TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19

ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ በ6 የመድሃኒት አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ በተደረገ የግላቭ፣ የማስክ እና የአልኮል ግብይት የዋጋ ቅኝት 1 የመድሃኒት አከፋፋይ 1 ሊትር አልኮል ላይ 10 ብር ጭማሪ ፤ 1 የመድሃኒት አከፋፋይ ደግሞ በግላቭ ላይ በካርቶን 53 ብር ያልተገባ ጭማሪ አድርገው ተገኝተዋል።

በ8482 በኩል በደረሰ ጥቆማ ደግሞ 1 መድሃኒት ቤት ላይ በተደረገ ድንገተኛ የዋጋ ማጣራት 5 ብር ይሸጥ የነበረውን ማስክ 50 ብር እየሸጠ መሆኑ በመረጋገጡ ተገቢው እርምጃ መወሰዱን የምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ የኮሮናን ቫይረስ [COVID-19] ለመከላከል እና ለማከም ማቆያ ተዘጋጅቷል። የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ግብረ ሃይል ተቋቁሟል::

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በድሬዳዋ አስተዳደር እስካሁን በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ሰው ባይኖርም ችግሩ ቢከሰት ሊያስከትል የሚችለውን ማህበራዊ ቀውስ ለመቀነስ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት በነምበር ዋን ጤና ጣቢያ ከተዘጋጀው ለይቶ ማቆያ በተጨማሪ የፈረንሣይ ሆስፒታልን ለዚሁ አገልግሎት ለማዋል ከሚመለከተው አካል ፍቃድ ማግኘት ተችሏል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በድሬዳዋ ከተማ በነገው እለት የፀረ- ተህዋስያን መድሀኒት ርጭት ይከናወናል። የፀረ-ተህዋስ መድሀኒት ርጭት የሚከናወንባቸው መንገዶች፦

- ከኮኔል ድልድይ - ክርስቶስ ት/ቤት - ኮተን ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ

- ከኮኔል ድልድይ - ታይዋን - አላይበዴ - ክርስቲያን መቃብር

- ከኮኔል ድልድይ - ደቻቱ - ቀፊራ - አምስተኛ

- ከድ/ዳ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት - ምድር ባቡር ክለብ - ሰዒዶ

ከላይ በተጠቀሱት የከተማው መንገዶች ላይ ከነገ መጋቢት 24/2012 ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ለ1 ቀን ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማይፈቀድ መሆኑ ተገልጿል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ባወጣው የ48 ሰዓት የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መግለጫ ከድሬዳዋ የተላከው 6 ሰዎች ናሙና ሁሉም ውጤታቸው ከቫይረሱ ነፃ መሆኑን አመልክቷል።

#DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Djibouti

የጅቡቲን የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት እጠበቅን ነው። በሰዓታት ውስጥ ይፋ ይደረጋል።

የጅቡቲ ጉዳይ ይህን ያህል የሚያስጨንቀን በእነዚህ ምክንያቶች ነው ፦

- በርካታ ዜጎቻችን ከጅቡቲ እየተመለሱ በመሆናቸው።

- የተሽከርካሪና የባቡር ትራንስፖርት ቢቁምም በተለያዩ መንገዶች በእግርም ጭምር ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ በመሆኑ።

- የጭነት ተሽከርካሪዎች አሁንም ወደጅቡቲ ይሰራሉ። ሹፌሮቻችን ደህንነታቸው ካልተጠበቀ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ስለሚሆኑብን።

ዛሬ የድ/ዳ/አስ/ጤ/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ባወጡት መግለጫቸው በተለይ በጅቡቲ በኩል ስጋት በመኖሩ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለህዝብ አሳውቀዋል፦

- በተሽከርካሪዎች ላይ የመድሃኒት ርጭት የማካሄድ ስራ እየተሰራ ነው።

- ለሹፌሮች የሙቀት ልኬት እየተደረገላቸው ይገኛል። ስልክ እና የመኖሪያ አድራሻቸው ተወስዶ ክትትል እየተደረገ ነው።

- በእግር የሚመጡ የጅቡቲ ተመላሾች በኬላዎች እንዲሰባሰቡ በማድረግ ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ እየተደረገ ነው (ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና ሃይስኩል)

#DrLemlem #TIKVAH #DMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia