TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ⬆️

"ዛሬ ከሰአት 202 ኪ.ሜ ርዝመት የሚሸፍነውን እና 4 ተሽከርካሪዎች በትይዩ ለማስተናገድ የሚያስችል 32 ሜትር ስፋት ያለውን የሞጆ - ሃዋሳ የፍጥነት መንገድ የግንባታ ሂደት ያለበትን ደረጃ መመልከት ችያለው መንገዱ ካለዉ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ አኳያ በተያዘለት የግዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ #መጠናቀቅ እንደሚገባዉ የስራ #መመሪያ ሰጥተናል። በጉብኝቱ ከመንገዱ ባሻገር ኢትዮጲያውያን ሙያተኞች ከውጭ ሙያተኞች የሚቀስሙት ልምድ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር በላቀ ደረጃ አጠናክረው መሄድ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰብኩት።

በተመሳሳይ ማምሻውን የኢትዮጲያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ የአዲስ-አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የሚገኙት ቱሉዲምቱ እና የሞጆ የክፍያ ጣቢያ ላይ ያለውን የቁጥጥር እና የክፍያ ሲስተም ተመልክተናል። ዘመናዊ በሆነ ቴክኖሎጂ እና ብቃት ያለው የሰው ሃብት በመጠቀም ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት ተልኮውን ላደረገው ኢንተርፕራይዝ በቀጣይም ከዚህም በተሻለ ሁኔታ አገልግሎት እንዲሰጥ ሚንስትር መስሪያ ቤታችን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል።"

@tsegabwolde @tikahethiopia
#update ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መጋቢት 1 ቀን፣ ከሰዓት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 በወደቀበት ቦታ ተገኝተዋል። ለሟቾቹ ከልብ የመነጨ ኀዘናቸውን፤ ለሞቱት ወዳጅ ዘመዶች ደግሞ መጽናናትን ተመኝተዋል። የአደጋው መንሥኤ እንዲጣራ፣ ለሟች ወገኖችም ተገቢው ሁሉ እንዲደረግ #መመሪያ አስተላልፈዋል።

Via የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተደራጅታችሁ በሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ ብንባልም እስካሁን #መመሪያ ስላልተዘጋጀ ስራ ፈትተናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናገሩ፡፡ አስተዳደሩም መመሪያው #በቅርቡ ይወጣል ብሏል፡፡

Via #ሸገርFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኤችአይቪ / HIV #የሚያድን አዲስ መድሃኒት ተገኝቷል ?

አጭር ምላሽ ፦
#አልተገኘም

ሰሞነኛው የPrEP ጥናት ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ያወጡትን ዘገባ ሰዎች በተለይም በርካታ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በተሳሳተተ መንገድ ሲረዱትም ተስተውሏል።

አንዳንዶች በሞያው ውስጥ የሌሉና በቂ ግንዛቤ የሌላቸው " ኤችአይቪ / HIV አዲስ መድሃኒት እንደተገኘለት " አድርገው ሲያጋሩም ነበር።

እውነታው ግን HIVን #የሚያድን መድሃኒት ተገኘ አልተባለም።

ከሰሞኑን በእንግሊዝ ሀገር የተደረገው ጥናት ለHIV #ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ከመያዛቸው በፊት የሚወስዱት መድሃኒት ላይ ትኩረት ያሰረገ ነው። ይህ አሰራር አዲስ ሳይሆን ቀድሞም የነበረ ነው።

የጤና ባለሞያዎች ምን አሉ ?

(ዘሪሁን ግርማ,MPH)

ማህበርሰቡ ማዋቅ ያለበት ነገር ቢኖር PrEP በHIV ከታያዝን በኃላ እንደማያገለግል ነው።

የPrEP መድሃኒት በHIV ሳንያዝ ቀድሞ የሚሰጥ የራሱ #መመሪያ ያለዉ ሲሆን የምሰጠዉም ለምሳሌ በHIV ለመያዝ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ ሠዎች እንደ ግብረስጋ ግንኙነትን በማድረግ ገቢ የሚያገኙ ሠዎች ፣ ለአስገድዶ መደፈር ለተጋለጡና የመሳሰሉት ናቸው።

PrEP ምንድን ነው ?

PREP፣ ወይም ቅድመ-መጋለጥ ፕሮፊላክሲስ፣ በቫይረሱ ​​​​የመያዝ ከፍተኛ ተጋላጭነት ባላቸው ግለሰቦች ላይ የHIV ኢንፌክሽን አደጋን ለመቀነስ የሚያገለግል ነው።

በHIV #መከላከል ስትራቴጂዎች ውስጥ ጠቃሚ መንገድ ነው

PrEP እንዴት ይሰራል ?

PrEP የሚሰራው የHIV ቫይረስ በሰውነት ውስጥ ዘላቂ የሆነ ኢንፌክሽን እንዳይፈጥር በመከላከል ነው።

መድሃኒቱ ቫይረሱ ወደ ጤናማ ሴሎች እንዳይገባ እና እንዳይበከል የሚያግድ እንቅፋት ይፈጥራል።

ቫይረሱ እንዲባዛ እና እንዲሰራጭ አስፈላጊ የሆነውን reverse transcriptase የሚባል ኢንዛይም እንዳይሰራ ይከለክላል። ይህንን ኢንዛይም በመዝጋት፣ PrEP ቫይረሱ በሰውነት ውስጥ እራሱን እንዳይፈጥር እና የHIV ኢንፌክሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ይረዳል።

ወቅታዊ ጥናቶች በPrEP ዙሪያ ምን ይላሉ ?

በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች የPrEPን ውጤታማነት በገሃዱ ዓለም ውጤቶች አሳይተዋል።

በእንግሊዝ በ24,000 ተጠቃሚዎች ላይ የተደረገ ጥናት PrEP በኤችአይቪ የመያዝ እድልን በ86% ቀንሷል።

እነዚህ ውጤቶች በተከታታይ እና በትክክል ጥቅም ላይ ሲውሉ የPrEPን የHIV ስርጭትን ለመከላከል ያለውን ውጤታማነት ያሳያሉ።

ጥናቱ ስለ PrEP የገሃዱ ዓለም ውጤታማነት ማረጋገጫ ይሰጣል እና ይህን የመከላከያ መድሃኒት በቀላሉ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝባል።

*             *                 *                  *              *

" የኤችአይቪ (HIV) መድሀኒት ተገኘ የሚል አውድ ያለው አዘጋገብ አሳሳች ነው " - ዶ/ር  አሳልፍ

ዶ/ር አሳልፍ ፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ " የኤችአይቪ (HIV) መድሀኒት ተገኘ " የሚል አውድ ያለው አዘጋገብ #አሳሳች ነው ብለዋል።

ፒአርኢፒ " Pre-exposure prophylaxis" ማለት ለኤችአይቪ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች (commercial sex workers, health professionals ... etc) ከመጋለጣቸው በፊት / ለቫይረሱ በተጋለጡ በጥቂት ሰዓታት/ቀናት ውስጥ የሚወስዱት እስካሁንም በተለያዩ አማራጭ መድሃኒቶች ይተገበር የነበረ መከላከያ መንገድ እንጂ ኤችአይቪን የሚያክም (curative ህክምና) አይደለም ሲሉ አስገንዝበዋል።

" ጥናቱም እንደዛ አይልም " ብለዋል።

@tikvahethiopia