TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#LieutenantGeneralBachaDebele 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ ለቢቢሲ ቃለምልልስ ሰጥተዋል።

ቃለምልልሱ በወቅታዊ የጦርነቱ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ህወሓት ባደራጀው ሰራዊት አዲስ አበባ ገብቶ ኢትዮጵያን እበትናለሁ በሚል ሂሳብ እስከ ሰሜን ሸዋ የተወሰኑ አካባቢዎች ድረስ ገብቶ እንደነበር ገልፀዋል።

" በመከላከል ማዳከም ከዚያም በማጥቃት ለመደምሰስ በሚለው መርህ መሰረት። ይህንን ኃይል ለተከታታይ አንድ ወር መከላከል አድርገናል። ለማጥቃት የሚያስችለንን ተገቢ ዝግጅት በመከላከል ውስጥ ሆነን አድርገናል። ሰሞኑን የማጥቃት እርምጃ ወስደናል " ብለዋል።

በተወሰደው የማጥቃት እርምጃ ሰሜን ሸዋ የነበረውን የጠላት ኃይል አባረናል ፤ በጋሸና፣ በደቡብ ወሎ፣ በወረ ኢሉ እንዲሁም በምሥራቅ ከጭፍራ አልፈን በዋናው መስመር በባቲ በኩል የነበረውም እንደዚሁ አባረናል ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ አርብ ባቲም፣ ደሴም ኮምቦልቻም አንድ ላይ ይያዛሉ የሚል ግምት እንዳለ የተናገሩት ሌ/ጄነራሉ አሳውቀዋል።

እየታየ ያለው ውጤት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ግንባር ከመሄዳቸውም ጋር እንደሚያያዝ እና የጠ/ሚኒስትሩ ወደዚያ መሄድ የሠራዊቱን የመስራት አቅም በከፍተኛ ደረጃ እንደጨመረው ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከትላንት በስቲያ #ህወሓት በአማራ ክልል ተይዘው ከነበሩ ቦታዎች በታክቲካዊ ውሳኔ ሠራዊቱ ለቆ መውጣቱን ስለገለፀበት መግለጫ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ፥ "ምን እንዲሉ ነው የሚጠበቀው ? በአቅማቸው በጉልበታቸው አይደለም እዚህ የደረሱት። በላኳቸው ሰዎች ጉልበትና አቅም ነው እዚህ የደረሱት። ስለዚህ ጌቶቻቸው ለማስደሰት ምን ይበሉ ? " ብለዋል።

አክለውም ፥ " እነሱ እኮ አዲስ አበባ ለመግባት በቀናት ሳይሆን ሰዓታት ነበር ሲቆጥሩ የነበሩት። አንዳንድ የመገናኛ ብዙኃን እኮ አዲስ አበባ ተከባለች፣ ሊገቡ ነው የሚል ዘገባ ሲያስተላልፉ ነው የነበሩት። እነዚህ ሰዎች ተሸነፍን ሊሉ አይችሉም " ሲሉ መልሰዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ ስለድርድር ሲነሳ "መንግስት የለም ጦርነቱ አልቋል፣ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው" ብለዋል ሲሉ ያስታወሱ ሲሆን አሁን እነሱ ባልጠበቁት መንገድ የማጥቃት ጎርፍ ሲወስዳቸው ሊሉ የሚችሉት ይህንን ብቻ ነው ብለዋል።

" ለምን እንደድሮው ጻድቃን የሚባለው ወይም የእነሱ ሰዎች ወጥተው መግለጫ አይሰጡም? " ሱሉ የጠየቁት ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ " ስለመኖራቸውም እጠራጠራለሁ፤ ሁለተኛ ደግሞ ያንን ለማድረግ ሐፍረት ይዟቸዋል። ሐፍረት የያዛቸው ስለጌቶቻቸው ነው። በዚህ ጉዳይ ትልልቆቹ ምዕራባዊያን ናቸው የሚያፍሩበት። ሊሉ የሚችሉት አልተሸነፍንም ለቀቅን ነው። መልሰን እናጠቃለን የሚል ቃል ለመግባት የተደረገ ነው " ብለዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ፥ " በሳተላይት ይከታተሉናል ሲሉ ነበር። ስለዚህ ከየት ቦታ እንደወጡ በደንብ ያያሉ። ስለዚህ ተመትተው እንደወጡ እነሱ ቢክዱም ጌቶታቸው ያውቃሉ " ያሉ ሲሆን " ከአማራ ክልል ለቀን ወጣን ካሉ ከአፋር ክልልስ ይህንን ሁሉ መሬት እንዴት አድርገው ለቀቁ ? ጭፍራ፣ ቡርቃ፣ ጪፍቱ አፋር ናቸው። ይሄንን ሁሉ መሬት እንዴት አድርገው ነው የለቀቁት። አመኑም አላመኑም የሆነው ይሄ ነው " ብለዋል።

ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፤ በቀጣይ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ትግራይ ክልል መዲና #መቐለ የማምራት እቅድ ይኖረው እንደሆነ ተጠይቀው ፥ " ይህ ወታደራዊ ጉዳይ ነው። እኛ እዚህ ጋር እንቆማለን አንልም። ወታደራዊ ሁኔታው ነው የሚወስነው። ጦርነት በእርግጠኝነት የሚነገር ነገር አይደለም። የማይገመቱ ነገሮች (አንሰርቴይኒቲ) የሞላበት ነው። ስለዚህ በቀጣይ የሚፈጠረው ነገር ነው የሚወስነው። ነገር ግን እኛ አንቆምም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ጦሩ ህወሓት የያዛቸውን ቦታዎች ደረጃ በደረጃ እያስለቀቀ እና እየደመሰስ እንደሚቀጥል የተናገሩት ሌ/ጄነራል ባጫ ደበሌ ፤ " መቐለ ነው የምንቆመው የት ነው የምንቆመው ለሚለው፤ የምንቆም አይደለንም። አሁን ግን እቅዳችን እዚህ ድረስ ነው የሚል ነገር የለንም " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጦር ህወሓት የገባበት ገብቶ እስከሚያጠፋው ድረስ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia