ጦርነት ውስጥ መግባት አንፈልግም!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እንዳሉት ኢራን በሳምንቱ መጨረሻ በሳዑዲ አረቢያ የድፍደፍ ዘይት ማጣሪያ ላይ ለተሰነዘረው ጥቃት ተጠያቂ ብትሆንም ጦርነቱ ውስጥ መግባት እንደማይፈልጉ ገልጸዋል፡፡ ለዶናልድ ትራምፕ ጥቃቱ በኢራን ተፈፅሟል የሚል እምነትና አመላካች ሁኔታዎች እንዳሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡ የጥቃጡን ፈጻሚ በእርግጠኝነት ለማወቅ እንዲቻል ዋሽንግተን የተሸለ ማረጋገጫ እንደምትሻ ተናግረዋል፡፡ ትላንት የሳውዲ አረብያ ቃል አቀባይ እንደገለፀው የመጀመርያው ግኝት እንደሚያሳየው በሳምንቱ መጨረሻ በደረሰው ጥቃት ላይ የኢራን ጦር መሳሪያ አገልሎት ላይ መዋሉን ያሳያል፡፡ ኢራን በበኩሏ ይሄ ማረጋገጫ የሌለው ውንጀላ በሷላይ እርምጃ ለመውስድ መታሰቡን አመላካች መሆኑን ትናግራለች፡፡
ምንጭ፦ አልጀዚራ/ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ፣ ሀረር፣ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ አሁንም እንደተዘጋ ይገኛል። #ETHIOPIA
ፎቶ📸ይሄ ደግሞ ሀዋሳ መግቢያ #ቶጋ አካባቢ የደረሰ የመኪና አደጋ ነው። በአደጋ ስለደረሰው ጉዳት ወደበኃላ መረጃዎችን ሰብስበን እናሳውቃለን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግጭቱ የተፈጠረው፦ በአይሱዙ ቅጥቅጥ እና ዶልፊን እየተባለ በሚጠራ መኪና መካከል ነው። ዶልፊኑ ከሀዋሳ ሻሸመኔ የሚሄድ ነበር፤ አይሱዙ ቅጥቅጡ ደግሞ ከቡታጅራ ወደ ሀዋሳ እየሄደ የነበረ ነው።
•በአደጋው የሰዎች ህይወት እንዳለፈ ሰምተናል። ተጨማሪ መረጃዎችን የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን ለማቅረብ እንሞክራለን።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
•በአደጋው የሰዎች ህይወት እንዳለፈ ሰምተናል። ተጨማሪ መረጃዎችን የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን ለማቅረብ እንሞክራለን።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መንገዱ ተዘግቷል! ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር እሚወሰደው መንገድ #ቆቦ ላይ ተዘግቷል። መኪና እንዳያልፍ ተከልክሎ ወደ ኋላ እስከ 7 ኪሜ ድረስ መንገድ በመኪና ሰልፍ ተዘግቷል። ከአካባቢው የቤተሰባችን አባላት እንደሰማነው ለአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት እየጨፈሩ እየተጓዙ በነበሩ ሰዎች ላይ አንድ መኪና እላያቸው ላይ ወጥቶ የሰዎች ህይወት አልፏል/የሟቾችን ቁጥር ቆየት ብለን እነግራችኃለን/ የመኪናው ሹፌር…
10 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል!
በምስራቅ ሀርጌ ዞን ጎሮ ጉቱ ወረዳ መዲሳ ጃለላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ትላንት ምሽት በሰርገኞች ላይ በደረሰ የተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አምስቱ ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፉ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት አደጋው የደረሰው ከጅጅጋ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሙሽሮችን አጅበው ሲሔዱ በነበሩ ሰርገኞች ላይ በመውጣቱ ነው።
የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3. 66092 ኦ.ሮ የሆነው ይህ መለስተኛ አውቶብስ ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ በስፍራው ሲደርስ ባስከተለው አደጋ ሙሽሮችን አጅበው በእግር ሲጓዙ የነበሩ ሰርገኞች ላይ የህይወትና የአካል ጉዳት አድርሷል።
በአደጋው የቆሰሉ ተጎጂዎች በድሬዳዋ ድልጮራ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት ኃላፊው ከሌሊቱ አደጋ በኋላ የደረሱበት ያልታወቀ ሰርገኞችን ለማግኘት ከህብረተሰቡ ጋር ፍለጋ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ ለጊዜው ቢሰወርም እሱን ይዞ ለህግ ለማቅረብና የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ክትትል መጀመሩን ኮማንደር ስዩም ተናግረዋል።
Via #ENA

ካፒታል ጋዜጣ ከህዝቡ በሰበሰበው ድምፅ መሰረት የአመቱ ምርጥ የመዝናኛ መዳረሻ ሆነን በመመረጣችን ደስታ ይሰማናል!
የፊልም የጊዜ ሰሌዳችንንና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት÷ የሚከተለውን አድራሻ በመጫን ቻነላችንን ይቀላቀሉ
👇
@Century_Cinema
አድራሻ: ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው ዋና መንገድ: የመጀመሪያው የመኪና ማዞሪያ

ጥንቃቄ አድርጉ!
በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከመደበኛዉ በላይ የሆነ ዝናብ የሚጥል በመሆኑ በጎርፍ ተጠቂ አካባቢዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለኢቲቪ እንደገለጹት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች ከመደበኛው በላይ የሆነ ዝናብ እንደሚጥል ከብሄራዊ ሜትሮሎጂ ትንበያ መረጃ ደርሶናል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ከሚዘንበው ተከታታይና ከፍተኛ ዝናብ ጋር ተያይዞ የቆቃ ግድብ ውሃ መጠን ከሚጠበቀው ከፍታ በላይ በመሆኑ ከግድቡ ውሃ የመልቀቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አቶ አበበ ተናግረዋል፡፡ በዚህም በግድቡ አካባቢና ከግድቡ በታች ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሶደሬ፤ በኑራኤራና መተሃራ፤ በአፋር ክልል አሚባራ፤ መልከ ሰዲ እንዲሁም በአዋሽ ተፋሰስ አካባቢዎች በሚገኙ ቦታዎች ላይ በመደበኛነት ከሚዘንበዉ ዝናብ በተጨማሪ ከግድቡ የሚለቀቀዉ ዉሃ ተደምሮ የጎርፍ ክስተት ሊያጋጥም ስለሚችል ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተብሏል፡፡
Via #EBC

#ሰኔ15
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰኔ 15ቱ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ በተጠረጠሩ ግለሰቦች የምርመራ ቡድን ያቀረበውን ይግባኝ ለመወሰን ለመስከረም 21/2012 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጠ። በባህር ዳር ከተማ በተፈፀመው የባለስልጣናት #የግድያ ወንጀል መረጃ የማሰባሰብና የማጣራት ስራው ባለመጠናቀቁ ክስ መመስረት በሚያስችል ደረጃ ላይ አልደረስኩም ሲል መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤቱ አስታውቋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/eth-09-17

#update በሰኔጋል የቱሪስት ጀልባ ተገልብጦ አራት ሰዎች ሞቱ። አደጋው የደረሰው በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር የባህር ዳርቻ ሲሆን ጀልባዋ በማእበል ሰኞ ምሽት በመገልበጥዋ መሆኑን የሃገሪቱ የድንገተኛ አደጋዎች አገልግሎት ለቢቢሲ አስታውቋል፡፡ ቱሪስቶቹ መጥፎ የአየር ፀባይ እንዳለ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ቸል ብለው ወደ ማድሊን ደሴት ማምራታቸው ለአደጋው መንስኤ ነው ተብሏል፡፡ በአደጋው ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ 35 ሰዎች መካከል ስድስት ፈረንሳያውያን፣ሁለት ጀርመናውያን፣ሁለት ሰዊድናውያንና አንድ ከጊኒ ቢሳው እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡ ህይወታቸው ያለፈው የአራቱ ሰዎች ዜግነት እስካሁን አለመረጋገጡን ነው ቢቢሲ የዘገበው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያን ይቅርታ ጠየቀች!
ደቡብ አፍሪካ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ ናይጄሪያን ይቅርታ መጠየቋ ተነግሯል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያንን ጨምሮ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ህይወት ጠፍቷል፤ በርካታ ንብረትም ተዘርፏል፡፡
በዚህ ሳቢያ ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸው ሻክሮ ከቆየ በኋላ አሁን ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያን ይቅርታ ጠይቃለች፡፡ አንድ የደቡብ አፍሪካ ልዮ መልዕክተኛ የፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳን የይቅርታ ደብዳቤ ለናይጄሪያው መሪ ሙሐመዱ ቡሐሪ አድርሰዋል፡፡
ደቡብ አፍሪካ ናይጄሪያውያንን ጨምሮ በውጭ አገራት ዜጎች ላይ ጥቃቱን በሰነዘሩ ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዷን ልዮ መልዕክተኛው ተናግረዋል፡፡ በአገሪቱ በተከሰተው ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ተፈናቅለዋል፤ ንብረታቸውም ተዘርፏል ነው የተባለው፡፡ ሁለቱ አገራት በተፈጠረው ችግር የሻገረ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል እየሰሩ ቢሆንም ናይጄሪያ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ እያስወጣች ትገኛለች ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ

የቁጥጥር መላላትና መቀዛቀዝ ይታያል!
"ሲ ነኝ ከአዳማ የTikvah ቤተሰብ፤ በአዳማ ከተማ ውስጥ ብዙ የንግድ ድርጅቶች የVAT ደረሰኝ አይሰጡም። በተለይም ዳቦ ቤቶች ፊት እያዩ አልፎ አልፎ ከመስጠት ሌላ አብዛኛውን ጊዜ ደረሰኝ አይሰጡምና እባክህ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስና ከህዝብ የሚሰበሰብ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን አድርስልኝ። የቁጥጥር መላላትና መቀዛቀዝ ይታያልና።"

#update ኢትዮጵያና ግብጽ በካይሮው የሦስትዮሽ ውይይት ሳይስማሙ እንደተለያዩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ቀጣዩን ስብሰባም ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 3 ከገለልተኞቹ የባለሙያዎች ቡድን ጋር በካርቱም ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ግድቡ በ3 ዐመታት ውሃ ሙሌቱ ይጠናቀቅ የሚለውን የኢትዮጵያ ሃሳብ ግብጽ አልተቀበለችም፡፡ ኢትዮጵያም የግብጽን ሃሳብ ኢፍትሃዊ በማለት በሰነዱ ላይ ሳትወያይበት ቀርታለች፡፡ ግብጽ ትናንት ባወጣችው መግለጫ ኢትዮጵያ በካርቱሙ ስብሰባ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እንድትወያይ ጠይቋል፡፡
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሁመራ መቅረጫ ጣቢያ የተቆጣጠራቸው ከአንድ ሚለዮን 500ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን ዛሬ እንዲወገዱ አደረገ። ጣቢያው እንዲወገዱ ያደረጋቸው እቃዎቹ በተለያዩ ጊዜያት በህገ ወጥ መንገድ ከሀገር ሲወጡና ሲገቡ የተገኙ ናቸው። እቃዎቹ አንድ ሚሊዮን 542 ሺህ ብር ግምት እንዳላቸው የጣቢያው አስተባባሪ ተወካይ አቶ ጌታቸው በሪሁ ገልጸዋል። ከተወገዱት ውስጥ የሺሻ ማጨሻዎች፣ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና የጥራት ደረጃቸው ያልጠበቁ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ይገኙበታል።
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስቴሩ የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኙ!
የጤና ሚኒስቴሩ ዶክተር አሚር አማን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ዛሬ ጎበኙ። ሆስፒታሉ የማህበረሰቡን የአገልግሎት ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ እየተሰራባቸው ከሚገኙት 22 ሆስፒታሎች መካከል አንዱ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በያዝነው ዓመት ስራው ተጠናቆ የሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማስተማሪያነት ያገለግላል ያሉት ሚኒስትሩ የተማሪዎች ማደሪያ፣ ቤተ-መጽሀፍት፣ መማሪያ ክፍሎች እንዲሁም የመሰረተ - ልማት ዝርጋታ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አስራት አሰፋ የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው አስተዳዳር ቦርድ አባል በጤናው ዘርፍ በዞኑ ከሚስተዋሉ አበይት ተግዳሮቶች መካከል ዋንኛው መሆኑን ገልጸው የሆስፒታሉ ለማስተማሪያነት ጭምር መዋሉ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በየደረጃውም የሚገኙ የዘርፉ ሀላፊዎች እና የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው ሚኒስትሩ ትኩረት ሰጥተው ያካሄዱትን ጉብኝት አድንቀዋል፣ ጉብኝቱ በርትተን እንድንሠራ ይረዳናልም ብለዋል፡፡
እንደ መንግስት በ22 ሆስፒታሎች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በአጭር እና በረጅም ጊዜ ዕቅድ የሚፈጸሙትን ተግባራት በዝርዝር በማስቀመጥ እየተሰራ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባገኘነው መረጃ የሆስፒታሉ የማስፋፊያ ግንባታ ስራዎች፣ የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ፣ ሌሎች ግብዓት እንዲሟሉ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
Via #EPA

ከንቲባው እንዴት ተገደሉ?
አቶ አበበ ዕሁድ ምሽት ላይ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጪ በታጣቂዎች መገደላቸውን የጉሊሶ ወረዳ የአስተዳደር እና ጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋ ሊካሳ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። "ደጃፋቸው ላይ በሁለት ጥይት ግንባራቸውን ተመትተው ነው የተገደሉት" ሲሉ የጸጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊው ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹ ከንቲባውን ደጃፋቸው ላይ ከገደሉ በኋላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ዘልቀው በመግባት "ለስብሰባ የተዘጋጀ ጽሑፍ እና የአካባቢውን ባለስልጣናት ስም ዝርዝርን የያዘ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር ይዘው ሄዱ'' ሲሉ አቶ ተስፋ ጨምረው ተናግረዋል።
ከንቲባውን ገድለው ላፕቶፕ ዘርፈው ሄዱ የተባሉት ታጣቂዎች በቁጥር ወደ ስድስት እንደሚጠጉ የሟች የቤተሰብ አባላት ለመንግሥት የጸጥታ አካል መናገራቸውም ተገልጿል። ግድያው እንዴት ተፈጸመ? ጥቃቱ በተፈጸመበት ምሽት የሁለት ልጆች አባት የነበሩት ከንቲባ አበበ ተካልኝ እሁድ ምሽት ላይ ከልጆቻቸው ጋር ቴሌቪዥን እየተመለከቱ ላፕቶፓቸው ላይ እየጻፉ ነበር።
አራት ሰዓት ገደማ ላይ ከንቲባውን የሚፈልግ ሰው ከውጪ እንደተጣራና 10 ዓመት የማይሞለው ልጃቸው ወደ ውጪ ሊወጣ ሲል አባት ልጅን ከልክለው እንደወጡ ደጃፋቸው ላይ በሁለት ጥይት ግንባራቸውን ተመትተው መገደላቸውን የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተስፋ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ከዚህ ቀደምም በምዕራብ ኦሮሚያ በነዋሪች ላይ ከሚፈጸሙ ጥቃቶች በተጨማሪ፤ የአካባቢው ባለስልጣናት የታጣቂዎች ኢላማ ሆነው ቆይተዋል። ከጥቂት ወራት የቄለም ወለጋ ዞን የደህንንት እና የኦዲፒ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ግለሰብ ተገድለዋል።
#BBC
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-17-2

ዶ/ር አለማየሁ⬆️
ስመ ጥሩው ሐኪም ዶ/ር አለማየሁ ተገኝ የ2011 ዓ.ም የአቢሲኒያ ሽልማት ድረጅት በሙያቸው ያደረጉትን አስተዋጽዎ በመንገዘብ የሎሬት ማእረግ ሠጥቷቸዋል፡፡ ተገልጋዮቻችንና የስራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ! ለዶር ዓለማየሁም እንኳን ደስ ያልዎ ለማለት እንወዳለን፡፡ ዶክተሩ UROLOGIST - የኩላሊት፣ የፊኛና፣ የሽንት ቱቦ ስፔሻሊስት ናቸው።

ቤተሶቦቻችን ተጋብዛችኃል⬆️
ኢያሱ ሲሳይ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 10 2012 ዓ/ም በፈንደቃ የባህል ማዕከል የስዕል አውደርዕይ አዘገጅቶ በአክብሮት ጠርቷችኃል።
ከ20 በላይ ውብ እን ማራኪ ስራዎች!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢያሱ ሲሳይ በመጪው ቅዳሜ መስከረም 10 2012 ዓ/ም በፈንደቃ የባህል ማዕከል የስዕል አውደርዕይ አዘገጅቶ በአክብሮት ጠርቷችኃል።
ከ20 በላይ ውብ እን ማራኪ ስራዎች!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ ከተማ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች በመማር ላይ ለነበራችሁ ተማሪዎች በሙሉ በያላችሁበት፤
የጅማ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ ከተማ ባልተፈቀደ የትብብር ኘሮግራም በመማር ላይ ለነበራችሁ ተማሪዎች መንገላታት እንዳይደርስባቸሁ ወደ ሌላ ተቋም አዛውሮ ለማስጨረስ እንዲቻል፡-
1ኛ. በተቋሙ ስትመዘገቡ የተሰጣችሁ የተማሪ መታወቂያ፣
2ኛ. የተማራችሁበትን ትምህርት የመጨረሻውን ሲሚስተር ውጤት ሪፖርት፤
3ኛ. በመማር ላይ እያላችሁ #የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በአጠቃላይ እነዚህ 3 መረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከዛሬ ማክሰኞ መስከረም 6 ቀን ጀምሮ እስከ አርብ መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ቢሮ እንድታቀርቡ እያሳሰብን በቀጣይ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉበትን አግባብ በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻችን፡- አዲስ አበባ፤ ሽሮሜዳ አሜሪካን ኢምባሲ ፊት ለፊት

#share #ሼር --- የጅማ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ ከተማ በሚሰጣቸው ፕሮግራሞች ለምትማሩ ተማሪዎች በሙሉ በያላችሁበት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia