TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ለላፉት ሁለት አመታት ባጋጠማት ህመም በዱባይ ራሺዲያ ሆስፒታል በህክምና ላይ የቆየችው ሰርካለም ታመነ በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጽ/ቤትና በዱባይ የኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲ ማህበር ድጋፍና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ባደረገው ክትትልና ድጋፍ ትናንት ግንቦት 7 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ አገሯ ተመልሳለች፡፡ በራሺድ ሆስፒታል በህክምና ላይ የነበረችው ሶፊያት መሀመድ ሚያዚያ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ወደ አገሯ መመለሷ የሚታወስ ነው፡፡ ሶፊያ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድጋፍ በአቤት ሆስፒታል ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል ለ7 ሺህ 29 የህግ ታራሚዎች #ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ አስታወቁ፡፡ በክልሉ መንግስት ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በቆይታቸው መልካም ባህሪ ያሳዩ መሆናቸው ጉዳዩን የሚመለከተው ቦርድ እንዳረጋገጠ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ይቅርታው በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በዘር ጭፍጨፋ፣ በደን ጭፍጨፋ እና በሴቶችና ህፃናት ላይ ጥቃት የፈፀሙ አካላትን እንደማይመለከት ነው የተነገረው። ማህበረሰቡም ይቅርታ የተደረገላቸው ሰዎች ከማረሚያ ቤት ውጭ ያለውን ህይወት እስከሚላመዱ ድረስ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የህግ ታራሚዎችም ወደ ማህበረሰቡ ከተቀላቀሉ በኋላ በስራ ለመካስ መስራት እንደሚገባቸው ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት። ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎችም ከዛሬ ጀምሮም ህብረተሰቡን መቀላቀል ይጀምራሉ።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ከ600 በላይ ጥይት ከአንድ ክላሽንኮብ ጠብመንጃ ጋር በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር መያዙን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙላት እንደገለጹት መሳሪያው ከነጥይቱ ሊያዝ የቻለው የህብረተሰቡን ጥቆማ መሰረት በማድረግ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው፡፡

በእዚህም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-20584 በሆነ የህዝብ ማመላለሻ አይሱዝ መኪና ውስጥ አንድ ታጣፊ ክላሽ እንኮብ የጦር መሳሪያ፣ 613 የክላሽ እንዲሁም ዘጠኝ የመትረየስ መሳሪያ ጥይቶች ተይዘዋል።

በተጨማሪም ሰባት ህገ ወጥ የሞባይል ስልኮች በፍተሻው መያዛቸውን የገለጹት። ተሽከርካሪው የተያዘው ትናንት ከወረባቦ ወረዳ ተነስቶ ወደ ሐይቅ ከተማ ሊገባ ሲል ቀበሌ 02 ላይ ሲደርስ መሆኑንም ኮማንደር ጌታቸው አመልክተዋል፡፡

እንደእርሳቸው ገለጻ በወንጀሉ የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ በመጣራት ላይ ሲሆን ሁለቱ መምህር መሆናቸው ታውቋል።

ህብረተሰቡ #ለፖሊስ ላደረሰው #ጥቆማ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ኮማንደሩ በቀጣይም ህገ ወጥነትን በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እየተሰጠ ነው...

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተለያዩ የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ ነው። የፈተናውን ሂደት በጣምራ የሚመሩት የትምህርት ሚኒስቴር እና ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና የፈተናዎች ኤጀንሲ ለፈተናው አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

የኦሮሚያና ሶማሌ ክሎሎች የህዝብ ለህዝብ መድረክ ነገ በጅግጅጋ ከተማ ይካሔዳል፡፡ ነገ በሶማሌ ክልል ጂግጂጋ ከተማ የሚካሔደው የህዝብ ለህዝብ መድረክ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ግንኙነት የሚያጠናክር ተመሳሳይ መድረክ በአዳማ መካሔዱ የሚታወስ ነው።

Via #OBN
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢንትሮዳክሽን ቱ ገዳ!

ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ በ2012 የትምህርት ዘመን ስለ ገዳ ስርዓት የሚያስተምር ‘’ኢንትሮዳክሽን ቱ ገዳ ሲስተም ‘’ የተሰኘ አዲስ ትምህርት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጅግጅጋ

10ኛው የፌደራል ና የክልሎች ማረሚያ ቤቶች የውይይት መድረክ በጂግጂጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ ውይይቱም ‘’ሃጋራዊ የማረሚያ ተቋማት ሪፎርም ለውጤታማ የማረም፣ ማነፅና ተሀድሶ ልማት’’ በሚል መሪ ቃል ነው እየተካሔደ ያለው፡፡በመድረኩ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሙሰጠፌ መሀመድ ሁመርን ጨምሮ የክልሎችና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከUK መንግስት ሴክሩተሪ አሎክ ሻርማ ጋር ኢስተርን ኢንደስተሪ ዞን በመገኘት ዩኒሌቨር ኩባንያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱ በኃላ በዱክም ከተማ በጋራ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና በክልል ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቀዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012

ከመቶ ሀምሳ ዓመታት በሀኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ሊከበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የኢሬቻ በዓል እንደ ትልቅ እድል ሊታይ ይገባል እንጂ የስጋት ምንጭ መሆን እንደሌለበት የገዳ አባቶች አስገንዝበዋል፡፡

#OBN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወርቁ ተገኝቷል⬆️

“ዶሮው ከጆሮዬ ላይ በጥሶ የዋጠውን ወርቅ ቤት ገብቼ እንዳረድኩት አግኝቼዋለው” - ወይዘሮ ሃጫልቱ

የኢዜአ በትናንትናው ዕለት ይዞት በወጣው ልዩ ዘገባ ለሽያጭ ገበያ የወጣው ዶሮ 1 ነጥብ 75 ግራም የሚመዝን ወርቅ ከጆሮ ላይ በጥሶ እንደዋጠ ማስነበቡ ይታወሳል፡፡ " ከገበያ መልስ ቤት እንደደረስኩኝ ባለቤቴን ጠርቼ ዶሮውን ወዲያው እንዳረደው የጆሮ ጌጥ ወርቄን በዶሮው አንጀት ውስጥ አግኝቼዋለው " ስትልም የወርቋ ባለቤት ወይዘሮ ሃጫልቱ ለኦቢኤን ተናግራለች፡፡ ወርቁን ባለቤቷ ለሠርጋቸው ጥሎሽ እንደሰጣትም አክላላች ወይዘሮ ሃጫልቱ፡ የታረደውንም ዶሮ በመብላት እልሄን ተወጥቻለው ስትልም የወርቋ ባለቤት ተናግራለች፡፡

Via #OBN/ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012 የመልካ ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ መከበሪያ ቦታ ተለይቶ መወሰኑ ተገለፀ፡፡ #OBN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

በሆረ ፊንፊኔ የሚከበረው የእሬቻ በዓል በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻዉን ሊወጣ እንደሚገባ የቡኖ በደሌ አባገዳዎች ጥሪ አቀረቡ። የዞኑ አባገዳዎች ለኦቢኤን እንደተናገሩት የኦሮሞ ሕዝብ ከ150 አመታት በኃላ ለዚህ ድል የበቃዉ በፈጣሪ ዋቃ ፈቃድ ነዉ፤ በመሆኑም መላዉ የኦሮሞ ሕዝብ ለዚህ ድልና ለአዲሱ ዘመን ያደረሰዉን ፈጣሪዉን በፍቅር እና በአንድት ወጥቶ ሊያመሠግነዉ ይገባል ብለዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከ49 ኩንታል በሶና ከ3 ሺ 5 መቶ 35 ኪ.ግ ቅቤ የተሰራው 4 ሺህ ሜትር ጩኮ ለእይታ ቀርቧል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀዳ ሲቄዎች የሰላም ንቅናቄ መድረክ በአዳማ!

ሰላምን ለማስፈን ሀዳ ሲቄዎች ያላቸዉን አቅም እንዲጠቀሙ እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡ የሀዳ ሲቄዎች የሰላም ንቅናቄ መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነዉ፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሪፎርም...

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዘርፉ ያለውን የህግ የበላይነት ለማስጠበቅና ፍትሃዊ አገልግሎት ለህዝቡ ለማድረስ የሪፎርም ስራዎች ማከናወኑን አስታወቀ። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ከሚገኙ ከተለያዩ የፍትህ አካላት ጋር በሪፎርም ስራው ውይይት እያደረገ ይገኛል።

በአዳማ እየተካሄደ ባለው ውይይት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተሰሩ ስራዎችን ማሳወቅና በዘርፉ የሚገኙ ባለሙያዎች ምርጫን ታሳቢ በማድረግ ስራዎች እንዴት መከናወን አለባቸው በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል፡፡

#OBN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OBN_LIVE

ልዩ የኢሬቻ በዓል የሙዚቃ ኮንሰርት ከአዲስ አበባ በቀጥታ በኦሮሚያ ብሮድስካስቲንግ ኔትዎርክ - OBN TV በቀጥታ እየተላለፈ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት በቅርቡ ህመም አጋጥሞት የነበረው አንጋፋው የሀገራችን አርቲስት ክቡር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የሙዚቃ ስራውን በማቅረብ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OBN

የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ በአራት ተጨማሪ ቋንቋዎች ስርጭት ሊጀምር ነው።

OBN Horn Of Africa በቅርቡ በአፋርኛ ፣ በኑዌር ፣ በአኙዋክኛ እና በመጃንግ ቋንቋዎች ስርጭት ለመጀመር ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ተገለፀ።

OBN አሁን ላይ በ8 ቋንቋዎች በአፋን ኦሮሞ ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ ፣ ሓዲይኛ ፣ ሃላቢኛ ፣ ሶማልኛ ፣ ሱዋሂሊ ፣ አረቢኛ እና ኢንግልዝኛ ቋንቋዎች ዜናዎች እና ፕሮግራሞችን እያሰራጨ ይገኛል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
" አደጋው የደረሰው ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ በመገልበጡ ነው ፤ ... እስካሁን የ15 መምህራን ህይወት አልፏል  " - የሮቤ ከንቲባ

ዛሬ ማለዳ ላይ 15 የመደ ወላቡ ዩንቨርሲቲ  መምህራን በትራፊክ  አደጋ  ህይወታቸው  ማለፉ ተሰምቷል።

የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን  ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰው የትራፊክ አደጋ  ህይወታቸው ማለፉ የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ገልጸዋል።

ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት ጋራ ዋሻ አካባቢ በመገልበጡ ፤ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን  ህይወት ማለፉን አመልክተዋል።

#OBN

@tikvahethiopia
በሻሸመኔ በደረሰ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰው ህይወት አለፈ።

የቦንብ ፍንዳታው የደረሰው በአላቼ ክ/ከተማ ሲሆን በቆሻሻው መጣያ አካባቢ የፕላስቲክን ጠርሙስ ሲሰበስቡ የነበሩ ሁለት የ9 ዓመት እድሜ ያላቸው ልጆች ህይወታቸው አልፏል።

የቦንብ ፍንዳታው የደረሰው ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ በሚወስደው መንገድ ሲሆን ቦንቡ በአንድ ቆሻሻ ስር ተጥሎ ነበር።

#OBN

@tikvahethiopia