TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ተፈናቃዮችን ለማቋቋም ቴሌቶን ተዘጅቷል‼️

በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጭ #የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡

ነገ መጋቢት 7 ቀን 2011ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን ተዘጋጅቷል፡፡

በአማራ ክልል እና ከክልሉ ውጭ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ነው 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብሩ የሚያስፈልገው፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት ተፈናቃዮቹን ለመርዳት በጊዜያዊነት የሰብዓዊ ዕርዳታዎችን እያደረገ መሆኑንና በዘላቂነት ደግሞ መልሶ ለማቋቋም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን እና የቁሳቁስ ድጋፍ ለመሰብሰብም ነገ መጋቢት 7 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ቴሌቶን ለማዘጋጀት መርሀ-ግብር ተይዟል፡፡

በዝግጅቱ ዕርዳታ ከመሰብሰብ ባሻገር የአብሮነት እና የአንድነት መልዕክቶች እንደሚተላለፉም ታውቋል፡፡

አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለበትን የምጣኔ ሀብት ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት #ከተመረጡ አካላት ብቻ ዕርዳታ የመሰብሰብ ሥራዎችም ተጀምረዋል፡፡ በዚህም ከባለሀብቶች፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች፣ ከዲያስፖራዎች እና ሌሎች አካላት ዕርዳታ ለማግኘት ንዑስ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ወደ ተግባር መገባቱንም አልማን ዋቢ አድርጎ አብመድ ዘግቦ ነበር፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያ ቴሌቶኑ 90 ሺህ 736 ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡ ከቤታቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ አርሶ አደሮች የክረምት ጊዜ ከመድረሱ በፊት ለእርሻ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ማሟላትም ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ተልዕኮውን ‹‹አግዛለሁ›› የሚል እና ዕርዳታ ለማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ቅን ዜጋ በተለያዩ ባንኮች በተከፈቱ የሒሳብ ቁጥሮች ማስገባት እንዲችልም ቁጥሮቹ ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህ መሠረት፡-

•ዓባይ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡ 25 62 11 25 41 58 017፣

• አቢሲኒያ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡ 16 24 11 37፣

•የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሒሳብ ቁጥር፡ 10 00 25 82 50 811 ናቸው፡፡

በሸራተን አዲስ ሆቴል በሚኖረው መርሀ-ግብር በቀጥታ ስልክ እየደወሉ ድጋፋቸውን መግለጽ ለሚፈልጉ ሁሉ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሮች አገልግሎት እንደሚሰጡ ተነግሯል፡፡ ቁጥሮቹም፡-

09 08 91 91 91
09 08 92 92 92
09 08 93 93 93
09 08 94 94 94 ናቸው።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia