TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" አሜሪካ ዩክሬንን ከመደገፏ በፊት የትምህርት ቤቶቿ ደኅንነት ላይ ታተኩር " - ትራምፕ

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ የትምህርት ቤቶችን ደኅንነት ለማረጋገጥ የምታወጣው የገንዘብ ድጋፍ ለዩክሬን ከሚቀርበው እርዳታ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

ይህ የትራምፕ ንግግር የተሰማው በቴክሳስ ግዛት በት/ቤት ውስጥ 19 ህጻናት 2 መምህራኖቻቸው በአንድ በታጠቀ ወጣት ከተገደሉ በኋላ ነው።

የጦር መሣሪያን በተመለከተ እየተካሄደ በሚገኝ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ትራምፕ፣ አሜሪካ ወደ ዩክሬን ቢሊዮን ዶላሮችን መላክ ከቻለች " በአገራችን ውስጥ ያሉ ልጆቻችንን ደኅንነት ለመጠበቅ እንዲውል የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን" ብለዋል።

" በአፍጋኒስታን እና ኢራቅ ትሪሊዮን ዶላሮችን ብናፈስም ጠብ ያለ ነገር ግን ያለም” ያሉት ትራምፕ " የተቀረውን ዓለም ከመገንባታችን በፊት በአገራችን ለልጆቻችን ደኅንነቱ የተጠበቀ ትምህርት ቤት ልንገነባ ይገባል” ሲሉ አክለዋል።

በዚህ ወር መግቢያ ላይ የአሜሪካ ም/ቤት ለዩክሬን ወታደራዊ እርዳታ የሚውል 40 ቢሊዮን ዶላር እንዲላክ ወሰኗል። ጦርነቱ ከተነሳ ጊዜ ጀምሮ 54 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን አጽድቋል።

ትራምፕ የጦር መሣሪያ ቁጥጥርን የተቃወሙ ሲሆን ሰላማዊ አሜሪካውያን ራሳቸውን "ከመጥፎ" ሰዎች እንዲከላከሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል።

በጦር መሳሪያ ላይ ቁጥጥር ከማድረግ ይልቅ በት/ቤቶች ከላይ እስከ ታች የሚዘረጋ የደኅንነት ሥርዓት ሊኖር ይገባል ብለዋል።

በት/ቤቶች መግቢያ ላይ ብረት ነክ ነገሮችን የሚለዩ መሣሪያዎችን ማስቀመጥ እና ቢያንስ 1 የታጠቀ ፖሊስ እንዲኖር ማድረግን ጨምሮ የተጠናከረ ጥበቃ ሊኖር ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ እንዳይሆን እንቅፋት የሆኑት ዲሞክራቶች ናቸው ሲሉ ከሰዋል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ካናዳ ፦ የካናዳው ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ አነስተኛ የእጅ ሽጉጥ መግዛትም ሆነ መታጠቅ እንዲከለከል ጠይቀዋል። የትሩዶ መንግሥት በጠቅላላው የእጅ ሽጉጥ መግዛት ሆነ ቤት ማስቀመጥ በሕግ እንዲያስቀጣ ረቂቅ እያወጣ ነው። ረቂቁ እንደሚለው ካናዳዊያን የእጅ ሽጉጦቻቸውን ባይነጠቁም ከዚህ በኋላ አዲስ መግዛት ግን አይችሉም። ትሩዶ ይህን ሐሳብ ያፈለቁት በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት አንድ አፍላ ታጣቂ 19 ሕፃናትን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ነው።

➡️ #እስራኤል #UAE ፦ እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የነፃ ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል ፤ ይህ እስራኤል ከአረብ ሀገር ጋር ያደረገችው የመጀመሪው ትልቅ ስምምነት ነው።

➡️ #ሴኔጋል ፦ የሴኔጋል ፖሊስ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰው እና የ11 ህጻናት ህይወት ከቀጠፈው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

➡️ #ሩስያ ፦ በያዝነው ዓመት 70ኛ ዓመታቸውን የሚደፍኑት የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጤና እክል ምናልባትም በካንሰር ህመም እየተሰቃዩ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ያልተረጋገጡ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታመዋል መባሉን ሀሰት ሲሉ አስተባበሉ። ላቭሮቭ ፕሬዚዳንት ፑቲን በየቀኑ በአደባባይ እንደሚታዩ እና እንደማኛውም ጤነኛ ሰው የህመም ምልክት አያታይባቸውም ብለዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ባይዶዋ ከተማ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች። ከተማዋ ፕሬዝዳንቱ ፈርማጆን አሸንፈው ዳግም የፕሬዜዳንትነት መንበሩን ከተረከቡ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኟት ከተማ ትሆናለች።

#ቢቢሲ #ቲአርቲ #ሲጂቲኤን #SNTV

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 📣

➡️ #ካሜሮን፦ በካሜሩን መገንጠልን አላማቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ መንደር በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱ ባሳለፍነው እሁድ በደ/ምዕራብ የካሜሩን ክፍል ኦቦኒ ሁለት በተሰኘ መንደር የተፈፀመ ሲሆን ከሞቱ ሰዎች ባሻገር ከ60 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹ በየወሩ ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ይፈልጋሉ፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ ፍቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ነው ጥቃት ያደረሱባቸው ተብሏል።

➡️ #ሜክሲኮ ፦ በደቡባዊ ሜክሲኮ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የገቡበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ተሰምቷል።

➡️ #ቻይና ፦ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከሁለት ወር በኃላ የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ ነፃ ሆነዋል። ነዋሪዎች ባለፉት 2 ወር ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በተጣለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል።

➡️ #ዩክሬን ፦ የየክሬን ኬርሰን ግዛት በሩስያ ቁጥጥር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተነግሯል።

➡️ #አሜሪካ ፦ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን 'ቁልፍ ኢላማዎችን' ለመምታት የሚያስችላትን እጅግ የዘመኑ ሮኬቶችን እንደምትልክ አሳውቀዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ ወደ ባይዶዋ እንደሚሄዱ የተነገረላቸው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት መሪ አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ እና ከባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዜዳንቱ ወደ ባይዶዋ ያደረጉት ጉዞ ዳግም ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያቸው ነው።

#ቲአርቲ #ቢቢሲ #ፍራንስ24 #ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#US በየጊዜው በርካቶች በታጣቁ ሰዎች በሚከፈት ተኩስ የሚገደሉባት ሀገረ አሜሪካ ትላንትም እጅግ በጣም ዘግናኝ የሚባል ጥቃት ተፈፅሞ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት ተገድለዋል። በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት አንድ የ18 ዓመት ወጣት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 2 አዋቂዎችን ጨምሮ 19 ሕጻናት መገደላቸውን ተዘግቧል። ድርጊቱ የተፈፀመው በደቡብ ቴክሳስ ግዛት፣ ዩቫልዲ ከተማ ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት…
#አሜሪካ

በአሜሪካ ኦክላሆማ ግዛት ቱልሳ በተሰኘች ከተማ ሆስፒታል ውስጥ በተከፈተ ተኩስ አራት ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ትኩስ እንደከፈተ የተጠረጠረው እና ጠመንጃ እና ሽጉጥ ታጥቆ የነበረው ግለሰብ መሞቱንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ፖሊስ ጥቃቱ በተሰነዘረበት ቅዱስ ፍራንሲስ ሆስፒታል በሦስት ደቂቃ የደረሰ ሲሆን በጥቃቱ የሚጎዱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ በስፍራው በአስቸኳይ መድረሱ ተገልጿል።

ትላንት ረቡዕ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በርካቶች መቁሰላቸውንም ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል።

የቱልሳ ከተማ ምክትል የፖሊስ ኃላፊ ኤሪክ ዳላግሊሽ " አሁን ላይ አራት ሲቪል ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ጥቃት አድራሹም ሞቷል " ብለዋል።  

እስካሁን ማንነቱ ያልተለየው ጥቃት አድራሽ እራሱ ሳያጠፋ እንዳልቀረ ተገምቷል።

ተጠርጣሪው ሁለት መሳሪያዎችን ታጥቆ የነበረ ሲሆን " አንደኛው ረዝም ያለ፣ ሌላኛው ደግሞ የእጅ ሽጉጥ ነው በስፍራው የተገኘው " ብለዋል የፖሊስ ኃላፊው። 

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ሳዑዲ_አረቢያ ፦ ሳዑዲ አረቢያ የሃጅ ተጓዦችን እየተቀበለች ትገኛለች። ከቀናት በፊት የመጀመሪያው የሃጅ ተጓዦች ቡድን ከኢንዶኔዥያ ወደ ሳዑዲ መግባቱ ይታወሳል። ዛሬ ባገኘነው መረጃ እስከ ትላንት እሁድ ድረስ ከተለያዩ ሀገራት ለሃጅ ጉዞ ሳዑዲ የገቡ ተጓዦች 955 ደርሰዋል። ሳዑዲ አረቢያ ዘንድሮ ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ 1 ሚሊዮን የሃጅ ተጓዦችን እንደምታስተናግድ ይታወቃል።

#ጀርመን ፦ የጀርመኑ መኪና አምራች ኩባንያ መርሴዲስ-ቤንዝ 1 ሚሊዮን ገደማ አሮጌ መኪናዎችን ለጥገና ጠርቷል። ኩባንያው እኚህ መኪናዎች ፍሬናቸው ችግር አለባቸውና ጠግኜ ልመልስላችሁ ብሏል። ኩባንያው መኪኖቹ ከፍተኛ በሆነ ዝገት ምክንያት የፍሬን ሰርዓታቸው ተገቢውን ሥራ ላይሰራ ይችላል ብሏል። ጀርመን ያሉ 70 ሺህ መኪናዎችን ጨምሮ ከ993 ሺህ በላይ መኪናዎች መጠገን አለባቸው።

#UK ፦ ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመርያ ጊዜ ኤም 270 የተባሉ ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለዩክሬን ልትሰጥ ነው። እነዚህን እጅግ ዘመናዊ ሮኬት ማስወንጨፍያ መሣሪያዎች መቼ እና በምን ያህል መጠን ወደ ዩክሬን እንደምትልክ አልገለጸችም።

#ሩስያ ፦ የሩስያ ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአሜሪካ ማስጠንቀቂያ ልከዋል። ሀገሪቱ ለዩክሬን የጦር መሣሪያ ልገሳ እንድታቆም ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ሩሲያ በዩክሬን የምታደርሰው ጥቃት መጠኑ እየሰፋ እንደሚመጣ ገልፀዋል። አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ዘመናዊ ተወንጫፊ ሚሳኤል ሲስተምን ወደ ዩክሬን ልካለች። አሜሪካ መሣሪያውን ብትሰጥም ዩክሬን ይህን መሣሪያ ወደ ሩሲያ ግዛት እንዳትተኩስ አሳስባ ነው።

#ቢቢሲ #ሳዑዲጋዜቴ #ኤፒ

@tikvahethiopia
የጠ/ሚ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ምን አሉ ?

- መንግስት የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ለመቋጨት በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ለሚደረገው ሂደት ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

- የሰላም ሂደቱ ውስብስብ እና ረጅም መሆኑን ገልፀዋል። “የትኛውም የሰላም ሂደት ረጅም ነው። ቀላል አይደለም። ውስብስብና የተደራረቡ ሁነቶችን የያዘ ነው” ብለዋል።

- ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪ ለሆኑት ኦባሳንጆ ትልቅ ቦታ እንዳላት ተናግረዋል።

- ከባለፈው ሐምሌ ወር ጀምሮ 2 ነጥብ 1 ቢሊየን ጥሬ ብር፣ 87 ሺ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና ከ783 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ ፣ 217 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የህክምና መድሃኒቶች እንዲሁም የመጠለያ ግብዓቶች ጨምሮ 130 ሺህ ኪሎ ግራም ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ ድጋፎች ወደ ትግራይ ክልል ተልኳል ብለዋል።

- ህወሓት ቀጣይ የዝናብ ወቅት እየመጣ ባለበት በዚህ ወቅት ለሌላ ጦርነት እየተዘጋጀ መሆኑን ያሉ ሲሆን ህዝቡን በሃይል ለጦርነት እየመለመለ ነው ብለዋል። ድርጊቱ ቀጣዩን የእርሻ ስራ እንደሚያደናቅፍና በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያባብስ ያደርጋል ብለዋል።

- በአፋር ክልል በግጭቱ ጉዳት ለደረሳበቸው ዜጎች 19 ሺ ሜትሪክ ቶን ምግብ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮችም 244 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ መሰራጨቱን ገልፀዋል።

#ቢቢሲ #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Ethiopia #Sudan " መረጃው ውሸት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ " በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ በተጠንቀቅ ቆሟል " - አቶ አብራራው ተስፋ " ሱዳን ትሪቡን " የተባለው የሱዳን ሚዲያ የሱዳን ጦር ሰራዊት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኃይሎች ተወሰደብኝ ያለውን እርምጃ ለመበቀል የይገባኛል ጥያቄ በሚናሳበት የአልፋሽጋ አካባቢ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ስር የነበሩ " ካላ…
#Update

ከ1 ወር በፊት ተዘግቶ የነበረው የጋላባት ድንበር ተከፈተ።

ሱዳን ከ1 ወር በፊት ዘግታው የነበረውን እና ከኢትዮጵያ የሚያዋስናትን ቁልፍ የድንበር በረ ከፍታለች።

ሱዳን ድንበሩ የተከፈተው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ገንቢ የሆነ ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው ብላለች።

ከአንድ ወር በፊት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያወስነኝ አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት የጦር አባላቶቼ ተገድለውበኛል ስትል ክስ ማሰማቷ ይታወሳል።

ሱዳን በኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ተፈጽሟል ባለችው ጥቃት 6 ወታደሮቿ እና አንድ ሲቪል መገደሉን ገልጻ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግሥት/የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሰዎች ህይወት መጥፋት ሀዘን እንደተሰማው ገልጾ ነገር ግን በሱዳን የተሰራጨው መረጃ ትክክል እንዳልነበር መግለፁ ይታወሳል።

በመጀመሪያ ደረጃ በቦታው በነበረው ግጭት የአገር መከላከያ ሠራዊት ተሳትፎ እንዳልነበረው የተገለፀ ሲሆን ጉዳቱ ያጋጠመው ደግሞ እራሳቸው የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሠው አልፈው ከገቡ በኋላ ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር በተደረገ ግጭት ነው።

አሁን የገላባት ድንበር በር እንዲከፈት የተወሰነው ድንበር ላይ ያጋጠመውን ችግር የሁለቱ አገራት መሪዎች ለመፍታት ከተስማሙ በኋላ መሆኑን ሱና የሱዳን ደኅንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ቴክኒክ ኮሚቴን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በድንበር አካባቢ የታጠቁ ኃይሎችን ለመቆጣጠር "በኢትዮጵያ በኩል የታየው በጎ ፍቃድ" የድንበር በሩ እንዲከፈት ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳኑ መሪ ሌ/ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ከሳምንታት በፊት ለኢጋድ ስብሰባ በኬንያ በተገኙበት ወቅት ስለሁለቱ ሀገራት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች የጎንዮሽ ውይይት ማድረጋቸው አይዘነጋም። #ሱና #ቢቢሲ

@tikvahethiopia
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት !

የልጁን ሕይወት ለማዳን ከጀልባ ላይ የዘለለው እንግሊዛዊ አስክሬኑ ጣልያን ተገኘ።

ዛሬ ጥዋት ቢቢሲ በደረገፁ አንድ አሳዛኝ ክስተት አጋርቷል።

አረን ቻዳ የተባለ እንግሊዛዊ ልጁን ለመታደግ ከጀልባ ከዘለለ በኋላ ለሳምንታት ጠፍቶ አስክሬኑ ጣልያን ውስጥ ተገኝቷል።

አረን ባለፈው ወር " ጋርዳ " የተባለ ባሕር አካባቢ ከትዳር አጋሩና ከሁለት ልጆቹ ጋር እየተንሸራሸረ ነበር። ሽርሽሩ ተዘጋጅቶ የነበረው የአረንን 52ኛ ዓመት ልደት ለማክበር ነበር።

ቤተሰቡ ጀልባ ተከራይቶ በባሕር እየተጓዘ ሳለ  የአረን ልጅ " ሊሞን " የተባለ ሪዞርት አካባቢ ችግር ገጠመው። አባትም ልጁን ለማዳን ከጀልባው ከዘለለ በኋላ አስክሬኑ ከሊሞን በ800 ሜትር ርቀት፣ በ316 ሜትር ጥልቀት እንደተገኘ የነፍስ አድን ሰራተኞች ገልጸዋል።

#ልጁን_ካዳነ በኋላ ውሃ ውስጥ መስመጡት የተገለፀው አረን  " የሰመጠው አንዳች ሕመም ስላለበት ይመስለኛል " ሲል አንድ ነፍስ አዳን ሰራተኛ ገልጿል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት ! የልጁን ሕይወት ለማዳን ከጀልባ ላይ የዘለለው እንግሊዛዊ አስክሬኑ ጣልያን ተገኘ። ዛሬ ጥዋት ቢቢሲ በደረገፁ አንድ አሳዛኝ ክስተት አጋርቷል። አረን ቻዳ የተባለ እንግሊዛዊ ልጁን ለመታደግ ከጀልባ ከዘለለ በኋላ ለሳምንታት ጠፍቶ አስክሬኑ ጣልያን ውስጥ ተገኝቷል። አረን ባለፈው ወር " ጋርዳ " የተባለ ባሕር አካባቢ ከትዳር አጋሩና ከሁለት ልጆቹ ጋር…
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት !

የልጁን ህይወት ለማትረፍ ናይል ወንዝ የገባው አባት አስከሬኑ ተገኘ።

ስሙ ሮበርት ክዌሲ ይባላል የኡጋንዳ ተወላጅ ዜግነቱ ደግሞ እንግሊዛዊው ነው ፤ እድሜው 48 ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ ነበር።

ሮበርት ከባለቤቱ ጀስቲን ካታንታዚ እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ወደ ኡጋንዳ ለእረፍት ይመጣሉ። ኡጋንዳ መጥተው እየተዝናኑ ሳለ የ12 አመት ልጁ እየዋኘ በነበረበት ወቅት በነበረው ማዕበል ችግር ስላጋጠመው አባት ልጁን ለመርዳት ዘሎ ይገባል። ምንም እንኳን አባት ልጁን ቢያተርፍም የእሱ ደብዛ ግን ከዛች ደቂቃ አንስቶ ይጠፋል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች እና ጠላቂ ፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው በጎ ፍቃደኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ፍለጋ ያደርጋሉ በኃላም የሮበርትን አስክሬን አግኝተዋል።

ሮበርት ክዌሲ አስክሬኑ የተገኘው በናይል ወንዝ በአንደኛው ክፍል ነው ተብሏል።

ሮበርት በእንግዚዝ ፍሪጅ እና አየር ማቀዝቀዣዎችን በመጠገን በተቋራጭነት ይሰራ ነበር። ከባለቤቱ ጋር ጋብቻቸውን የፈጸሙት ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኡጋንዳ እንደነበር #ቢቢሲ ፅፏል።

ትላንትም አንድ እንግሊዛዊ አባት የልጁን ህይወት ለማትረፍ ሲል ከጀልባ ዘሎ ልጁን አትርፎ እሱ ግን ህይወቱ እንዳለፈ አስክሬኑም ጣልያን ውስጥ መገኘቱን የሚገልፅ መረጃ ማንበባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#Kenya

የኬንያ ፖሊስ 41 ኢትዮጵያውያንን ናይሮቢ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገለፀ።

ግለሰቦቹ ወደ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች አገራት ለመዘዋወር በአንድ ቤት ውስጥ ለአራት ቀናት ያህል ሲጠባበቁ ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም መያዛቸውን ገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑን በሕገ ወጥ መንገድ ሊያዘዋውሩ ነበሩ የተባሉ ሁለት አዘዋዋሪዎችም በዚሁ አጋጣሚ የተያዙ ሲሆን አንደኛው #ኢትዮጵያዊ መሆኑም ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸው እነዚህ የሕገ ወጥ ሰዎች አዘዋዋሪዎች በአገሪቱ ውስጥ ካሉ ሌሎች በርካታ ዝውውሮች ጀርባ እንዳሉበት ተገልጿል።

ኢትዮጵያውያኑ በዚህ ሳምንት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ወደ ኬንያ እንዴት እንደገቡ ተጨማሪ ምርመራ እስኪደረግ ድረስ ለተጨማሪ ስድስት ቀናት በእስር እንዲቆዩ መታዘዙን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia