ቦይንግ❓
ዛሬ የተከሰከሰው #ቦይንግ_737_Max ከላይ በምስሉ ላይ የሚታየው አይነት አውሮፕላን ሲሆን አየር መንገዱ ካሉት በጣም #አዲስ አውሮፕላኖች አንዱ ነው። የዚህ አውሮፕላን አይነት ስሪት ጥቅምት ወር ላይ #ኢንዶኔዥያ ላይ ተከስክሶ 189 ሰዎች ሞተው ነበር።
Via Elias Mesert
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update በተከሰከሰው ቦይንግ 737 ማክስ 8 ምርመራ ለማገዝ እና መረጃ ለመለዋወጥ #ኢንዶኔዥያ ሁለት ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደምትልክ የአገሪቱ የበረራ ደኅንነት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ለሬውተርስ ተናግሯል።
የኤጀንሲው ኃላፊ ሱሪሐንቶ ቻሒሆኖ እንዳሉት ባለሙያዎቹ ወደ ኢትዮጵያ የሚያቀኑት በመጪው ሚያዝያ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው።
ቦይንግ 737 ማክስ 8 የተባሉት ተመሳሳይ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዥያ በአምስት ወራት ልዩነት ተከስክሰው በአጠቃላይ 346 ሰዎች አልቀዋል።
ሱሪሐንቶ ቻሒሆኖ "አደጋዎቹ ተመሳሳይ ስለመሆናቸው ወይም ከአደጋው አዲስ መረጃ እናገኝ እንደሆነ መረጃዎቹን እንመረምራለን" ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የትራንስፖርትር ሚኒስትር ዳግማዊት ሞገስ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የደረሰው አደጋ በኢንዶኔዥያ ከተከሰተው ጋር የሚያመሳስለው ነገር መኖሩን ገልጸው ነበር።
በሁለቱ አደጋዎች የተደረጉ ምርመራዎች የቦይንግ 737 ማክስ 8 አብራሪዎች አፍንጫውን እየደፈቀ ያስቸገራቸውን አውሮፕላን ለመቆጣጠር ተደጋጋሚ ጥረት ማድረጋቸውን አሳይተዋል።
ትናንት የኢትዮጵያ አደጋ ምርመራ ቢሮ ይፋ ያደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ቢሾፍቱ አቅራቢያ የተከሰከሰው አውሮፕላን ከአብራሪዎቹ ትዕዛዝ ውጪ (automatically) አራት ጊዜ ወደ መሬት አፍንጫውን መድፈቁን ገልጿል። አብራሪዎቹ ቦይንግ ባስቀመጠው ቅደም ተከተል መሰረት በተደጋጋሚ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ጥረት ማድረጋቸውን እንደደረሱበት መርማሪዎቹ አሳውቀዋል። አብራሪዎቹ ስለ አውሮፕላኑ የአየር ፍጥነት እና ስለሚገኝበት ከፍታ የሚያገኙት መረጃም የተጣረሰ እንደነበር ምርመራው ይፋ አድርጓል። በምርመራው መሠረት አብራሪዎቹ በጥምረት የተደፈቀውን አውሮፕላን ለማቃናት ያደረጉት ጥረት አልሰመረም።
የቦይንግ ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ሞለንበርግ በኢትዮጵያ እና በኢንዶኜዥያ ለደረሱት አደጋዎች ኤምካስ (Maneuvering Characteristics Augmentation System) የተባለው የበረራ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር ሚና እንደነበረው ተናግረዋል። ቦይንግ ሶፍትዌሩ እስካሁን በባለሙያዎች ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሁለተኛ ዕክል እንዳለበት ደርሼበታለሁ ብሏል።
Via Eshete Bekele