TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሂጅራ_ባንክ

ሂጅራ ባንክ የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ሂጅራ ባንክ አክሲዮን መሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ከብሄራዊ ባንክ ካገኘ አንድ ወር እንደሞላው ነው የተገለጸው፡፡

የሂጅራ ባንክ አክስዮን አደራጆች ሰብሳቢ አቶ አህባብ አብድላ እንዳሉት ላለፉት ሁለት አመታት በሀገር ደረጃ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲፈጠር የተለያዩ ጥናቶችን ሲያከናውኑ እንደቆዩ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ ከወለድ ነጻ የፋይናንስ ስርአትን በማበልጸግ ለዘመናት በሀገራችን ምጣኔ ሀብታዊ እንቅቃሴ ውስጥ ባለው ውስን ተሳትፎ የሚታወቀውን የህብረተሰብ ክፍል በሀገሪቱ እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እንዲኖረው የማስቻል ስራ መስራቱንን ገልጿል።

የሂጅራ ባንክ አክሲዮን ማህበር አነስተኛው የአክሲዮን ሽያጭ 30ሺህ ብር ሲሆን ከፍተኛው የአክሲዮን ሽያጭ ደግሞ 20 ሚሊየን ብር ነው ተብሏል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ አንድ ቢሊየን ብር የአክሲዮን ሽያጭ ለመሸጥ እንዳሰበም ተገለጿል፡፡

Via #ኢትዮ_ኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሂጅራ_ባንክ

ከወራት በፊት ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ ባንክ ሆኖ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን የመጨረሻ ፈቃድ ከብሄራዊ ባንክ ያገኘው ሂጅራ ባንክ ዛሬ ህንፃውን አስመርቋል።

ሂጅራ ባንክ ዛሬ ያስመረቀው "ቦሌ ደንበል ፊት ለፊት" የሚገኘውን ለዋና መስሪያ ቤት እና አብይ ቅርጫፍ አገልግሎት እንዲውል የገዛውን ህንፃ መሆኑን ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ ይፋዊ ፌስቡክ ገፅ ተመልክተናል።

በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ ምሁራን ፣ ባለሀብቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተው ነበር።

ሂጅራ ባንክ በአጭር ጊዜ ውስጥ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር መገለፁን ደግሞ ከሀሩን ሚዲያ ተመልክተናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT