TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-EDU

#መምህራን

መምህራን እንዲሁም በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ የTIKVAH-EDU ቤተሰብ አባላት...

በጤና ዙሪያ መረጃዎችን የሚያቀርቡልን...

.ዶክተር/መምህር ነ. ኤርሚያስ

በፊልም ዙሪያ መረጃዎችን የሚያቀርብልን...

.ላመስግን አየሁዓለም(በአንድ ትልቅ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚሰራ)

በቴክኖሎጂ ዘርፍ መረጃዎችን የሚያቀብሉን...

.መምህርት ቤዛዊት አሰፋ
.መምህር ብርሀን ነጋ
.መምህር ኩሩቤል አበበ
.መምህር አዶናይ ሀይሌ

ከቋንቋ ጋር በተያያዘ መረጃዎችን የሚያቀርብልን...

.መምህር ሞሲሳ አሰግድ

በታሪክ ዙሪያ መረጃዎችን የሚያቀርቡልን...

.መምህር አውጋቸው አማረ
.መምህር ረድኤት በቀለ

በፖለቲካ ዘርፍ መረጃዎችን የሚያቀርብልን...

.መምህር አኪያ

በሳይኮሎጂ እና አንትሮፖሎጂ ዙሪያ...

.መምህር ፊሊሞን

በጋዜጠኝነት ዙሪያ መረጃዎችን የሚያቀርብልን...

.ጋዜጠኛ ሙልጌታ አንበርብር

ሌሎች ዘርፎች ላይ በቀጣይ ይሰራል።
@tsegabwolde @tikvahethedu
የመምህራን ውይይት ቀጥሏል...

"ASTU (የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ) #መምህራን በአሁን ሰዓት ከፌደራል ከመጡ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ጋር #እየተወያየን እንገኛለን። ቢዩ ታገሰ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከግማሽ በላዩ ምዘናውን አላለፉም...

በአገር አቀፍ ደረጃ ለሙያ ብቃት ምዘና ከተቀመጡ የ2ኛ ደረጃ #መምህራን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ምዘናውን አላለፉም ተባለ፡፡

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መልካም ተግባር!

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ #መምህራን በበጎ ፈቃድ ተነሳስተው የአንድ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥገናና እድሳት አከናወኑ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የምህንድስና ዲፓርትመንት መምህራን የከተማው ወጣቶችን በማሳተፍ ባደረጉት ጥረት ለሠላም በር መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ቀለም ቅብና እድሳት አድርገዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው በጎ አድራጎት ሥራው አስተባባሪ  መምህር ዮሐንስ ፈይሳ እንደገለጹት በትምህርት ቤቱ የተከናወነው ሥራ 80 ሺህ ብር ይገመታል፡፡

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ...

"በወቅታዊው ሁኔታ በከተማችን እየተፈጠሩ ባሉ ሁኔታዎች ትምህርት ቤቶች ላያ ያለውን ተፅዕኖ አስመልክቶ የቀበሌ አስተዳደር እንዲሁም እኛ #መምህራን #ከወላጆች ጋር እየተወያየን እንገኛለን። ትናንትናም የቀበሌው አስተዳደር ከመምህራን ጋር ተወያይተዋል። ይህ እየተደረገ ያለው በሁለም የ02 ቀብሌ አካባቢ ባሉ ትምህርት ቤቶች ነው።" መምህር S - ድሬዳዋ ቲክቫህ ቤተሰብ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

መላው የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ትላንት በደረሰው አሰቃቂ የመኪና አደጋ ከባድ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ዶ/ር አህመድ ከሊል ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

አደጋው ትላንት 1 ሰዓት ከ20 ላይ በዶዶላ ማዕከል ለማስተማር መምህራንን ይዞ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ " ሰብስቤ ዋሻ " የሚባል አካባቢ ገደል ውስጥ ገብቶ መድረሱን ያብራራቱ ፕሬዜዳንቱ " አደጋው እጅግ በጣም አሰቃቂ ነበር " ብለዋል።

አደጋው እንዴት ሊደርስ ቻለ በሚለው ጉዳይ ላይ ከቴሌቪዥን ጣቢያው የተጠየቁት ዶ/ር ኢብራሂም " መኪናው ገደል ውስጥ የገባበት ቦታ በተደጋጋሚ መሰል አደጋዎች የሚደርሱበት ቦታ ነው ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ከአደጋው የተረፉና ህክምና ላይ ያሉ መምህራኖቻችን ናቸው እንዴት የተፈጠረ የሚለውን መረጃውን መስጠት የሚችሉት " ብለዋል።

" በአካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች ግን መኪናው አደገኛ ኩርባ አለች እሱን ጨርሶ እንደወረደ ቀጥታ እንደገባ ነው የነገሩን " ሲሉ አክለዋል።

በአደጋው እስካሁን የ20 መምህራን ህይወት ማለፉን የገለፁት ዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት በአስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ መኖራቸውን ተናግረዋል።

ከጉዳት የተረፉ በዶዶላ፣ ሻሸመኔ፣ ሀዋሳ ሆስፒታሎች ህክምና ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተዋል። በህክምና ላይ ካሉት ቀላል ጉዳት እንዲሁም ከባድ ጉዳት የደረደባቸው ያሉ ሲሆን ተቋሙ እነሱን እየተከታተለ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ህይወታቸው ያለፈውን ወደ ጎባ ሆስፒታል የመመለስ ስራ መሰራቱን ጠቁመው " በብዛት የባሌ አካባቢ ተወላጆች ስለሆኑ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች ተሟልተው ቤተሰቦቻቸው ወስደወል፤ ራቅ ራው ካሉ አካባቢዎች የመጡ መምህራኖቻችንን ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሽኝት እንዳረጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ተቋሙ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰራጨው የሀዘን መግለጫ ለማስተማር ወደ ዶዶላ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ 19 የዩኒቨርስቲው #መምህራን#ሠራተኞች እና #ተማሪዎች ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል።

28 የሚሆኑ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በተለያዩ ሆስፒታሎች በህክምና ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ዩኒቨርሲቲው አደጋው ከደረሰበት ሰዓት ጀምሮ አብረውት ለነበሩት የምዕራብ አርሲና የባሌ ዞኖች፣ የሻሸመኔ፣ አዳባ፣ ዶዶላና ሮቤ ከተሞች ነዋሪዎችና አመራሮች ዩኒቨርስቲው አመራርና ሠራተኞች በተለይ አደጋው የተፈጠረበት አከባቢ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#መምህራን #ትግራይ

" ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " ሲሉ የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።

መምህራኑ " መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን " ያሉዋቸው እንዲመለሱላቸው ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። 

መነሻቸው ሽረ ስታድዮም በማድረግ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዞር ድምፃቸው ያሰሙ መምህራኑ ፤ ያጋጠማቸው ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ጊዜ አይሰጥም ብለዋል። 

" ጥያቄያችን የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ ነው " ያሉት መምህራኑ የ2014 እና የ2015 ዓ.ም የደመወዝና የጋዎን ልብስ ክፍያ #እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። 

በተጨማሪ፦
- የስራ ግብር እንዲቀነስላቸው
- የደመወዝ እድገት እርከን እንዲሻሻልላቸው
- የቤት ኪራይ ክፍያ እንዲፈቀድላቸው የጠየቁት መምህራኑ ለደረሰባቸው ችግር #የሞራል_ካሳ እንዲሰጣቸው ጭምር በመፈክሮቻቸው ድምፃቸው አሰምተዋል። 

መምህራኑ በሰልፋቸው ያሳለፉት ከባድ የጦርነት ወቅት ፤ የተከሰተው የኑሮ ወድነትን የዋጋ ንረት ታሳቢ በማድረግ ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ የወሰዱት የብድር ወለድ #እንዲሰረዝላቸው ጨምረው ጠይቀዋል።

የእንዳስላሰ ሽረ ከአዲስ አበባ በ1100 ፤ ከመቐለ በ300 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ የትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ዋና ከተማ መሆንዋ የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በመጥቀስ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                   
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን #ትግራይ " ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " ሲሉ የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ። መምህራኑ " መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን " ያሉዋቸው እንዲመለሱላቸው ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።  መነሻቸው ሽረ ስታድዮም በማድረግ በከተማዋ…
#ትግራይ #መቐለ #መምህራን

" ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበል የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " - መምህራን

በመቐለ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን ፤ " 17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል።

ተማሪ ሄመን ሰለሙን በመቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የሓየሎም መለስተኛ ትምህርት የ8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆን ፤ ታህሳስ 13 /2016 ዓ.ም በትምህርት ቤትዋ የወላጆች በዓል ከተከበረ በኃላ ከትምህርት መአድ መስተጓጎሏን ተናግራለች።

ምክንያቱ ደግሞ የትምህርት ቤትዋ መምህራን " 17 ወራት ዉዙፍ ደመወዛችን ካልተከፈለን አናስተምርም " ብለው የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው ነው።

የተማሪ ሄመን ሰለሙን አስተያየት በመቐለ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚማሩ በ10 ሺዎች  የሚቆጠሩ ተማሪዎች ይጋሩታል።

ተማሪዎቹ ትምህርት ካቆሙ ቀናት ተቆጠረዋል።

እንደ ተማሪ ሄመን የመሰሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ፤ በከተማው በግል ትምህርት ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ጠዋት ተንስተው ወደ እውቀት ገበያ ሲያመሩ በማየት አዝነው ሲበሳጩ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባል ታዝቧል።

የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ መምህራም ፤ " ባዶ ሆዳችሁን ስሩ የሚል መጨረሻ የሌለውና ለመቀበሉ የሚከብድ ስለሆነብን ነው ስራ ያቆምነው " ብለዋል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለመቐለ ኤፍ ኤም ቃሉን የሰጠው የመቐለ ከተማ አስተዳደር ፤ " መምህራኑ ጥያቄያቸው ሳይሆን ፤ ለጥያቄያቸው መፍትሄ ብለው የወሰዱት እርምጃ ጎጂ ነው " ብሎታል።

የተማሪ ወላጆች በበኩላቸው ፤ " መምህራኑ ጥያቄ ማንሳታቸው እንደ ችግር የሚቆጥር ባይሆንም ፤ የነገ አገር ተረካቢ የሆኑ ህፃናት ተማሪዎች በመቅጣት ጥያቄያቸው ለመፍታት መፈለጋቸው ግን የከፋ የስህተት መንገድ ነው " ብለዋል።

ምሁራን ፤ " መምህራኑ ስለ ደመወዛቸው መጠይቅ ብቻ ሳይሆን የህፃናት ተማሪ ልጆቻቸው ቀጣይ አድልም ከግምት ማስገባት ነበረባቸው " ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

በመቐለ ከተማ በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምህሩ መምህራን ስለወሰዱት ስራ የማቆም እርምጃ የክልሉ ትምህርት ቢሮ መግለጫ አሰጣለሁ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ተከታትሎ ያቀርባል። 

ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም ፤ " ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " በማለት  የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን  በሰላማዊ ሰልፍ መጠየቃቸው መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው ከመቐለ ኤፍ ኤም ሬድዮ እና ከመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።
                                   
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update  ባጋጠመው የበጀት እጥረት ውዙፍ የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አስታውቋል። ከፌደራል መንግስት ያልተላከ በጀት ጨምሮ የ300 ሚሊዮን ብር የበጀት ጉድለት አለበኝ ብሏል የጊዚያዊ አስተዳደሩ በፋይናንስና ሃፍት አሰባሰብ አስተዳደር ቢሮ በኩል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ።  የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ምሕረት በየነ እንዳሉት ፤ የተላከው በጀት ከ4 ዓመት…
#መምህራን

" የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን እንዲከፍለን እንጠይቃለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የመምህራንን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፍል ጠየቀ።

ማህበሩ ይህን ያለው ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ ነው።

ማህበሩ ፤ " የመምህራን መብትና ጥቅማ ጥቅም ሲከበር የትምህርት ጥራት ይረጋገጣል " በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፤ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም በውቕሮ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይ የምክክር መድረክ ከመምህራን የደመወዝ ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ውዝግብ የሚፈታበት አቅጣጫ አስቀምጧል።

ከመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ የደመወዝ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ባለፉት ቀናት የ33 የመንግስት ትምህርት ቤቶች መምህራን ስራ ሲያቆሙ ፤ የተቀሩ ስራ ለማቆም ፊርማ የማሰባሰብ ስራ በማካሄድ ላይ መሆናቸው መግለጫው ገልፆ ፤ ችግሩ ይፈታሉ ያላቸው 8 ነጥቦች ዘርዝሯል ፦

1. የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት የተላከው የ2015 ዓ.ም ውዙፍ የ5 ወር ደመወዝ " በቅርብ ቀን እከፍላለሁ " እያለ እስከ አሁን አለመክፈሉ መምህራንን ችግር ላይ ስለጣለ አስተዳደሩ ይህንን ችግር በመረዳት ውዙፍ ደመወዙ እንዲከፍል ወይም ቁርጥ ቀን እንዲያስቀምጥ፤

2. የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሚመራውን መምህርና ትምህርት በቅጡ በመረዳት የመምህራን ጥያቄ እንዲመልስ፤

3. የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፌደራል መንግስት በመወያየት የ2014 ዓ.ም የ12 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዲከፍል፤

4. በመቐለ በአንድ ክፍለ ከተማ የተጀመረው የመኪና የሰርቪስ አገልግሎት በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንዲጀመር የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት አቅጣጫ እንዲሰጡ፤

5. ታህሳስ 16/2016 ዓ.ም በክልሉ የፋይናንስ ፣ የሃብት ማሰባሰብ አስተዳደርና የትምህርት ቢሮዎች የተሰጠው መግለጫ ጊዜው ያልጠበቀና ውዝግቡ ከመፈጠሩ በፊት መሰጠት የነበረበት ነው፤

6. መምህራን ለቤት መስሪያ ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ ሌሎች ባንኮች ከወሰዱት ብድር ከ2013 እስከ 2015 ዓ.ም ያለው ደመወዝ ያልነበረበት መሆኑ እየታወቀ ክፈሉ መባሉ አግባብ ስላልሆነ የመምህራንን ችግር ከግምት በማስገባት ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከሚመለከታቸው አበዳሪ ተቋማት በመወያየት የብድር ወለድ #እንዲሰረዝ

7. ከ1 እስከ 6 የተዘረዘሩ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ ባጠረ ጊዜ መልስ ካልተሰጠ እስከ ጥር 15/2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት በክልል ደረጃ ሰላማዊ ሰልፍ ይካሄዳል።

8. የመምህራን ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ፤ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለትውልድ ሲባል ከታህሳስ 18/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቀጥል መምህራን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማህበሩ ውሳኔ አሳልፏል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia            
#ደመወዝ

" ላለፉት ወራት በደሞዝ መዘግየትና መቆራረጥ ስንፈተን ቆይተናል " ያሉ የዎላይታ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች " ስራችንን በአግባቡ ለመስራት እንችል ዘንድ መንግሥት በአግባቡ ደሞዝ ሊከፍለን ይገባል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸው ከሰጡት የመንግስት ሰራተኞች ውስጥ በተለይም #መምህራን እና #የህክምና_ባለሙያዎች ይገኙበታል።

" ጉዳዩን በተዋረድ ለሴክተር መስሪያ ቤቶች እና ለወረዳ አመራሮች ካሳወቅን ቆየን " የሚሉት እነዚህ ሰራተኞች " ማክሰኞ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም ወደ ክልሉ መንግስት መቀመጫ ወደሆነችዉ ወላይታ ሶዶ ከተማ ብናቀናም ሰሚ አላገኘንም " ብለዋል።

በተለይ ይህ የደሞዝ አለመክፈል እና መቆራረጥ ችግር የተከሰተባቸው በዎላይታ ዞን ስር የሚገኙት የኪንዶ ኮይሻ ፣ የሆብቻ ፣ አባላ ፣ አባያ፣ ዳሞት ሶሬ፣ ዳሞት ፑላሳ ፣ ዳሞት ወይዴ ፣ ኪንዶ ዲዳዬ እና አካባቢዉ ወረዳና ቀበሊያት እንደሆኑ ተገልጿል።

በሆብቻ ወረዳ የሚገኘው የሆብቻ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስራ ካቆመ መሰነባበቱንና ተማሪዎች ቤታቸዉ እየዋሉ መሆኑን ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ መምህራን " መንግስት በአፋጣኝ እርምጃ ወስዶ ወደስራችን ይመልሰን " ብለዋል።

ከዚህዉ ጋር ተያይዞ የከልሉን መንግስት ሀሳብ በተመለከተ ጥያቄ ያቀረብንላቸዉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሮ አዜብ ስለጉዳዩ መረጃ እንደሌላቸዉ በመግለጽ ዝርዝር ሀሳብ ከመሰንዘር ተቆጥበዋል።

ይህን ጉዳይ እየተከታተልን እናሳውቃችኃለን።

መረጃዉን አዘጋጅቶ የላከዉ የሀዋሳው ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
 #Update " ለፍትሃዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ መሰጠት አለበት ፤ መንግስት የገባው ቃል ካልተገበረ ማህበሩ መብቱን ለማስከበር ይንቀሳቀሳል " - የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ መምህራን ማህበር የተገባለት ቃል እንዲተገበር ጠየቀ። ማህበሩ ባወጣው መግለጫ፤ መምህሩ የተማሪው የትምህርት ጥማት ለማርካት እየሰራ ቢገኝም ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በኑሮ ውድነት ከፉኛ እየተጎዳ ይገኛል ብሏል።…
 #ትግራይ #መምህራን

" ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ ካላገኘ ወደ ቀጣይ እርምጃ እንገባለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጥያቄያችን ፍትሃዊ መልስ ካላገኘ በምክር ቤት አስወስነን ለቀጣይ ትግል እንዘጋጃለን " አለ።

የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የ5 ወራት ውዙፍ ደመወዝ ለመክፈል የገባው ቃል እስከ አሁን አልተገበረም ብለዋል። 

መምህራን ውዙፍ ደመወዝ ባለመከፈላቸው ምክንያት ለከባድ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠዋል ሲል አሳውቋል።

ማህበሩ ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የትግራይ መምህራን ካለቸው ያልተከፈለ የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ መካከል የ5 ወራት እንደሚከፈል በወርሃ ጥር መግባባት ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል።

ነገር ግን እስከ አሁን አለመተግበሩ እንዳሳዘነው ገልጿል።

መምህራኑ ያላቸው 17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ አለመከፈላቸው እየታወቀ ፣ ከጦርነቱ በፊት ከደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ የወሰዱት ብድር ወለድ የወለድ ወለድና ቅጣት እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን የገለጸው ማህበሩ " ጉዳዩ መንግስታዊ መፍትሄ ያሻዋል " ብሏል።

" ፍትሃዊው ጥያቄያችን ፍትሃዊ የሆነ መላሽ እንዲያገኝ ተደጋጋሚ መግለጫ አውጥተናል ፤ ከሚመለከተው አካል ጋር ተወያይተናል ነገር ግን ምልስ የማያገኝ ከሆነ በማህበሩ ምክር ቤት በማስወሰን ለቀጣይ እርምጃ እንዘጋጃለን " ሲል ማህበሩ አስጠንቅቋል።

' ቀጣይ እርምጃው ምን እንደሆነ ' ግን በግልፅ አላብራራም።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
                        
@tikvahethiopia            
#መምህራን

" ለልማት በሚል ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው " - መምህራን

" እውነት ነው። ከህግ አግባብ ውጪ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " - የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር

የደመወዝ በወቅቱ አመከፈል፣ የጥቅማጥቅም ክፍያ አለማግኘት ችግር ባልተቀረፈበት ሁኔታ፣ ያለፈቃዳቸው ከደመወዝ ለልማት በሚል እየተቆረጠባቸው መሆኑን መምህራን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

መምህራኑ በሰጡት ቃል፣ " ለልማት በሚል እስከ 50 በመቶ ከደመወዛችን እየተቆረጠብን ነው። የወር አስቤዛን በቅጡ ከማይሸፍን ደመወዝ ላይ እየተቆረጠ እንዴት ቤተሰብ እናስተዳድር ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

ይህ የመንግስት ድርጊት ሰንበትበት እንዳለ ገልጸው፣ ጭራሽ ቤተሰብ ማስተዳደር አቅቷቸው በብድር እየማቀቁ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

መምህራኑ ያቀረቡት ቅሬታ እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበለት የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር፣ " እውነት ነው ችንሩን በደንብ ነው የምናውቀው "  ብሏል።

የማኀበሩ ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " በየክልሉ የተለያየ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ። ያለመምህራን ፈቃድ የደመወዝ  ቆረጣም በጣም #ትክክል ያልሆነ፣ #ጉልበተኝነት የበዛበት፣ #ሰሚ ያጣ ነው " ብለዋል።

ታዲያ ለቅሬታው ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " ትክክል አይደለም ብለን እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አድርሰናል። ባለፈው ነሐሴ ወር በነበረን ውይይት " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አሁንም በተለይ ዳውሮ ዞን የሚገኙ መምህራን እንደሚያለቅሱ፣ ማኀበሩም ለትምህርት ሚኒስቴር እንዳሳወቀ፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ያለፈቃዳቸው ደመወዝ እንዳይቆረጥ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ደብዳቤ እንደጻፈ፣ ክልሉም ደመወዛቸው እንዳይቆረጥ ለሚመለከተው አካል እንዳሳወቀ አስረድተዋል።

" ዞኑ ላይ 'ለማዕከል ግንባታ' በሚል ለዛ ነው ደመወዛቸው እየተቆረጠ ያለው። መምህራኑም እዚህ ድረስ መጡ። እኛም ለእንባ ጠባቂ ተቋም ደብዳቤ ጻፍን። የተለያዩ አካላትን ለመድረስ ጥረት አደረጉ። ግን እንባ ጠባቂም ምን ያህል ኃላፊነቱን እንደተወጣ አላውቅም " ነው ያሉት።

" በእኛ በኩል ያላረግነው ነገር የለም " ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፣ " ግን አሁን ህግ የሌለ በሚስል ሁኔታ የመምህራን ደመወዝ እየተቆረጠ ነው " ብለዋል።

መምህራኑ ደመወዛቸውን ቀድመው ለተለያዩ ፕሮግራሞች ከፋፍለው የሚጠቀሙበት ብቸኛ ገቢያቸው እንደሆነ ገልጸው፣ " መካከል ላይ ደመወዝ ሲቆረጥ ምስቅልቅል ይወጣል " ሲሉ አስረድተዋል።

" ይህንን የማያይ ምን አይነት የዞን አመራር እንዳለ አይገባኝም በበኩሌ። እጅግ በጣም ጫፍ የወጣ ስልጣን መጠቀም እንደሆነ ነው የምረዳው። መምህራን እየተሰቃዩ ነው የሚያዳምጣቸው አጥተዋል " ሲሉ አክለዋል።

ምን ያህል መምህራን ናቸው ደመወዝ የተቆረጠባቸው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ሽመልስ፣ " ለምሳሌ ዳውሮ ላይ የዞኑ መምህራን በሙሉ ተቆርጦባቸዋል። ኦሮሚያ ላይ የ230 ሺህ መምህር ይቆረጣል ደመወዙ " ነው ያሉት።

የሚቆረጠው መጠን በሁሉም ቦታ እንደየሁኔታው እንደሚለያይ አስረድተው፣ የክልል መንግስታት በማናለብኝነት ደመወዝ መቁረጥ አግባብነት እንደሌለው ቆም ብለው እንዲያስቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመምህራኑን ቅሬታ በተመለከተ ምን ሀሳብ እንዳለው በቀጣይ የመረጃ የምናደርሳችሀ ይሆናል።

#TikvahErhiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#መምህራን

" የአማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም ፤ መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ ነው ያስተማሩት " - ማኀበሩ

የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር / ኢመማ / በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ከባድ የሚባል ፈተና ለመጋፈጥ እየተገደዱ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ቃሉን ለቲክቫህ የሰጠው ማኀበሩ፣ መምህራኑ በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆነው እየሰሩ ባለበት እንኳ ደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው መሆኑን ገልጿል።

" የአማራ ክልል መምህራን የሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ወታደር፣ 'ፋኖ' እየሰፈሩ በዚያ ችግር ውስጥ ሆነው እንኳ መስዋዕትነት ከፍለዋል " ብሏል።

" አማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም " ያለው ማኀበሩ፣ ሚዲያዎች ግን ትኩረት እየሰጡት ባለመሆኑ ከአሁን ወዲያ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

በጣም ከአቅም በላይ በሆነባቸው አካባቢዎች ካልሆነ በስተቀር በጸጥታ ችግር ውስጥ የሚገኙት መምህራኑ ትምህርት እንዳይቋረጥ ጥረት ማድረጋቸውን አስረድቷል።

" ሱፐር ቫይዘር በሌለበት፣ የትምህርት መዋቅር እዚህ ግባ በሚባል ደረጃ በማይንቀሳቀስበት ሁኔታ አማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ኮሚትመንት ወስደው እየሰሩ ነው " ሲል አክሏል።

" የአማራ ክልል መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ፣ በላያቸው ላይ የጥይት ሀሩር እየተወረወረ ነው ያስተማሩ። ይሄ በደንብ መታወቅ አለበት " ነው ያለው።

" መምህራን በዚህ ኮሚትመንት ልክ እየሰሩ ደመወዛቸው እየተቆረጠ ነው " ሲልም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

" በአንድንድ ምክንያቶች ሁለት ወራት፣ ሦስት ወራት ደመወዝ የተቆረጠባቸው አሉ " ያለው ማኀበሩ፣ " ግን ያ ደግሞ ውዝፉ ጭምር እየተከፈለ ነው " ብሏል።

የ8ኛ ፣ 6ኛ፣ 12ኛ ክፍል ፈተና ያልወሰዱ ተማሪዎች በቀጣይ የሚወስዱበት መንገድ እንዲመቻችም አሳስቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#መምህራን " የአማራ ክልል ከማንም ጋር የሚወዳደር አይደለም ፤ መምህራን ጥይት በላያቸው ላይ እያፏጨ ነው ያስተማሩት " - ማኀበሩ የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር / ኢመማ / በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ከባድ የሚባል ፈተና ለመጋፈጥ እየተገደዱ መሆናቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ። ቃሉን ለቲክቫህ የሰጠው ማኀበሩ፣ መምህራኑ በከፋ የጸጥታ ችግር ውስጥ ሆነው እየሰሩ ባለበት እንኳ ደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው…
🔈#መምህራን

" ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም !! " - የኢትዮጵያ
መምህራን ማኅበር

በተለያየ ጊዜ በብሔራቸው አማካኝነትያ ከተለያዩ ክልሎች የተፈናቀሉ
መምህራን በሥራ አጥነት ሳቢያ የከፋ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር (ኢመማ) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለልጿል።

የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አበበ በሰጡት ቃል፣ " ትግራይ ክልል ዝግ ሆኖ የቆዬ አካባቢ ነው፡፡ ከዚያ አንጻር የተፈናቀሉ
መምህራን አሉ " ብለዋል፡፡

" የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሥራ ፈትተው የተቀመጡ
መምህራን አሉ። የትግራይ ክልል መምህራን ሆነው ከአማራ ክልል የተፈናቀሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ያሉም አሉ " ሲሉ ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

" ኮይሃ የሚባል አካባቢም የትግራይ ክልል ተወላጆች ሆነው ግን አፋር ክልል ይሰሩ የነበሩ ተፈናቅለው ሥራ ፈትተው የተቀመጡ
መምህራን አሉ " ሲሉ አክለዋል።

" በትግራይ ክልል ይሰሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጅ መምህራንም ቢሆኑ ተፈናቅለው ጎንደር የተቀመጡ አሉ " ያሉት አቶ ሽመልስ፣
መምህራን የትም አካባቢ ሂደው መስራት እንዳለባቸው ቢታመንም ችግሮች ግን ጎልተው እየተስተዋሉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም እንዲሁ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ለመውጣት የተገደዱ
መምህራን እንደነበሩ አስታውሰው፣ " ብሔሩ ተቆጥሮ ያልተፈናቀለ መምህር የለም " ብለዋል፡፡

" በተለያዩ ጊዜያት ችግራቸው እንዲፈታ፣ ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሳውቀናል" ሲሉ ማኅበሩ ያደረገውን ጥረት አስረድተዋል፡፡

" ለትግራይ ትምህርት ቢሮ አሳውቀናል፡፡ ትግራይ ክልልም የሰው ኃይል እጥረት አለና ቀጥራችሁ አሰሯቸው የሚል ሃሳብ ነው እያነሳን ያለነው " ብለዋል፡፡

መምህራን ያለምንም ፈቃዳቸው በተለያየ መንገድ ደመወዝ እንደሚቆረጥባቸው ፣ የደረጃ እድገት እየተሰራላቸው እንዳልሆነ ማኅበሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM