TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የሥራ ማቆም አድማ መትተዉ የነበሩት #የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸዉ ለመመለስ #ተስማሙ። የአሠሪዉ ኩባንያ ኃላፊዎችና የሠራተኞቹ ተወካዮች በተከታታይ ሲደራደሩ ነበር። የሠራተኞቹ ተወካዮች ለDW እንደነገሩት ሠራተኞቹ ነገ #ሥራ ለመጀመር ተስማምተዋል። ሠራተኞቹ አድማዉን አቁመዉ ወደ ሥራ ለመመለስ የወሰኑት በደል አድርሰዉብናል በማለት ቅሬታ አቅርበዉባቸዉ ከነበሩ ኃላፊዎች ሁለቱን አሠሪዉ ድርጅት ከሥራ #በማገዱ ነዉ። የዶቸ ቬለ ምንጮች እንዳረጋገጡት እገዳ የተጣለባቸው ሁለቱ ኃላፊዎች ግድቡን በኮንትራት በሚገነባዉ በሳሊኒ ኩባንያ ወስጥ በከፍተኛ የሰው ሀብትና የፋይናንስ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ይሠሩ የነበሩ ናቸዉ።ወደ ስድስት ሺሕ የሚጠጉ የኮይሻ ግድብ ሠራተኞች የስራ ማቆም አድማ የመቱት ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia