TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Somalia #SW

ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር ተገደሉ።

የሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ክልል ፍትህ ሚኒስትር ሀሰን ኢብራሂም ሉግቡር በባይዶዋ ከነ ልጃቸው በአጥፍቶ ጠፊ የቦንብ ጥቃት ተገደሉ።

ሚኒስትሩ የተገደሉት ዛሬ ዓርብ ዕለት ከመስጂድ ሲወጡ በተፈፀመ ጥቃት ነው።

በጥቃቱ ሌሎች 11 ሰዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ለጥቃቱ ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።

የደቡብ ምዕራብ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ ግድያውንና ጥቃቱን አውግዘው ከጥቃቱ ጀርባ የአልሸባብ የሽብር ቡድን መኖሩን አመልክተዋል።

ይህ ጥቃት በያዝነው ወር እኤአ በቀን 27 በታችኛው ሸበል ክልል የማርካ ወረዳ አስተዳዳሪ አብዱላሂ አሊ ዋፎውን ጨምሮ ከ10 በላይ ሰዎችን ከገደለው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት እንዲሁም በአፍጎዬ ከተማ ፍንዳታ ተከስቶ ቢያንስ አራት ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች ከቆሰሉበት ጥቃት ከቀናት በኃላ የተፈፀመ ነው።

በሌላ በኩል፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን ዛሬ #ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰነው የሶማሊያዋ የድንበር ከተማ " አቶ " ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልወደዱ የሶማሌ ክልል ባለሥልጣን በሰጡት ቃል ፤ የሽብር ቡድኑ አቶ ላይ በ2 ሳምንት ውስጥ ለ2ኛ ጊዜ ጥቃት መሰንዘሩን ይህን ተከትሎ ውጊያ መካሄዱን አመልክተዋል።

ዛሬ ወደ አቶ ዘልቆ ጥቃት የመፈጸም ዓላማ የነበረው የአልሻባብ ታጣቂ ኃይል፤ ያሰበው ሳይሳካ #ሽንፈት እንዳጋጠመው ተናግረዋል።

በፀጥታ ኃይሎችም በኩል ጉዳት መድረሱን ያመለከቱት ባለስልጣኑ ለጊዜው ዝርዝር መናገር አልችልም ብለዋል።

አልሸባብ ከጥቂት ቀናት በፊት ኢትዮጵያን ለመዳፈር ሞክሮ በሶማሌ ልዩ ኃይል ክፉኛ መመታቱ አይዘነጋም። አሁንም በድንበር የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩን ለማወቅ ችለናል።

@tikvahethiopia