TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም !! " " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም ! " ያለው የእግር ኳስ ተጫዋች ግብረሰዶማውያን ለመደገፍ ሲባል ክንድ ላይ የሚጠለቀውን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል። በዓለም ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ ፍልሚያ አፍቃሪያን እንዳሉ ይታወቃል። ከየትኛውም ሀገራት በላይ ደግሞ የአውሮፓ ሀገራት ውስጥ የሚካሄዱት ፍልሚያዎች እጅግ ብዙ ተመልካች ያላቸውና ከፍተኛ ተወዳጅነትን ከፉክክር ጋር…
" እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ !! "

በሀገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ በመላው ዓለም ላይ በቢሊዮኖች ተመልካች ያለው የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ በሚል በየአመቱ ዘመቻ ያደርጋል።

ይህንን ዘመቻ የሚያደርገውም በእያንዳንዱ ክለብ አምበል ክንዶች ላይ ግብረሰዶማውያንን የሚገልጸውን ባዲራ / እንዲያደርጉ በማድረግ ነው።

ይህን የሊጉን ተግባር እጅግ በርካታ ሃይማኖተኛ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች ነው የሚያወግዙት።

በዘንድሮው ዓመት የሊጉ ፍልሚያ ኢፒስዊች ታውን የተባለው ክለብ አምበል እና የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲ " እኔ ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ቀርቷል።

ከዚህ ባለፈ ግን አንድ የሌላ ክለብ ተጫዋችና አምበል የክርስትና እምነት ተከታይ ክንዱ ላይ ምልክቱን ቢያደርግም ከላይ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ !! " የሚል ፅሁፍ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳደሮች እንዳስቆጣ በዚህም ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ተሰምቷል።

ተጫዋቹ ማርክ ጉሂ ይባላል ፤ እድሜው 24 ሲሆን የአይቮሪኮስት ዝርያ ያለበት የእንግሊዝ ዜጋ ነው።

የሚጫወትለት ክለብ ክርስታል ፓላስ የሚባል ነው።

ይኸው ተጫዋች ነው ባለፈው ቅዳሜ ኒውካስትል ከተባለው ሌላኛው የሊጉ ክለብ ጋር ጨዋታቸውን ሲያደርጉ ግብረሰዶማውያንን የሚደግፈውን ምልክት ክንዱ ላይ ቢያጠልቅም ከላዩ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስን እወደዋለሁ ! " የሚል ፅሁፍ ፅፎበት በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

በዚህም የሊጉን አስታዳዳሪዎች አስቆጥቶ ቅጣት ሊጥሉበት እንደሆነ ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ግብረሰዶማውያንን ለመደገፍ በየዓመቱ አምበሎች የግብረሰዶማውያን ምልክት የሆነውን የተለያየ ቀለም ያለው ምልክት በክንዳቸው አጥልቀው እንዲጫወቱ ያደርጋል።

#Guehi #Christian #PremierLeague

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " - ማርክ ጉዬ

➡️ የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሞርሲም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ሳያደርግ ወደ ሜዳ ገብቶ ጨዋታውን አድርጓል !

ማርክ ጉዬ የተባለው እግር ኳስ ተጫዋች በድጋሚ ክንድ ላይ በሚጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " የሚል ፅሁፍ በመፃፍ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ክሪስታል ፓላስ ለተባለው ክለብ የሚጫወተውና የቡድኑ አምበል የሆነው ጉዬ ከቀናት በፊት ኒውካስል ዩናይትድ ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባጠለቀው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ " ኢየሱስን እወደዋለሁ " ብሎ ፅፎ በመግባቱ የሊጉን አስተዳዳሪዎች አስቆጥቶ ነበር።

ይኸው ተጫዋች ትላንት ምሽት ቡድኑ ኢፒስዊች ታውን ከተባለው ቡድን ጋር ሲጫወት ክንዱ ላይ ባለው የግብረሰዶማውያን ምልክት ላይ በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ብሎ በመፃፍ በመግባት ጨዋታውን አድርጓል።

ባለፈው ቅዳሜ ከፃፈው " ኢየሱስን እወደዋለሁ ! " ከሚለው ፅሁፍ በኃላ ፉትቦል አሶሲዬሽን የተባለው የሊጉ አስተዳዳሪ " ኃይማኖታዊ ምልክቶች የእግር ኳስ ማሊያ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ላይ መፃፍ ክልክል ነው " ሲል ለክለቡ እና ለአምበሉ ማስጠንቀቂያ ቢልክም ማስጠንቀቂያው ወዲያ በሉት ብሎ ትላንት ምሽት በድጋሚ " ኢየሱስ ይወዳችኋል ! " ሲል በመፃፍ ገብቶ ተጫውቷል።

የሊጉ አስተዳዳሪ ቅጣት ሊጥልበት ይችላል እየተባለ ነው።

በሌላ በኩል የእስልምና እምነት ተከታይ የሆነው ሳም ሞርሲ የተባለው የኢፒስዊች ታውን ተጫዋች ትላንትም የግብረሰዶማውያንን ምልክት ያለበትን የአምበልነት መለያ ሳያደርግ ነው የገባው።

ተጫዋቹ " ሃይማኖቴ አይፈቅድልኝም " በማለት ባለፈው ቅዳሜም ይህንን የግብረሰዶሞች ምልክት ሳያደርግ መግባቱ የሚዘነጋ አይደለም።

' እኩልነት እና ብዝሃነት ' በሚል ሰብሰብ በዓለም ላይ የግብረሰዶማውያንን እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ እና ሰዎች ጋር ለማድረስ የግብረሰዶማውያን ደጋፊዎች ብዙ አይነት መንገድ ይከተላሉ።

አንዱ ግብረሰዶማውያንን ለማስተዋወቅ የሚጠቀሙት በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ በተለይም ወጣት ተመልካቾች ያሉትን የእግር ኳስ ፍልሚያ ነው።

ከነዚህ የእግር ኳስ ፍልሚያዎች አንዱ ደግሞ በኢትዮጵያ / አፍሪካ ሆነ በዓለም ላይ ብዙ ተመልካች ያለውን እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነው።

በዚሁ ሊግ የሊጉ አስተዳዳሪ አካላት በ ' እኩልነት እና ብዝሃነት ' ሰበብ የክለብ አምበሎች ክንዳቸው ላይ የግብረሰዶማውያንን ምልክት እንዲያጠልቁ አድርገው ለግብረሰዶማውያን ማስታወቂያ እንዲሰሩ ያደርጋሉ።

ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ የሊጉ ፍልሚያ በሚጋጋልበት ወቅት ነው።

ግብረሰዶማውያን እና የነሱ ደጋፊዎች እጅግ በጣም ተወዳጁን የእግር ኳስ ፍልሚያን ተጠቅመው ግብረሰዶምን የሚያስተዋውቁት በልጆች ፣ ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ዘንድ ድርጊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግና እነሱን ለማነሳሳት ነው።

#TikvahEthiopia
#Guehi #Christian  #PremierLeague
#SamMorsy #Muslim

@tikvahethiopia