TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የሚሰጠው የመታወቂያ ካርድ #ይዘትና ንድፍ ለካቢኔ ቀረበ፡፡ በምክትል ከንቲባ #ታከለ_ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በቀረቡለት ሁለት አማራጮች ላይ ከመከረ በኋላ አንዱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎች ምዝገባና የመታወቂያ አሰጣጥ መመርያ ቁጥር 3/2010 መሠረት የተዘጋጀው አዲሱ መታወቂያ፣ ከቀድሞው የሚለይባቸው ይዘቶች አሉ፡፡

አዲሱ መታወቂያ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪ መታወቂያ›› የሚል ሲሆን፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ መግለጫ አልያዘም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የትውልድ ሥፍራና #የብሔር ስያሜ ያላካተተ ሲሆን፣ ዜግነትን በልዩነት አካቶ ይዟል፡፡

የአዲሱ መታወቂያ የምዝገባ ሒደት በኮምፒዩተር የታገዘ የዲጂታል አሠራር የሚከተል ሲሆን፣ በአሻራ የተደገፈ ነው፡፡

መታወቂያው በአማራጭ #በሁለት ቀለማት በመዘጋጀቱ፣ ካቢኔው የሚመርጠው አንደኛው ንድፍ ተቀባይነት እንደሚያገኝ ተመልክቷል፡፡

የመታወቂያ አሰጣጥ ሒደቱንና ይዘቱን እንደ አዲስ ማዘጋጀት ያስፈለገው፣ የቀድሞው መታወቂያ #ብሔርን የሚያጎላና #አንድነትን የሚያላላ በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

ምክትል ከንቲባ ታከለ እንዳሉት የቀድሞው መታወቂያ ቀላል ቢመስልም ከፍተኛ ቅሬታ ሲነሳበት ቆይቷል፡፡ የመታወቂያውን ይዘት በማስተካከል፣ አንድነትን ማጎልበት ያሻል በሚል ዕርምጃው መወሰዱ ተመልክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም መታወቂያ አሰጣጡ አሻራን የሚጠቀምና ዲጂታል ስለሆነ፣ ሕገወጦችን ለመቆጣጠር አመቺ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በአዲሱ መታወቂያ ከዚህ ቀደም ይፈጸሙ የነበሩ ማጭበርበሮችን ማከናወን እንደማይቻል፣ በምርጫ ጊዜ ተደጋጋሚ ምዝገባ ማድረግ እንደማይቻልና ሌሎች ሕገወጦች ድርጊቶችን መፈጸም አይቻልም ተብሏል፡፡

መታወቂያው ለካቢኔው ቀርቦ ይሁንታ ካገኘ በኋላ የሕዝብ አስተያየት እንደሚሰጥበት ተጠቁሟል፡፡ ከዚህ በኋላ በቅርቡ የነዋሪዎች ምዝገባ እንደሚጀመር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአዲሱ መታወቂያ አጠቃላይ ወጪ ኅትመትን ጨምሮ 300 ብር ያህል ቢሆንም፣ ነዋሪዎች ግን የሚከፍሉት የካርዱን ዋጋ ብቻ 80 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

©ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ‼️

(15.04.2011ዓ.ም የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)

ወቅታዊ የሀዋሳ ከተማን #ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በከተማው አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የተሰጣዊ ዜጣዊ መግለጫ፦

ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኗ በግልፅ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በከተማችን ሀዋሳም አልፎአልፎ አሉታዊ ክስተቶች ይስተዋላሉ፡፡

ከእነዚህ አሉታዊ ክስተቶች መካከል ከሰኔ 10/2010 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችና የፀጥታ መናጋት በቀዳሚነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ይህን አልፎ አልፎ የሚከሰተው ግጭት ሀዋሳ ከተማ የምትታወቅበትን ነዋሪዎቿ ለዘመናት ያዳበሩት የመከአበክሮ የመፈቃቀድ እና አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር መንግስት አበክሮ በመስራት ላይ ነው፡፡

በከተማዋ ለዘመናት የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት ለማጠልሽት፣ ቅሬታ ለመፍጠርና የጥላቻ ጥቁር ነጥብ ጥለው ለማለፍ የሚዳክሩ አካላትን ጥረት ለማክሸፍና የህግ የበላይነትን ለማስፈን ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ ግጭቶች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሀይሎችን ለህግ በማቅረብ ባጠፉት ልክ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ቀጥላል፡፡

ይሁንና ፀረ-ሰላም ሀይሉ ከድርጊቱ ባለመቆጠብ የተሳሳተ የትግል ስልቱን በመቀያየር የእውቀት መገበያያ የሆነውን ትምህርት ቤት የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በሀዋሳ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሚገኘው አዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት
ቤት ሁከትና እረብሻ በመፍጠር 12 ወጣቶች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ተማሪ ያልሆኑ መሆናቸው ተለይቷል፡፡

በግጭቱም እርስበእርስ ድንጋይ በመወራወር በአስሩ ላይ ቀላል ጉዳት እንዲሁም ለፀጥታ ሀይሉ ባለመታዘዝ በሁለቱ ላይ ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ወጣቶች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የረብሻው መንስኤ ገና በፀጥታ ሀይሉ #በመጣራት ላይ ያለ ቢሆንም በርካታ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካላት ያልሆኑ ነገር ግን እራሳችውን ከተማሪ ጋር ያመሳሰሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ተማሪዎችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከተዋል፡፡

ክስተቱን #የብሔር_ግጭት ቅርፅ ለማስያዝ ጥረት ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገው የከተማው ነዋሪ ግን አልተባበራቸውምና ልፋታቸው ሳይሳካ #መና ሆኖ ቀርቷል፡፡

በዚህ ድርጊት #ጠንሳሽነትና ተሳታፊነት የተጠረጠሩ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም
ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ሀይሉና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት የከተማው #ፀጥታ_ሁኔታ ወደነበረበት የተመለሰ ሲሆን ለከተማው ሰላም ወዳድ ህዝብ የከተማው አስተዳደር ያለውን ክብርና አድናቆት እየገለፀ በቀጣይም ነዋሪው ከመንግስት ጎን በመቆም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስና አብሮ የመኖር እሴትን ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላትን አጋልጦ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን እያቀረበ የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሰላም እና ፀጥታ የማስጠበቅ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ዲጂታል የነዋሪዎች መታወቂያ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ መስጠት እንደምትጀምር የከተማዋ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አስታወቀ። አዲሱ የዲጂታል መታወቂያ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አገልግሎቱ የሚጀመር ሲሆን ለዚህም በቂ መታወቂያ ካርዶች መዘጋጀታቸውን በኤጀንሲው የነዋሪዎች አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አብዱራሂም ገልጸዋል። በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአዲሱ መታወቂያ አሰጣጥ ጥንካሬና ድክመት ታይቶ በቀጣይ በሁሉም ክፍለ ከተማ ወረዳዎች መስጠት ይጀመራል ብለዋል። አዲሱ መታወቂያ #የብሔር ማንነትና የትውልድ ቦታ የሚገልጽ ይዘት የሌለው ሲሆን በአንጻሩ የደም ዓይነት እንዲጠቀስ መደረጉም ተገልጿል። የነዋሪዎች መታወቂያ አገልግሎት መዘመን በመታወቂያ ማጭበርበርን ለመቀነስ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ያነሱት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ መታወቂያ አሰጣጡ ደረጃውን የጠበቀና በአሻራ የተደገፈ እንደሆነም ጠቁመዋል። ደህንነቱ የተጠናከረ የነዋሪዎች መረጃ ምዝገባ ሶፍትዌር፣ የመታወቂያ ማተሚያና የአሻራ መቀበያ መሳሪያዎች መዘጋታቸውንም ተናግረዋል። ኢዜአ እንደዘገበው አገልግሎቱ የኢንተርኔት አቅርቦትን የሚፈለግ በመሆኑ የኔትወርክ መቆራረጥ እንዳያጋጥም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር እየሰሩ ነውም ብለዋል። ነባሩ መታወቂያ በዲጂታል ሙሉ ለሙሉ እስኪቀየር ድረስ የወረቀት መታወቂያ አሰጣጡ #እንደማይቋረጥም አቶ መሐመድ ገልጸዋል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የወላይታ_ሶዶ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ ማጠቃለያውን በሶዶ ስታዲየም እያደረገ ይገኛል፦

√ጋሞ፣ ጎፋ፣ ሲዳማ፣ ዳውሮ የወላይታ #ወንድም ሕዝቦች ናቸው!

√ኢትዮጵያዊነት #ፀጋ እንጂ ኩነኔ ሊሆን አይገባም!

√የኢንዱስትሪ ፓርኮች #ለወላይታ!

√ወላይታ #የብሔር ጠላት የለውም!

√ልማት ለወላይታ፣ #ፍትህ ለወላይታ

√ለሕገመንግስታዊ ጥያቄ ሕገመንግስታዊ መልስ ይሰጠን!

√ወላይታ #ፍቅር ነው ሁሉን #ያቅፋል!

Via ናትናኤል መኮንን & TIKVAH-ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ፈተናውን ብዙዎቹ ሊያልፉ ይችላል የሚል ግምት ነው የተያዘው " - የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል #ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል።

በቅርቡ ለሚተገብረው #የሠራተኞች_ድልድል ሲባል ከ14 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና ይቀመጣሉ።

ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ባለፉት ሳምንታት ከሠራተኞቹ ጋር ውይይት ሲያደርግ ቆይቷል ተብሏል።

163 ሺህ ገደማ ሠራተኞች በስሩ ያሉት አስተዳደሩ ፤ በሚተገበረው ለውጥ ውስጥ ከተካተቱ ጉዳዮች መካከል የከተማዋን የመንግሥት ሠራተኞችን በአዲስ መልኩ መደልደል የሚለው ይገኝበታል።

ለለውጡ ትግበራ ተብሎ የተዘጋጀ #የሥልጠና_ሰነድ ምን ይላል ?

-አሁን በመጀመሪያው ዙር ድልድል እንዲተገበርባቸው የተመረጡት አስራ ስድስት (16) ተቋማት ናቸው። ከእነዚህም መካከል ፦

* የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር፣
* ቤቶች ልማት እና አስተዳደር፣ ትራንስፖርት፣
* ፐብሊክ ሰርቨሲ እና ሰው ሀብት ልማት፣
* ፕላን እና ልማት፣
* ሥራ እና ክህሎት፣
* ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮዎች
* ቤቶች ኮርፖሬሽን፣
* ኅብረት ሥራ ኮሚሽን እንዲሁም ሌሎች የከተማይቱ ኤጀንሲዎች እና ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቶች ይገኙበታል።

- የተዘረዘሩት መስሪያ ቤቶች ድልድል የሚደረግባቸው በማዕከል ቢሮዎቻቸው ብቻ ሳይሆን ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ላይ ባሉ ጽህፈት ቤቶቻቸው ጭምር ነው።

የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ምን አሉ ?

° ከላይ የዘረዘሩት መስሪያ ቤቶች ለመጀመሪያው ዙር ትግበራ የተመረጡት ብዙ ተገልጋይ የሚያስተናግዱ እንዲሁም ብልሹ አሰራር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ብዙ መጓደል ያለባቸው በመሆናቸው ነው።

° የሠራተኞች ድልድል ከመከናወኑ በፊት የእነዚህ መ/ቤቶች ሠራተኞች ለፈተና ይቀመጣሉ።

° ፈተና ለመስጠት የታቀደው የሠራተኞቹን የብቃት ደረጃ ለማረጋገጥ ነው።

° ፈተናው የባህሪ እና የቴክኒክ ምዘናዎችን የያዘ ነው። የሚሰጠው የቴክኒክ ምዘና ሠራተኞቹ ከሚሠሩት ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ነው። የባህሪው ፈተና ደግሞ አገልግሎት አሰጣጡን የሚፈታተኑ የባህሪ ችግሮች ስላሉ ያንን ክፍተት ለመሙላት አመላካች እንዲሆን ተስቦ የተዘጋጀ ነው።

° የምዘና ፈተናው የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በጋራ ትብብር ነው።

° ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርስቲ / በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው።

° እስካሁን ባለው መረጃም ነገ ፈተናውን የሚወስዱ ሠራተኞች ቁጥር ከ14 ሺህ በላይ ነው።

° ፈተናውን የማያልፉ ሠራተኞች እንዳይኖሩ ዝግጅት እንዲያደርጉ፣ እንዲያጠኑ ተነግሯል። ፈተናው ለማለፍ በሚያስቸግር መንገድ በጣም የተወሳሰበ፣ አብስትራክት እና ንድፈ ሀሳባዊ የሆነ ሳይሆን የሠራተኞችን አቅም ለመለካት አመላካች ሆኖ ነው የተዘጋጀ ነው።

° ብዙዎቹ ሊያልፉ ይችላል የሚል ግምት ነው የተያዘው።

የሪፎርም ሥልጠና ሰነዱ ምን ይላል ?

- የከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ፈተናውን ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

- ከዚህ የማለፊያ ውጤት በታች የሆነ ነጥብ ያገኘ ባለሙያ ከደረጃው ዝቅ ብሎ ባሉት የአስተዳደር እርከኖች ላይ ይመደባል።

- ለዳይሬክተሮች እና ለቡድን መሪዎች የተቀመጠው የፈተና ማለፊያ ነጥብ 60 በመቶ ነው። ይህን ነጥብ የማያስመዘግቡ አመራሮች ለዳይሬክተርነት ወይም ለቡድን መሪነት ኃላፊነት #መወዳደር_አልችሉም

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ፦

ሠራተኞች ፈተናውን ማያልፉ ከሆነ ዝቅ ተደርገው ሊመደቡ ይችላሉ። ድልድሉ ሲያልቅ ሌሎች አማራጮች ታይተው ምን ሊደረግ እንደሚችል የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅሞ መፍትሄ ይፈለግላቸዋል።

በአዲስ መልኩ #ሠራተኞች ሲደለደሉ ከፈተናም በተጨማሪ ሌሎች መስፈርቶችን ይኖራሉ።

- ሰነዱ የሠራተኞች ድልድልን በተመለከተ " ትኩረትን የሚሹ አዳዲስ ጉዳዮች " በሚል ካስቀመጣቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የብሔር ብሔረሰቦች ስብጥር ጉዳይ ነው።

- ድልድሉ ሲከናወን " ሕብረ ብሔራዊነትና አካታችነት በጥንቃቄ " መተግበር እንዳለበት በሰነዱ ላይ ሰፍሯል።

- " አካታችነትና ፍትሐዊነትን " በሚመለከተው የሰነዱ ክፍል ላይ በዳይሬክተርነት እና ቡድን መሪነት የሥራ መደቦች ላይ አመራሮች ሲመደቡ " የሜሪት ሥርዓት " ይጠበቃል።

- የአመራሮች ድልድል "የብሔር ብሔረሰብ ስብጥርን ባካተተ እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ " ይከናወናል።

- በመ/ቤቱ ካሉ የሥራ መደቦች መካከል በተመሳሳይ ማንነት የተያዙት ከ40 በመቶ መብለጥ የለባቸውም።

- መ/ቤቶቹ ድልድሉን ሲያከናውኑ ይህንን #የብሔር ስብጥሩን ለመጠበቅ እንዲችሉ " ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ከሌሎች መ/ ቤቶች በመለየት በዝውውር እንዲሟሉ " ይደረጋል።

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ ፦

ከ40% መብለጥ የለበትም በሚል የተቀመጠው አሠራር፤ የሚተገበረው የቡድን መሪዎች እንዲሁም የዳይሬክተሮች ድልድል ላይ ብቻ ነው።

በዚህ ድልድል ወደ #ሠራተኛው የወረደ እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። የድልድል ደንቡ ውስጥም የለም።

የተመሳሳይ ማንነት ያላቸው ከተወሰነ ፐርሰንት በላይ መሆን የለበትም የሚለው ለዳይሬክተሮች እና ለቡድን መሪዎች ነው።

ከተማዋ የአገሪቱ ዋና ከተማ ናት። ብዙ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ያሉባት ስለሆነች ያንን ሥዕል የሚያሳይ እንዲሆን መደረግ ስላለበት የተቀመጠ ነገር ነው።

ይህ የአገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርምና የሠራተኞች ድልድል እስከ ታኅሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለማጠናቀቅ በጊዜያዊነት ዕቅድ ተይዟል።

ይህ መረጃ #ባለቤትነቱ የቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ፈተናውን ብዙዎቹ ሊያልፉ ይችላል የሚል ግምት ነው የተያዘው " - የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ ከሚኖሩ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች መካከል #ተመሳሳይ የብሔር ማንነት ያላቸው አመራሮች ብዛት ከ40 በመቶ እንዳይበልጥ ሊያደርግ መሆኑ ተሰምቷል። በቅርቡ ለሚተገብረው #የሠራተኞች_ድልድል ሲባል…
#Update

" ፈተናው በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

ከ16 ሺህ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ሠራተኞች ነገ አርብ ታኅሣሥ 12/2016 ዓ.ም. ለፈተና ይቀመጣሉ።

ይህን በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ከ11ዱ ክፍል ከተማ ከተውጣጡ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ከተመረጡ 16 ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ኦረንቴሽን እና ውይይት አካሂዷል።

በዚህ ወቅት ምን ተባለ ?

- በቅርቡ በሚተገብረው የሠራተኞች ድልድል መነሻ ከ16 ሺህ በላይ የከተማ አስተደደሩ ሠራተኞች ነገ አርብ ፈተና ይቀመጣሉ።

- ፈተናውም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና በከተማው በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ  ት/ቤቶች በቀን 12/2016 ዓ.ም ከቀኑ በ 7 ስዓት ጀምሮ እንደሚሰጥ ይሰጠል።

ተፈታኞች በፈተናው ወቅት ማሟላት የሚገባቸው እና የተከለከቱ ተግባራት ምንድናቸው ?

* በሰዓቱ በፈተናው ስፍራ መገኘት፤
* የግል መታወቂያ (ID CARD) መያዝ፤
* ምንም አይነት ፅሁፎችን እና ወረቀት፣ የእጅ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እንዲሁም መሰል ቁሳቁሶችን ይዞ ወደ ፈተና መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤
* በተሰጠው ሰዓት ፈተናውን አጠናቆ መውጣት ይገባል።

- በፈተናው ወቅትም ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት እንዳይኖር ቢሮው ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ እንዲሁም ከፀጥታ አካላት ጋር በጥምረት እየሰራ ነው።

- ለተፈታኞች በቂ የትራንስፖርት ስምሪት ስራ የከናወናል ተብሏል።

- ለፈተና በተለያየ ምክንያት መገኘት ያልቻለ ተፈታኝ ምክንያቱ ታይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ለፈተና የሚቀርብበት መንገድ ይመቻቻል ተብሏል።

- ፈተናውም በ3 የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ይሰጣል።

ተጨማሪ ፦

☑️ ፈተናው የባህሪ እና የቴክኒክ ምዘናዎችን የያዘ ነው። የሚሰጠው የቴክኒክ ምዘና ሠራተኞቹ ከሚሠሩት ሥራ ጋር ግንኙነት ያለው ነው። የባህሪው ፈተና ደግሞ አገልግሎት አሰጣጡን የሚፈታተኑ የባህሪ ችግሮች ስላሉ ያንን ክፍተት ለመሙላት አመላካች እንዲሆን ተስቦ የተዘጋጀ ነው።

☑️ የምዘና ፈተናው የተዘጋጀው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በጋራ ትብብር ነው።

☑️ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርስቲ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው።

☑️ የከተማ አስተዳደሩ ባለሙያዎች ፈተናውን ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

☑️ ከዚህ የማለፊያ ውጤት በታች የሆነ ነጥብ ያገኘ ባለሙያ ከደረጃው ዝቅ ብሎ ባሉት የአስተዳደር እርከኖች ላይ ይመደባል።

☑️ ለዳይሬክተሮችና ለቡድን መሪዎች የፈተና ማለፊያ ነጥብ 60 በመቶ ነው። ይህን ነጥብ የማያመጡ አመራሮች ለዳይሬክተርነት / ለቡድን መሪነት ኃላፊነት #መወዳደር_አልችሉም

☑️ በመ/ቤት ካሉ የሥራ መደቦች መካከል በተመሳሳይ ማንነት / ብሔር የተያዙት ከ40 በመቶ እንዳይበልጡ ይደረጌ። ድልድሉን ሲያከናውኑ ይህንን #የብሔር ስብጥሩን ለመጠበቅ እንዲችሉ " ብቃት ያላቸውን ሠራተኞች ከሌሎች መ/ ቤቶች በመለየት በዝውውር እንዲሟሉ " ይደረጋል።

ከ40% መብለጥ የለበትም በሚል የተቀመጠው አሠራር፤ የሚተገበረው የቡድን መሪዎች እንዲሁም የዳይሬክተሮች ድልድል ላይ ብቻ ነው። በዚህ ድልድል ወደ #ሠራተኛው የወረደ እንደዚህ ዓይነት ነገር የለም። የድልድል ደንቡ ውስጥም የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ባለፈው ሳይሰጥ የቀረው የመንግሥት ሰራተኞች ፈተና ቅዳሜ ታህሳስ 20/04/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ይሰጣል ተባለ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባለፈው ለደረሰው መጉላላት እና እንግልት ሁሉ መላው ሰራተኞችን በይፋ ይቅርታ ጠይቋል። የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና፦ - ለአመራሮች ፣ - ለባለሙያዎች - ለሰራተኞች አርብ 12/04/2016…
#AddisAbaba

" ... አስተዳደሩ የብሔር ኮታ ምደባን አስመልክቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች በአፋጣኝ ግልጽ ማብራሪያ ይሰጥ " - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ሊሰጥ በዝግጅት ላይ ስላለው የመንግሥት ሰራተኞች የብቃት ምዘና ፈተና ጉዳይ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ፓርቲው ፤ በመርኅ ደረጃ ምዘናው ለማኅበረሰቡ የሚሰጡ አገልግሎቶች በተሻለ ብቃት እና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት በተላበሰ ሥነምግባር እንዲሠጡ ታላሚ ያደረገ ከሆነ ለአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት የሚረዳ መሆኑን ለሠራተኞች ደግሞ ሁልጊዜም ተወዳዳሪ የሚያደርግ አሠራር ስለሚሆን የሚበረታታ ተግባር እንደሆነ ገልጿል።

" በእነዚህ አስተዳደር መ/ቤቶች ፦
- የተገልጋይን ስም እንኳ በቅጡ በሠነዶች ላይ ማስፈር የማይችሉ፣
- ፈጣን አገልግሎት እንዲሠጡ ታስበው አገልግሎት ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም የማይችሉ፣
- ከሥነምግባር ያፈነገጡ እና በሌብነት የተተበተቡ ሠራተኞችን መመልከት የተለመደ ሆኗል " ያለው ኢዜማ ፤ " ሌላው ቀርቶ አንድ ዜጋ በነፃነት ለመንቀሣቀስ የሚያስፈልገውን የነዋሪነት መታወቂያ ለማግኘት እንኳ ሲጉላላ እና እጅ መንሻ ሲጠየቅ ይስተዋላል። " ብሏል።

ከዚህ አንጻር የአገልግሎት ጥራትን ለማስፈን የምዘና ጅምሩ የሚበረታታ መሆኑን አመልክቷል።

ነገር ግን እነዚህን አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚመሩት #የገዢው_ፓርቲ አመራሮችም ሆነ ገዢው ፓርቲ እንደተቋም #ለብሄርተኝነት ባላቸው የተዛባ ውግንና በተደጋጋሚ በሚያደርጓቸው አግላይ የአደባባይ ንግግሮች እና አሠራሮች ምክንያት እያንዳንዱ በነዚህ አካላት የሚደረግ እንቅስቃሴና ውሳኔ በማኅበረሰቡ በጥርጣሬ የሚታይ እንዲሆን አድርጎታል ብሏል።

በመሆኑም አስተዳደሩ " የብቃት ደረጃን ለማረጋገጥ እና አገልግሎትን ለማሻሻል የሚደረጉ እርምጃዎች ናቸው " ቢልም ከላይ በተጠቀሰው ምክንያት በጥርጣሬ እንዲታዩ መሆናቸውን መገንዘብና ተገቢውን ማብራሪያ በወቅቱ መስጠት ዜጎችን ከስጋትና ከውዥንብር ያድናል ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በአንድ መ/ቤት የሚገኙ ዳይሬክተሮች እና የቡድን መሪዎች ከአንድ ብሔር ከ 40 % በላይ ሊበልጡ እንደማይገባ መገለጹ አገልግሎት የሚሰጡ መሥሪያ ቤቶች ውሰጥ ለምዘና ሊቀመጥ የሚገባውን ዋነኛውና መሠረታዊ የሆነውን ከትምህርት ዝግጅት እና ከሥራ ልምድ የሚመነጩ የችሎታና የብቃት ጉዳይ አሳንሶ እንዳይመለከት ጥብቅ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ፓርቲው አሳስቧል።

ፓርቲው ፤ የከተማ መሥተዳደሩ ስለፈተናው እና ለማኅበረሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት ከመስጠት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም ስላለው #የብሔር ኮታ ምደባን አስመልክቶ ለነዋሪዎች በአፋጣኝ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ኢዜማ በኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለሚደረጉ ምደባዎች በምንም ዓይነት መንገድ የብሔር ማንነትን መሠረት ያደረገ መድልኦ የሚደረግባቸው እንዳይሆኑ፤ አሠራሩም ለሁሉም ዜጎች ግልፅና ችግር በሚፈጥሩ አመራሮች ላይ የማያወላዳ ተጠያቂነት ማስፈን የሚችል እንዲሆን ማድረግ ይገባል ብሏል።

(ፓርቲው የላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia