TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሜ/ጄነራል ገዛኢ አበራ ልጅ...

"አባቴ በግፍ ከተገደለ ዛሬ 80 ቀኑ ነው፤ ከአባቴ አሟሟት ጋር በተያያዘ ያለው እንቆቅልሽ ምንድነው ተብዬ ብጠየቅ የማውቀው ነገር የለም፣ ትክክለኛ ገዳዩ ማን እንደሆነም እስካሁን ግልፅ አይደለም። ያ ገደለ የተባለው ጠባቂም ቢሆን የት እንዳለ አናውቅም፣ ክስ ተመስርቶበታል አልተመሰረተበትም፣ የት ፍርድቤት ነው የሚቀርበው ምንም መረጃ የለም"

Via ዳዊት ከበደ/Awramba Times/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሰባት የሃይማኖት ተቋማትን ያካታተዉ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ዛሬ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመገኘት ህሙማንን የማጽናናት እና የመባረክ ተግባርን አካናዉኗል፡፡ የጨቅላ ህጻናት ጽኑ ህሙማን ክፍል፣ የህጻናት የልብ ህክምና ክፍል እና የወላድ እናቶች ክትትል ክፍሎች በየተቋማቱ በሃይማኖት አባቶች ተጎብኝተዋል፡፡ በበጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶች ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በሆስፒታሉ እድሳት የተደረገላቸዉ ክፍሎችም የጉብኝቱ አንድ አካል ነበር፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢምግሬሽን፣ ዜግትና ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዜጎች ለፓስፖርት 45 ቀናት መጠበቅ እንዳለባቸው መግለጹን ካፒታል ጋዜጣ ዛሬ አስነብቧል፡፡ ኤጀንሲው ለፓስፖርት ሕትመት የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት አለብኝ ሲል ገልጻል፡፡ አመልካቾች የተፋጠነ ፓስፖርት ለማግኘት ከመንግሥት ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ፣ የጤንነት ሁኔታ ማረጋገጫ፣ የቪዛ ፍቃድ፣ የአስመጭና ላኪነት ማረጋገጫ የመሳሰሉ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው ብሏል፡፡ ለተፋጠነ አገልግሎት 2 ሺህ 182 ብር ሲጠየቅ፣ ለመደበኛው ደሞ 600 ብር ነው፡፡

Via #CPAITAL/wazema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓት!

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪትን በተመለከተ አዲስ መመሪያ በነሃሴ ወር መጠናቀቂያ ላይ ነበር ያፀደቀው። አዲሱ መመሪያ ከፈቀዳቸው አሰራሮች መካከል በኮድ 1 ታክሲ መመዝገብ የሚቻሉ ባለ ቢጫ ወይም ባለሰማያዊ ቀለም ታክሲዎች ሊሆኑ እንደሚችሉና ቴክኖሎጂ አግዟቸው በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችሉ ታክሲዎች ሆነዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው የኢኮኖሚክ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ለሸገር ራድዮ በሰጡት ማብራሪያ ከዚህ ወዲያ ለሚተገበረው መመሪያ ይህን ብለዋል፦

"የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓት የሚባል መመሪያ ወጥታል። የወጣው መመሪያ ከዚህ በፊት መጠቀም ሚችሉም ናይችሉም የሚለያይ ነበረ አሁን ግን ማንም ሰው መጠቀም የሚችልበት ከዚህ በፊት አግደን የነበረው አገልግሎት ክፍት ያደረግንበት መመሪያ ነው። ከዚህ በፊት ተከልክለው የነበሩ አገልግሎቶች ክፍት ያደረገ አዲስ መመሪያ ነው። ...ከዚህ በፊት ኮድ 1 ታክሲ መስጠት ተከልክሎ ነበር ስለዚህ ይህ መመሪያ ኮድ ኣንድ ታክሲ ማውጣት እንዲቻል ፈቅዶ የወጣ መመሪያ ነው። ማንም ሰው ሄዶ ኮድ 1 ታክሲ አውጥቶ...ሰማያዊና ነጭ ቀለም ሊሆን ይችላል ቀብቶ መንቀሳቀስ እንዲችል የፈቀድንበት ነው። ስንፈቅድ ግን ወደ ኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት ሲስተም ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው። ወደዛ ከገቡ ገብተው ለመስራት ፍቃደኛ ከሆኑ በስልክ ጥሪ፣ ማስተናገድ ፍቃደኛ ከሆኑ ይሄ ተከልክሎ የነበረውን የሚፈቅድ መመሪያ ነው።"

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-4
"ማንም ሰው ወደታክሲ #መግባት ይችላል የሚችለው ግን ኮድ 1 ሆኖ ነው። ኮድ 1 ተፈቅዷል ለማንም ሰው ዝግ አይደለም። ግን ይሄንን የሚያደርገው የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ስምሪቱን በሚቆጣጠሩ ድርጅቶች ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ ከሆነ ብቻ ይሆናል። ሰው ደግሞ ያንን መግባት ስላቃተው ነው ተደብቆ በኮድ 2 እና 3 የሚሰራው ኮድ 1 ጠይቆ ስለተከለከለ ነው። አሁን ግን ክፍት ሆኗል። . . . እየፈራ፣ እየተደበቀ የሚመጣው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በነፃነት ደስ ብሎት መስራት የሚችልበትን ነው።" በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው የኢኮኖሚክ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ስለአዲሱ መመሪያ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ሰዎች አንዳንዴ የሚጠየቁት ፐርሰንቴጅ በጣም ብዙ ነው። ምንም ነገር በመኪናቸው፣ በነዳጃቸው፣ በመለዋወጫ እቃቸው፣ እራሳቸው ሰርተው 17% ይሰጣሉ በጣም fair አይደለም። አማራጭ ስለሌላቸው ነው ይሄን የሚያደርጉት እኛ ደግሞ ፈቀድንላቸው ታክሲ ካደረግናቸው ነፃነት አላቸው መርጠው ማድረግ ይችላሉ ስለዚህ በተሻለ ዋጋ መደራደር ይችላሉ፤ መርጠው የወደዱት ጋር መስራት ይችላሉ። ለነሱም ደግሞ የተሻለ መስራት የሚችሉበት ነው። ይሄ መሆኑ ደግሞ ብዙ ሰው ፈርቶ ቁጭ ያለው ወደዚህ እንዲመጣ ማድረግ ይችላል ማለት ነው። ...መንግስትም በአግባቡ ሚቆጣጠረው ዘርፍ መሆን ይችላል። ...በኮድ 2 እና በኮድ 3 ህግ የለም፤ ታክሲ መስራት ህግ የለም የፌደራል አዋጁ ይከለክላል።" ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"እኛ ለእኛ"

በትምህርት ሚኒስቴር ስር በክረምቱ ወራት ሲሰራ የነበረው ሀገራዊ የበጎ ፍቃድ ሥራ ተገባዶ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችና አልባሳትን አካቶ ለጉዞ ዝግጁ ሆኗል፡፡ ይህ ሰብዓዊ ድጋፍ ዛሬ ላይ ከአዲስ አበባ ወደ፡-

1, ሶማሌ ክልል -ጅግጅጋ
2, ቤንሻንጉል ጉሙዝ- አሶሳ
3, ደቡብ ክልል- ሀዋሳ
ተጭኗል፡፡ በየአከባቢው በሚደርስበት ሰዓት ደግሞ ከፍተኛ የሰው ኃይል ያስፈልጋል ስለሆነም ጅግጅጋ ፣ አሶሳና ሀዋሳ ያላችሁ በጎ መስራት የምትፈልጉ ሰዎች ደውሉልን፡፡

1. በሀዋሳ ያላችሁ 👉 +251911485705 ደውላችሁ ተመዝገቡ፡፡
2. ጅግጅጋና አሶሳ ያላችሁ 👉+251944260072 ደውላችሁ ተመዝገቡ፡፡
ለበለጠ መረጃ @emush21 ላይ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የሁሉም መኪኖች የጉዞ መዳረሻ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ነው፡፡
ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው ተገደሉ !

ከትናንት በስቲያ (ቅዳሜ) ከምሽቱ 1 ሰዓት ገደማ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ከተማ ሁለት ሰዎች በጥይት ተመትተው መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ ይህን መሰሉ ግድያ ነዋሪ የዕለት ተዕለት ሰቆቃ ከሆነ ሰነባብቷል።

"ቅዳሜ ምሽት ተኩስ ነበር። በዚያ ተኩስ ሳቢያ ነው ሁለቱ ነዋሪዎች የተገደሉት። እነሱን የገደለው አካል የቱ እንደሆነ ደግሞ መለየት አልቻልንም" በማለት ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅስ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናግረዋል።

ከተገደሉት ሁለቱ ግለሰቦች አንዱ የጊዳሚ ከተማ ቀበሌ 01 ነዋሪ የነበሩት አቶ ነጋሽ ፉፋ ሲሆኑ ሌላኛው ሟች ደግሞ፤ "ከቄለም ገጠራማ ስፍራ የመጡ ናቸው፤ ማንነታቸውን አለየንም" በማለት የከተማዋ ነዋሪ ተናግረዋል።

የጊዳሚ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ #ደሳለኝ_ቱጁባ በበኩላቸው ሟቾቹ አቶ ነጋሽ ፉፋ እና አቶ ያዕቆብ ቶላ እንደሚባሉ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

"አቶ ነጋሽ ፉፋ ቤት አቅራቢያ በቅኝት ሥራ ላይ በነበሩ የልዩ ፖሊስ እና የሃገር መከላከያ አባላት ላይ ቦንብ ተወረወረ፤ #ተኩስም ተከፈተ" የሚሉት የወረዳው አስተዳዳሪ፤ ቦንምቡን የወረወረው እና ተኩስ የከፈተው አካል አሁን ድረስ እንደማይታወቅ ጠቅሰው፤ ድንገተኛ ጥቃቱ የተሰነዘረው ግን በመንግሥት ኃይሎች ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

#ቢቢሲ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-16-5
አሳዛኝ ዜና!

በአፋር ክልል አደአደር ወረዳ ዛሬ መለሰተኛ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪ ተገልብጦ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና 16 ሰዎች መጎዳታቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መንሰኤ ጥናት ከፍተኛ ባለሙያ ምክትል ኮማንደር መሃመድኑር አደም እንዳሉት አደጋው የደረሰው የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3-20420 አ.አ የሆነ ዶልፊኝ 17ሰዎችን አሳፍሮ ከኮምቦልቻ ከተማ ወደ ሎግያ ከተማ በመጓዝ ላይ እንዳለ ነው።

ተሽከርካሪው ዛሬ ቀን ሰባት ሰዓት አካባቢ በአደአር ወረዳ ካሳጊታ ቀበሌ እንደደረሰ ነው የመገልበጥ አደጋ የገጠመው። በአደጋው ህይወቱ ካለፈው ሌላ 12 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

ምክትል ኮማንደር መሃመድኑር እንዳመለከቱት ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው አራት ሰዎች ደግሞ በአደአር ጤና ጣቢያ ህክምና አግኝተው ወደየቤተሰቦቻቸው ተልከዋል። የሟቹ አስክሬንም ለቤተሰቦች መላኩንና አሽከርካሪውም ተይዞ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን አስረድተዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሚዲያ ሁለት #ስለት ያለው መሳሪያ ነው፤ መልካም ከሰራህበት ትውልድ ታድንበታለህ፤ መጥፎ ነገር ካሳየህበት ደግሞ ትውልድ #እንዲጠፋ ታደርግበታለህ።...በፍፁም አግላይ የሆኑ፣ ስሜታዊ የሆኑ፣ ዘርን አመላካች የሆኑ፣ የሰው ልጆችን ወደክፋት እና ወደጥላቻ ሊወስዱ የሚችሉ ድምፆችን #በፍፁም ሚዲያዎች ይዘው መውጣት የለባቸውም።" ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስራኤል 2ኛውን ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ነው!

እስራኤል ከአምስት ወር በፊት ከተደረገው ሀገራዊ ምርጫ በኋላ ሁለተኛውን ጠቅላላ ምርጫ እያካሄደች ነው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሁለተኛ ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ ያስፈለገው ከአምስት ወር በፊት በተደረገው ምርጫ ቤንጂያሚን ኔታንያሁን ፓርቲያቸው እራሱን ችሎ መንግስት ለመመስረት የሚያስችለውን አብላጫ ድምጽ ማግኘት ባለመቻሉ ነው፡፡

ባለፈው ምርጫ የግራ ዘመመም ከሊኩድ ፓርቲያቸው ከሴንተሪስት ብሉና ኋይት ፓርቲ ጋር ትንቅንቅ የታየበት ፉክክር እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው የሊኩድ፣ የብሉና የኋት ፓርቲዎች ከ120 መቀመጫዎች እንያንዳንዳቸው 35 አግኝተው እንደነበርም አመላክቷል፡፡

በዚሁ ውጤት ኔታንያሁ አሸነፊ መሆናቸውን ለደጋፊዎቻቸው ማብሰራቸውን ተከትሎ የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ኔታንያሁ የጥምር መንግስት ለመመስረት ተገደዋል፡፡

ኔታንያሁ በምርጫ ቅስቀሳው ወቅት በመሪነታቸው የሚቀጥሉ ከሆነ የዮርዳኖስ ሸለቆን ፣ የዌስት ባንክን 30 በመቶ የእስራኤል አካል ለማድረግ ቃል መግባታቸውንም ነው ዘገባው ያስታወሰው፡፡ የአሁኑ ምርጫ እንደተጠናቀቀም አዲስ የጥምር መንግስት ምስረታ ድርድር ይደረጋል ነው የተባለው፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በእኛ ለእኛ የኢትዮጵውያን ወጣት በጎ ፈቃደኞች መርሃ-ግብር የተሰበሰበ ከ34 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው አልባሳትና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ ርክክብ ተደረገ። በተጠናቀቀው የትምህርት ዘመን ከመኖሪያ እና ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ለነበሩ ተማሪዎች ከ300 በላይ በሚሆኑ “በእኛ ለእኛ የኢትዮጵውያን ወጣት በጎ ፈቃደኞች” የአልባሳትና የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብና የበጎ ሥራ አገልግሎት ተግባር ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተዘግቷል!

ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር እሚወሰደው መንገድ #ቆቦ ላይ ተዘግቷል። መኪና እንዳያልፍ ተከልክሎ ወደ ኋላ እስከ 7 ኪሜ ድረስ መንገድ በመኪና ሰልፍ ተዘግቷል። ከአካባቢው የቤተሰባችን አባላት እንደሰማነው ለአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት እየጨፈሩ እየተጓዙ በነበሩ ሰዎች ላይ አንድ መኪና እላያቸው ላይ ወጥቶ የሰዎች ህይወት አልፏል/የሟቾችን ቁጥር ቆየት ብለን እነግራችኃለን/ የመኪናው ሹፌር አምልጧል የአካባቢው ነዋሪዎች ሹፌሩ መያዝ አለበት በሚል መንግዱን ዘግተውታል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BAHIRDAR_INDUSTRIAL_PARK

የባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያው የግንባታ ምእራፍ ተጠናቆ በመስከረም ወር መጨረሻ ሥራ እንደሚጀምር የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለፀ።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አማረ አስገዶም እንደገለፁት፣ የፓርኩ የመጀመሪያው ምእራፍ ግንባታ በ75 ሄክታር መሬት ላይ በውሉ መሰረት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በዚሁ ምእራፍ የተገነቡት የፋብሪካ ሼዶችም ስምንት ሲሆኑ፣ በመጀመሪያው ዙር ለአራት ሺ በሁለተኛው ዙር ደግሞ ለስምንት ሺ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንደ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ፤ በመጀመሪያው ምእራፍ የፓርኩ ግንባታ የሚያስፈልገው የኃይል መጠን ስምንት ሜጋ ዋት በመሆኑ በኃይል አቅርቦቱ ዙሪያ ጥናት ተሰርቶ ተጠናቋል። የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰጪ አካሉም የኤሌክትሪክ ምሰሶ ተከላዎችን ጀምሯል። በዚህ ወር መጨረሻም ለፓርኩ የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ይቀርባል ተብሎ ይታሰባል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ከአዲስ አበባ ወደ ሀረር የሚወስደው መንገድ⬆️
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰን የወጣውን መመሪያ ይፋ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በመመሪያው ዙሪያ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥን ለመቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ መውጣቱን ተናግረዋል።

በዘርፉ ለታክሲ አገልግሎት የሚሰማሩ ተሽከርካሪዎች የታርጋ ቁጥራቸውን ወደ ኮድ 1 እንዲቀይሩ እና ቀለም እንዲቀቡ ይደረጋልም ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም የታክሲ አገልግሎቱን የሚሰጡ አካላት በድርጅት መታቀፍ እንዳለባቸው በመመሪያው መቀመጡንም ገልጸዋል። ሃላፊው አያይዘውም ከዚህ ቀደም ተክልክሎ የነበረው ኮድ 1 ታርጋ ማውጣት መፈቀዱንም አንስተዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከንቲባው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገደሉ!

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ከንቲባ “ማንነታቸው አልታወቀም” በተባሉ ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ ማታ መገደላቸውን የወረዳው አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ!

የ2012 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች #መግቢያ ቀናት እንደሚከተለው እንዲሆን ተወስኗል፦ የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 22-23/2012 ዓ.ም እንዲሁም አዲስ ተማሪዎች ከመስከረም 28-29/2012 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል።

ምንጭ፦አስራት አፀደወይን የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት

የዩኒቨርሲቲ ጉዳዮችን ብቻ በTIKVAH-MAGAZINE ይከታተሉ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#update ኬንያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት የምረጡኝ ዘመቻዋን በይፋ ጀምራለች። ኬንያ ብቸኛዋ የአፍሪካ እጩ ሆና ለመቅረብ የነበራትን ፍላጎትና በአፍሪካ ኅብረት የተላለፈውን ውሳኔ ጅቡቲ ውድቅ አድርጋለች።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia