TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ወላይታ ሶዶ⬇️

በወላይታ ሶዶ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ችግር  ንብረት ለወደመባቸውና #ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች በክልሉ መንግስት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ #ድጋፍ ተደረገ፡፡

የደቡብ ክልል መንግስት ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ተጎጂዎችም ድጋፉ ተስፋ ከመቁረጥ እንዳዳናቸው ተናግረዋል፡፡

የሶዶ ከተማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ #ባታላ_ባራና ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር የንብረት ጉዳት መድረሱን አስታወሰዋል፡፡

ከተጎጂዎች መካከል አብዛኞቹ በተለያዩ የንግድ ሥራዎች የተሰማሩ ሲሆን በንግድ ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤቶችና በተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም አመልክተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራት የማጣራትና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ መሰራቱን ገልጸው በተገኘው መረጃ መሰረት ለ89 ተጎጂ ግለሰቦች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ተጎጂዎቹ ራሳቸው ባቀረቡትና ከአካባቢው ህብረተሰብ በተሰበሰበ መረጃ እንዲሁም በንግድ ፈቃዳቸው ላይ ያስመዘገቡት ካፒታልና የገቢ ግብር ማህደርን መነሻ በማድረግ የማጣራት ሥራው መከናወኑንም አቶ ባታላ ገልጸዋል፡፡

በዚህ መሰረት የክልሉ መንግስት ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎ ከ11 ሚሊዮን 478 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቀዋል።

የሶዶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤና የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ታልጎሬ ታደሰ በበኩላቸው የተሰበሰበውን መረጃ መሰርት በማድረግ እንደጉዳታቸው መጠን ድጋፉ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

“እስከ 10 ሺህ ብር ጉዳት ያቀረቡ 34 ተጎጂዎች ገንዛባቸው ሙሉ በሙሉ እንዲተካላቸው የተደረገ ሲሆን ቀሪዎቹ 55ቱ የጉዳታቸውን 50 በመቶ እንዲያገኙ ተደርጓል” ብለዋል፡፡

ባለሁለት ጎማ የሞተር ብስክሌት ለተቃጠለባቸው ወገኖች ምትክ እንዲገዛ መወሰኑንና በመኖሪያ ቤታቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ደግሞ ጥገና ለማድረግ የሚያስችል ድጋፍ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው ተጎጂዎች መካከል ወይዘሮ ምህረት መሸሻ በከተማዋ ጤና ጣቢያ ሰፈር የህጻናት አልባሳትና ኮስሞቲክስ ይነግዱ እንደነበረና በዕለቱ በድንገት በተፈጠረው ችግር መዘረፋቸውን ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡት ወይዘሮ ምህረት ችግሩ ከደረሰ በኋላ ከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ቢቆዩም ድጋፉ ሥራቸውን ዳግም ለመጀመር የሚያስችልና ተስፋ ከመቁረጥ እንደታደጋቸው ገልጸዋል፡፡

በሶዶ ከተማ መሃል ከተማ በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ ኑሪ ባዲ በበኩላቸው ድንገት በተፈጠረው ችግር  በህገ-ወጦች ቢዘረፉም የመንግስት ድጋፍ ዳግም ወደስራቸው ለመመለስ እንዳገዛቸው ተናግረዋል፡፡

ችግሩ ሰላም የማይፈልጉና በሁከት ሰበብ ለዘረፋ የተዘጋጁ ነውጠኞች ያደረጉት መሆኑን ጠቁመው የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ ነዋሪውና የከተማው ጸጥታ ኃይል ያደረገው ርብርብ የማይረሳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2010 ዓ.ም በከተማዋ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች መንግስትና የከተማዋ አስተዳደር ከቃል ባለፈ ተጨባጭ ድጋፍ ባለማድረጋቸው ተቸግረናል ሲሉ ያቀረቡትን ቅሬታ ኢዜአ በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia