TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
“ገፍተው ገፍተው #ወደማንፈልግበት ሁኔታ ሊከቱን የሚፈልጉ ሰዎች(አካላት) አሉ፤ #የመቻቻል ጥቅሙ ለራስ ሲባል እንጂ ለመለያየት አንድ ቀን በቂ ነው፡፡ ግለሰቦች በየመድረኩና በየመገናኛ ብዙኃን ሕዝብ #እንዲለያይ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ በመሆኑ፣ እኛ #ኢትዮጵያውያን ቆም ብለን ይኼ #ፖለቲካ እያደገ ነው? ወይስ ወደኋላ እየሄደ? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት አለብን። ከ30 ዓመታት በኋላ ወደ 1960ዎቹ ልንመለስ ነው? ወይስ እያደግን ነው? የሚለው ላይ በጥሞና መወያየትና መነጋገር ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም #ካልተቻቻለ ሁሉንም ልትጠቅም የምትችል አንዲት ኢትዮጵያ መፍጠር እንደማይቻል አውቀን አንድነትን የሚጎዱ ነገሮች ሁሉም ሊያወግዟቸው ይገባል፡፡ ከምንም በላይ #ሕዝቡ ማውገዝ ያለበት የብሔር ብሔረሰቦችን አጀንዳ እያነሱ አንደኛው ወገን በሌላኛው ወገን ላይ የሚያሳያቸውን #ጥላቻዎች ነው።”

ክቡር ዶ/ር #ለማ_መገርሳ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ ውሉ በጠፋና ተለዋዋጭ በሆነ ጊዜ ውስጥ ናት " - ጥናት

አገር በቀሉ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ተቋም የማኅበራዊ ጥናት መድረክ (ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ) ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ውሉ በጠፋና ተለዋዋጭ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንደምትገኝ ገለጸ፡፡ 

ይፋ ባደረገው ጥናቱ የኢትዮጵያን ወቅታዊና የወደፊት መፃዒ ሁኔታ ዳሷል፡፡

"ኢትዮጵያ ወዴት? ቢሆንታዎች" በሚል ርዕስ የቀረበው ይኼው ጥናት የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ መንገራገጭ፣ የሐምሌ ጨለማና ፀደይ በማለት በሦስት ቢሆንታዎች (Scenarios) ለማስቀመጥ የሞከረ ነበር፡፡

የቢሆንታዎችን ምንነትን ወደኋላ በመመለስ ከታሪካዊ ዳራ ተነስቶ ብይን ለመስጠት የሚሞክረው ጥናቱ፣ የወቅቱን የአገሪቱን ሁኔታም ፍቺ ለመስጠት ሞክሯል፡፡

" በአንድ ማኅበረሰብ የመንግሥት ተዓማኒነት እየተሽከረከረ ሲሄድ፣ ማኅበረሰባዊ ትስስር ሲመነምንና በሕዝብ ዘንድ የፍትሕ መጓደል/ ተበዳይነት ስሜቶች ሲያንዣብቡ #ጽንፈኝነት ይነግሣል " በማለት ነው ይኸው ጥናት የኢትዮጵያን ገጽታ በማስቀመጥ ወደ ሐተታው የሚንደረደረው።

ጥናቱ በአሁኗ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች እንደሚታዩ ገልጾ ፖለቲካዊ መግባባት በአገሪቱ መፍጠር ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑን ያሰምርበታል፡፡

ያም ቢሆን ግን ባለፉት 50 ዓመታት በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች ችግሮችን ተወያይቶ የመፍታት ባህል አለመዳበሩ ትልቁ ራስ ምታት እንደሆነ ያወሳል፡፡

በዘውዳዊው ሥርዓት መውደቅ ማግሥት አምባገነናዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ በማቆጥቆጡ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ተስፋው መምከኑን ያስረዳል፡፡

ደርግ ወድቆ በ1983 ዓ/ም የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ " የሕዝቦች እኩልነት ይፈጠራል " የሚል ተስፋ መፈጠሩን ይሁን እንጂ ይህንን ለውጥ ተከትሎ የተቀረፀው ሕገ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ይፈጥራል ቢባልም ነገር ግን በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የጭቅጭቅ ምዕራፍ መክፈቱን ያትታል፡፡

በየታሪክ ምዕራፉ ለዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሽግግር ተስፋ የፈነጠቁ አጋጣሚዎችን አለፍ ገደም እያለ የሚዘረዝረው ጥናቱ፣ በ2010 ዓ.ም. የተፈጠረውን የፖለቲካ ለውጥ እንደ አንዱ አጋጣሚ ያነሳዋል፡፡ 

" ለውጡ ከፈጠረው ከፍተኛ የሕዝብ ፈንጠዚያ ጀርባ ግን በለውጥ አቀንቃኞችና በቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎች መካከል ውስጥ ውስጡን ውጥረት ሰፈነ " ይላል፡፡

የአዲስ ተስፋው ፍንጣቂ በለውጡ  ማግሥት ብዙም ሳይዘገይ በመጣው " የነውጥ ጊዜ " እንደተተካም ነው ጥናት ያመላከተው፡፡

የኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ታሪክ በብዙ ፈታኝ ውጣ ውረዶች ውስጥ የማለፍ አስገራሚ ፅናት የተላበሰ መሆኑን ጥናቱ ያብራራል፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል ግን ፈላጭ ቆራጭነት የሰፈነበት ሆኖ መቆየቱን ይገልጻል። በኢኮኖሚውም መስክ በአስከፊ ድህነት ውስጥ አገሪቱ ተዘፍቃ መኖሯን ያትታል፡፡

ከዚህ ሁሉ ተነስቶ አገሪቱ የሐምሌ ጨለማ፣ መንገጫገጭና ፀደይ የሚል ስም የተሰጣቸው ቢሆንታዎችን ልታስተናግድ እንደምትችል ሰፊ ትንተና ያቀርባል፡፡

በሌላ በኩል የመበታተን አደጋን እንደ አንድ ቢሆንታ ያነሳዋል። " አስደንጋጭ ቢሆንም የአገሪቱ የመበታተን አደጋ የማይታሰብ ነው ለማለት አይቻልም " ሲል ነው ጥናቱ ያብራራው።

ጥናቱ ከአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ እስከ አየር ንብረት ለውጥ #ከሃይማኖት እና #ፖለቲካ ፅንፈኝነት እስከ የብሔርና ያልተማከለ አስተዳደር ውጥረት አገሪቱን ሊፈትኑ የሚችሉ ነጥቦችን ይፈትሻል፡፡

ከኢኮኖሚ አለመረጋጋት እስከ የዋጋ ንረት ውጣ ውረዶንችም ያነሳል፡፡

በሌላ በኩል፤ የአማራ ክልልና አገሪቱን ወጥረው የያዙ በየአቅጣጫው ያሉ የግጭት ሁኔታዎችን ተፅዕኖም የፈተሸ ነው። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia