TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#Update

🗣 " ጦርነት ላይ ነን ፤ ጦርነቱንም እናሸንፋለን " - የእስራኤል ጠ/ሚ

🗣 " የከፈትነው ወታደራዊ ዘመቻ #ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ ነው " - ሃማስ

#በእስራኤል እና #ሃማስ መካከል ግጭቱ መባበሱ ተገልጿል።

- የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሕዝባቸው " የእስራኤል ህዝብ ሆይ ፤ ጦርነት ላይ ነን ፤ ይህን ጦርነትም እናሸንፋለን " ብለዋል።

- የእስራኤል ሀገር መከላከያ ሚንስቴር " ሃማስ ከባድ ስህተት ሰርቷል ፤ ለዚህም የከፋ ዋጋ እንደሚከፍል እና ለውጤቱም ሁሉ ኃላፊነቱን ይወስዳል " ብሏል።

- ፈረንሳይ ፣ ዩኬ ፣ ጀርመን ፣ ጣሊያን ፣ አውሮፓ ህብረት ሃማስ የፈፀመውን ጥቃት አውግዘው ከእስራኤል ጎን እንቆማለን ፤ እራሷን የመከላከል መብት አላት ብለዋል።

- በሃማስ ጥቃት በትንሹ 22 እስራኤላውያን መገደላቸው ተነግሯል።

- በምስራቅ እየሩሳሌም አካባቢ በእስራኤል ፖሊስ እና ፍልስጤማውያን መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተሰምቷል።

- ሃማስ ዛሬ ያለው ሁኔታ ከወራሪ ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው ብሏል። የከፈተው ወታደራዊ ዘመቻ ፍልስጤማውያን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ለደረሰባቸው ግፍ ሁሉ ምላሽ ነው ሲል ገልጿል።

- #ሂዝቦላህ ሃማስን #አወድሶ ቀጥተኛ ግንኙነት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

- ሃማስ እስካሁን 7000 ሮኬት ማስወንጨፉን ገልጿል።

- ሃማስ እስራኤል ላይ እያካሄድኩ ነው ባለው ኦፕሬሽን በርከት ያሉ #የእስራኤል_ወታደሮችን መያዙን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Update

ኢትዮጵያ #ድምፀ_ተአቅቦ ያደረገችበት የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባኤ ተካሄደ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት ጉዳይ  አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ አካሂዷል።

በዚህም ጉባኤ በ " ዮርዳኖስ " አቅርቢነት በጋዛ " አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም " እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።

የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦
- በ120 ድጋፍ፣
- በ14 ተቃውሞ
- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።

ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።

የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ የተካሄደው በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ነው።

እስራኤልም በጋዛ የምድር ዘመቻ ማካሄድ ጀምራለች።

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ አማካሪ ማርክ ሬጅቭ  የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን #ሃማስ በሰብአዊነት ላይ በርካታ የግፍ ወንጀሎችን መፈፀሙን ገልጸው ለዚህም ደግሞ ከዓርብ ምሽት (ትላንት) ጀምሮ ክፍያውን #እንደሚከፍል እና እስራኤልም መመለስ መጀመሯን ተናግረዋል።

ሀማስ እስራኤል ለምታካሂደው የምድር ላይ ዘመቻ አፀፋውን ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ገልጿል።

የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛው አመራር ኢዛት አል-ሪሻቅ " ኔታንያሁ ወደ ጋዛ ለመግባት ከወሰነ እኛም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " የወታደሮቹ ሬሳ በጋዛ ምድር ይዋጣል " ብለዋል።

21ኛ ቀኑን በያዘው በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት በእስራኤል ጥቃት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ከ7300 መብለጣቸውን በሃማስ ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በእስራኤል በኩል በሃማስ የተገደሉም ከ1400 በልጠዋል።

ℹ️ ተጨማሪ #የውጭ_ሀገር_መረጃዎችን በዚህ መከታተል ይችላሉ 👉https://t.iss.one/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Palestine

ዛሬ አይርላንድ ፣ ኖርዌይ እንዲሁም ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አስታወቁ።

" የዛሬው ቀን ለፍልስጤም እጅግ ታሪካዊ ቀን ነው " ተብሏል።

የአየርላንድ ጠ/ሚኒስትር ሲሞን ሃሪስ " ዛሬ አየርላንድ ፣ ኖርዌይ እና ስፔን ለፍልስጤም የነጻ ሀገርነት እውቅና ሰጥተናል። ውሳኔውን ተግባራዊ ለማድረግ እያንዳንዳችን ማንኛውንም አይነት ብሔራዊ እርምጃ እንወስዳለን " ብለዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " #በሚቀጥሉት_ሳምንታት ተጨማሪ ሀገራት ይህን ጠቃሚ እርምጃ ለመውሰድ ከእኛ ጋር እንደሚተባበሩ እርግጠኛ ነኝ " ሲሉ አክለዋል።

የአይርላንድ መንግሥት ይህ የሀገርነት እውቅና የሁለት ሀገር መፍትሄን እንደሚደግፍና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።

የስፔኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እና የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ኢስፔን ባርት ኢይድ ሀገራቸው ከግንቦት 28 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ለፍልስጤም ግዛት እውቅና እንደሚሰጡ በይፋ አሳውቀዋል።

የስፔኑ ጠ/ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ፥ " ምንም እንኳን ከአሸባሪው ቡድን #ሃማስ ጋር የሚደረገው ውጊያ ህጋዊ ቢሆንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለፍልስጤም የሰላም ፕሮጀክት የላቸውም " ብለዋል።

የኖርዌይ ጠ/ ሚኒስትር ጆናስ ጋህር ስቶር በበኩላቸው ፥ " እውቅና ከሌለ (የፍልስጤም) በመካከለኛው ምስራቅ ምንም ሰላም ሊኖር አይችልም " ብለዋል።

" ሽብር የተፈፀመው በሃማስና የሁለት ሀገር መፍትሄን በማይቀበሉ እንዲሁም የእስራኤልን መንግሥት በማይደግፉ ታጣቂ ቡድኖች ነው። " ሲሉ አክለዋል።

" ፍልስጤም ነጻ አገር የመሆን መሠረታዊ መብት አላት " ብለዋል።

የፍልስጤም #የነጻ_ሀገርነት እውቅና መስጠት በይፋ ከተሰማ በኃላ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር #በኖርዌይ እና #በአይርላንድ የሚገኙ አምባሳደሮችን በአስቸኳይ ወደ እስራኤል እንዲመለሱ አዘዋል።

ሚኒስትሩ፤ " የዛሬው ውሳኔ ሽብርተኝነት እንደሚከፍል ለፍልስጤማውያን እና ለዓለም መልእክት ያስተላለፈ ነው " ብለዋል።

መረጃው የስካይ ኒውስ ነው።

More - @thiqahEth