልፎ #ሽፍታ ወይም #ሌባ ሊኖር ይችላል እንጂ ጥቃት የሚባል ነገር የለም። ሁሉም አካባቢ ሰላም ነው " ብለዋል።

Credit :  Reporter Newspaper , Tikvah Bokoji Family (Sem, Joh, Ab Via @tikvah_eth_BOT)

@tikvahethiopia
#ባቱ

በባቱ ከተማ ባለፈው እሁድ ለሊት ላይ ታጣቂዎች ፖሊስ ጣቢያ ላይ በከፈቱት ተኩስ 3 የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ለሬድዮ ጣቢያው ቃላቸውን የሰጡ አንድ ነዋሪ ፤ ታጣቂዎቹ በከፈቱት ተኩስ አንዲት ሴት እና 2 ወንድ የፀጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት፤ ስርዓተ ቀብራቸውም በከተማው መፈፀሙን ፤ ከታጣቂዎቹ በኩል አንድ የተመታባቸውን ሰው እየጎተቱ አርቀው እንደወሰዱ የሚያሳይ መረጃ መገኘቱን ገልጸዋል።

የታጣቂዎቹ ተኩስ መክፈት እስረኞችን ለማስለቀቅ መሆኑን እኚሁ የከተማይቱ ነዋሪ ተናግረዋል።

ባቱ በዕለቱ ከተፈፀመው ክስተት በኃላ በወትሮ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ነዋሪው ገልጸዋል። ነገር ግን ሁኔታው ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉን ለሬድዮ ጣቢያው አመልክተዋል።

በሌላ በኩል ፤ በባቱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በዕለቱ ረጅም ደቂቃ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበርና ተኩሱ ይሰማ የነበረው በማረሚያ ቤት አካባቢ እንደነበር አመልክተዋል።

በከተማው አስተዳደር በኩል የተባለ ነገር የለም።

ከዚህ ቀደምም በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ፣ በቆጂ ከተሞች የታጠቁ ኃይሎች ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ተኩስ በመክፈት ሰዎችን መግደላቸውና እስረኞችን ለማስመለጥ ሙከራ ማድረጋቸው መነገሩ አይዘነጋም።

የኦሮሚያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኮሎኔል አበበ ገረሱ በበቆጂ ጨምሮ በቢሾፍቱ፣ ወለንጪቲ ስለተፈፀሙት ጥቃቶች ከዚህ ቀደም ከሪፖርተር ጋዜጣ ተጠይቀው ፤ የተደራጀ ጥቃት በየትኛውም አካባቢ እንዳልተፈፀመ " አልፎ አልፎ #ሽፍታ ወይም #ሌባ ሊኖር ይችላል እንጂ ጥቃት የሚባል ነገር የለም። ሁሉም አካባቢ ሰላም ነው " ማለታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia