TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦሮሚያ ክልል⬇️

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ሕገ ወጥነትን ለመከላከል በተሰራው ስራ የተለያዩ ሕጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

#ሱሉልታ

በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር
ውለዋል፡፡

#ሻሸመኔ

ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ቡራዩ

የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት ሲጠይቅ የነበረ፣ ቲተር: ማዕተምና የመታወቂያ ወረቀት በቄሮ ስም አዘጋጅቶ በመሸጥ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

#ለገጣፎ_ለገዳዲ

በቄሮ ስም የ62 ወጣቶችን ፎቶ በማሰባሰብና ወረቀት ላይ በመለጠፍ የቄሮ አደረጃጀት ከቀበሌ እስከ ላይ መኖር አለበት በሚል ወጣቶችን
ሲያታልሉና ሲያደረጁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ጅማ

በሕገ ወጥ ስራ ላይ ተሰማርተው ሕገ ወጥ ግንባታ ሲያካሄዱ የነበሩ 42 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰዎች ላይ ሙሉ መረጃ ተሰባስቦ ለሕግ ሊቀርቡ ነው፡፡
ድንገት በተደረገው ፍተሻም 2ሽጉጥና 180 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

#አዳማ

በቅርቡ በከተማው ለተከሰተው ግጭት መነሻ በመሆን ሰዎችን ሲያነሳሱ የነበሩና ግጭቱ የብሔር መልክ እንዲይዝ አድርገዋል የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ሞጆ

ጨለማን ተገን በማድረግ ፋብሪካን ለመዝረፍ ሲንቀሳቁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በአንደኛው ግለሰብ እጅ ሽጉጥ ተይዟል፡፡

#ሰበታ

በሕገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሰማሩ፣ ምግብ ቤት ገብተው በመመገብ ሒሳብ የማይከፍሉና ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከተማ በሆነችው #ለገጣፎ_ለገዳዲ የክልሉ መንግሥት ዛሬም በርካታ መኖሪያ ቤቶችን ማፍረሱን ቀጥሏል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ያለ መጠለያ ቀርተዋል- ብሏል አዲስ ስታንዳርድ ፡፡ ትናንት 48 ቤቶች የፈረሱ ሲሆን በቀጣይ ሳምንታት ከ12 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶች ይፈርሳሉ ተብሏል፡፡ የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ሐቢባ ሲራጅ ቤቶቹ ሕገ ወጥ ናቸው ይላሉ፤ በርካቶች ነዋሪዎች ግን በተለይ ከ2000 ዓ.ም ወዲህ ሕጋዊ መስፈርቶችን ሁሉ አሟልተው የገዟቸው ወይም የገነቧቸው ቤቶች እየፈረሱባቸው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

Via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia