TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።

በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopia
🔹 " እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው #በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው " የመ/ግ/ን/ባ

በመንግሥት የግዥ ሒደት እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ መሆኑን፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለሥልጣኑ ይህን ያስታወቀው ጥቅምት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በዘንድሮ በጀት ዓመት በ169 የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሲስተም ተግባራዊ ተደርጎና አፈጻጸሙን ለማሳደግ፣ ከንግድ ማኅበረሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ላይ ነው፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐጂ ኢብሳ ምን አሉ ?

- በመንግሥት በግዥ ሥርዓት ውስጥ፣ ከ80 እስከ ከ90 በመቶ በላይ ሙስና የሚፈጸመው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ነው ብለዋል።

- ስሙን መጥቀስ ያልፈለጉት የመንግሥት ተቋም #በጨረታ አንደኛ የወጣ ድርጅት እያለ ሦስተኛ ከወጣው ጋር ውል መግባቱን፣ በዚህም ምክንያት ባለሥልጣኑ እስከ ፍርድ ቤት በመሄድ ሒደቱ እንዲቋረጥ ማደረጉን ገልጸዋል፡፡

- ከኮንስትራክሽን ጋር ተያይዞ ጨረታ የሚያወጡ የመንግሥት ተቋማት #የሚፈልጉዋቸው ተጫራቾች ካልመጡ እስከ #መሰረዝ እንደሚደርሱ አመልክተዋል።

- የመንግሥት ተቋማት ተጫራቾችን ሆን ብለው ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ሕጎችን እንደ ምክንያት እንደሚጠቀሙ፣ ያሸነፉ ተጫራቾችንም #እንዲሰላቹ በማድረግ ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ እንደሚያደርጉ ጠቁመዋል፡፡

- በመንግሥት የግዥ ሥርዓት ምክንያት የሚመጡ ክሶች መኖራቸውን ገልጸው በዓመት እስከ 150 የሚደርሱ ክሶች እንደሚስተናግዱ ተናግረዋል። በአብዛኛው ጨረታ የማውጣትና የሚገመገምበት መሥፈርት በመለያየቱ ምክንያት በርካታ ተጫራቾች ክስ እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢጋድ አባል አገሮችና የነጋዴ ሴቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ ምን አሉ ?

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ከታዩ ክፍተቶች አንዱ በጠቅላላ የመንግሥት ግዥ መባሉ ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

- የመንግሥት ግዥ ተብሎ ስያሜ ቢሰጠውም የመንግሥት ተቋማትና የንግዱ ማኅበረሰብ የሚገናኙ በመሆናቸው ከስያሜ ጀምሮ ማስተካከያ ይፈልጋል ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ሙስናን ለመቅረፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጻዋል። ከዚህ ቀደም #በዩኒቨርሲቲዎች በሚደረጉ ግዥዎች ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምርቶች እየቀረቡ እንደነበርና ሥርዓቱ መዘመኑ በተወሰነ መንገድ ችግሩን መቀረፉን አስረድተዋል፡፡

- በኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ለሚታዩ የሙስና ብልሹ አሠራርን ከሥሩ ማድረቅ እንደሚገባ፣ በተለይ ተጫራጮች ወደ ተቋማት ሲሄዱ #ሲስተም_የለም የሚለው ቋንቋ የችግሩ መጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

- ተጫራቾች ወይም የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ለሙስና እንዳይጋለጡ መብቶቻቸውን ለማስጠበቅ ሞጋችና ተከራካሪ መሆን አለባቸው ብለዋል።

የመንግሥት ግዥ የንብረት ባለሥልጣን የመንግሥት ግዥ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ ከበደ ምን አሉ ?

- የነባሩ የወረቀት የግዥ ሥርዓት የሙስና ተጋላጭነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥናት እየተደረገበት ነው ብለዋል።

- የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት መኖሩ የሚቀርፏቸው ችግሮች ሰፊ ከመሆናቸው ባሻገር፣ ለብዙ ተጫራቾች ዕድል ከመስጠት አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

- የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት በ2015 ዓ.ም. ሲጀመር የተመዘገቡት የንግድ ማኅበረሰብ አባላት 100 ብቻ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጥቅሉ ከ15‚000 በላይ ተሻግረዋል።

- ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ በጀቷ 70 በመቶ የሚውለው ለግዥ ሥርዓት መሆኑን ገልጸው ይህም በገንዘብ ሲቀየር 560 ቢሊዮን ብር ለግዥ እንደሚውል ተናግረዋል።

#ReporterNewspaper

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሲቢኢ #ዩኒቨርሲቲዎች #ኦዲት

" ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል፤ ዝውውሩም አይታወቅም ብለው አስበው ነው ያደረጉት " - አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት አቶ አቤ ሳኖ በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ስለነበረው የመጋቢት 6 ለሊት የገንዘብ ዝውውር እና አጠቃላይ ወጭ ስለተደረገው / አሁን ስለተመለሰው የገንዘብ መጠን ምን አሉ ?

አቶ አቤ ሳኖ ፦

" የተቋረጠውን አገልግሎት ካስጀመርን በኃላ ወደ ግብይቶች ምርመራ ነው የገባነው።

በዛ ያለ ግብይት ያደረጉትን ለይተናቸው የፍትሕ አካላት እንዲያውቁት አድርገናል። በብዛት በዛ ያለ ቁጥር ያለው እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ #በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ ነው።

ተማሪዎቹ (የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ) ያሰቡት ባንኩ ላይ የሳይበር ጥቃት ደርሷል ብለው ነው። ስለዚህ የሚደረገው ግብይት (ወጭ / ዝውውር) አይታወቅም ብለው ነው ያደረጉት።

አሁን ላይ ግን ግብይቱ እንደሚታወቅ ሲያውቁ የወሰዱትን ገንዘብ እየመለሱ ነው ያሉት። አሁንም እንዲመልሱ ነው የምንፈልገው።

የወሰዱትን ገንዘብ ከመለሱ ወደ ክስ አንሄድም። የማይመልሱ ከሆነ ግን የህግ እርምጃ እንወስዳለን።

ዝርዝር ጉዳዩ (ከገንዘብ ዝውውር/ወጭ የተደረገ/የተመለሰ) ኦዲት ተደርጎ ሲያልቅ ይቀርባል።

የኦዲት ሂደቱ ስላላለቀ በዚህ መካከል ሌሎች ነገሮችን ማንሳት ከፋይናንሻል ኦዲት አካሄድ ጋር የሚሄድ ስላልሆነ አንዳንድ የህጋዊ እርምጃዎችም ሊከተሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ስለሚፈልግ ነው። "

@tikvahethiopia