ማር ሲል ቴሌቪዥን በ2012 መስከረም ወር ላይ ትምህርት ለሚጀምሩ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። ድጋፉ የተደረገው ለምዕራብ አርሲ ዞን አርሲ ነገሌ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሲሆን አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ፣ የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና የማር ሲል ቴሌቪዥን የሚዲያ አባላት ትናንት በአርሲ ነገሌ ከተማ አርሲ ነገሌ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት በመገኘት የመማሪያ ቁሳቁሱን አበርክተዋል። የመማሪያ ቁሳቁሱም የተሰበሰበው በመልካም ወጣት 2011 በሰባቱም ዙር ከተሳተፉ መልካም ወጣቶች ነው። ማር ሲል ቴሌቪዥን በ2012 ዓ.ም ትምህርት ለሚጀምሩ ተማሪዎችም መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ተመኝቷል።
Via #MarcilTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #MarcilTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia