TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኦነግ አቀባበል⬇️

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የሚደረገው የአቀባበል ስነ ስርዓት ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ #ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ፥ ኦሮሞ ነፃነት ግንባር የፊታችን ቅዳሜ መስከረምን 5 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ደማቅ የአቀባበል ስነ ስርዓት እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ለኦነግ የሚደረገው አቀባበል ስነ ስርዓት ለኦሮሞ ህዝብ ክብር የሚዘጋጅ ነው ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ለኦሮሞ ነፃነት ግንባር የሚደረገው አቀባበል ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ የበኩሉን ሀላፊነት እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

ዶክተር ነገሪ፥ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የዴሞክራሲ ምህዳር መስፋፋቱን ተከትሎ መቀመጫቸውን በውጭ ሀገራት አድርገው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር እየገቡ መሆኑን አንስተዋል።

ከውጭ ሀገራት እየተመለሱ ላሉና ለተመሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም በክልል እና በፌደራል ደረጃ አቀባበል ተደርጎላቸዋልም፤ እየተደረገላቸው ይገኛልም ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ መስከረም 5 2011 ዓ.ም ምህረት የሚደረገው አቀባበል በተለይ ወጣቶች የህዝቡን አንድነት በሚጠብቅ መልኩ እንዲሆን ማድረግ አለበት ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ይህ የአቀባበል ስነ ስርዓት #የማያስደስታቸው አካላት ሊኖሩ ይችላሉ ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ በተለይ ወጣቱ ከእነዚህ አካላት የሚመጡ ትንኮሳዎችን በብስለት ማለፍ እንዳለበትም አሳስበዋል።

እንዲሁም የአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ለየት ያለ ነገር በሚመለከቱበት ወቅት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡም ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

ዶክተር ነገሪ አክለውም፥ ማንኛውም አካል #ይገልፀኛል፤ ይወክለኛል የሚለውን ምልክትና ባንዲራ የመያዝ መብት አለው፤ የተደረገው ትግልም ሀሳብን በነፃነት መግለጽ እንዲቻል ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ከባንዲራ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ በትናንትናው እና በዛሬው እለት የሚስተዋሉ ችግሮች በምንም መስፈርት #ተቀባይነት የሌለ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

አሁን ያለንበት ወቅት ምክንያት ፈልገን የምንጣላበት ሳይሆን ምክንያት ፈልገን አንድነታችንን የምናጠናክርበት ነው ያሉት ዶክተር ነገሪ፥ ማንኛውም አካል ከባንዲራ ጋር በተያያዘ #ሊጋጭ አይገባም ብለዋል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የ˝ፀረ- ጥላቻ ንግግር˝ን አዋጅ አያረቀቀ ነዉ፦

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅ በተጨማሪ በርካታ ህጎችን በማሻሻል ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል፡፡ በጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዝናቡ ቱኑ እንደተናገሩት የ˝ፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅን የሰዎችን የመናገር ነፃነት #ሊገድብ በማይችል መልኩ እና ከህግ መንግስቱ ጋር #ሊጋጭ በማይችል መልኩ ለማፅደቅ አስፈላጊ ጥናቶች ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ ከሌሎች ህጎች ፈጥኖ የሚጸድቀው ይህ ˝የፀረ ጥላቻ ንግግር˝ አዋጅ ኢትዮጵያ ላይ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ብሄሮች እና ማንነቶች ላይ በጥላቻ ንግግር ምክንያት የሚደርሰውን ችግር እና ግጭት ለማስቀረት እንደሚያግዝ አቶ ዝናቡ ተናግረዋል፡፡

Via Arts TV World
@tsegabwolde @tikvahethiopia