TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰመራ

"...አብዛኛዎቹ #የመንግስት ቤቶች በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው"
.
.
#በሰመራ_ሎግያ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 200 የመንግሰት ቤቶች መካከል በህጋዊ ውል የተያዙት ከ35 እንደማይበልጡ የአስተዳደሩ ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፅህፈት ቤት በበኩሉ ከ2 እስከ 10 ዓመት ድረስ የቤት ኪራይ ባልከፈሉና የመንግስት ቤት በህገ ወጥ መንገድ በያዙ ግለሰቦች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንጂነር ራሁባ ሙሀመድ እንደገለጹት በመንግስት ቤት ከሚኖሩ 200 አባውሯዎች መካከል ህጋዊ ውል ያላቸው 35ቱ ብቻ ናቸው። “ቀሪዎቹ 165 አባወሯዎች ከፅህፈት ቤቱ እውቅና ውጪ ቁልፍ ገዝተውና በህገወጥ መንገድ ቤቶቹን በእጃቸው ያስገቡ ናቸው” ብለዋል። ህጋዊ ውል ያላቸውም ቢሆኑ በመንግስት የክትትልና ቁጥጥር ድክመት ምክንያት ከ2 እስከ 10 ዓመት ድረስ ያልከፈሉት ከ300 ሺህ ብር በላይ #ውዝፍ የቤት ኪራይ ዕዳ ያለባቸው ከ100 በላይ ሰዎች እንዳሉ በቅርቡ በተደረገው የማጣራት ስራ መረጋገጡን ኢንጂነር ራሁባ ገልፀዋል። የመንግስት ቤቶችን በህገወጥ መንገድ  ባስተላለፉ፣ ቤቶቹን በያዙና ለረጅም ዓመታት የቤት ኪራይ ባልከፈሉ ግለሰቦች ላይ እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ ክስ እንደሚመሰረትም ኃላፊዋ አስታውቀዋል።

Via #ena
ፎቶ፦ ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia