TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD #EthioSudan #Egypt #Sudan

ዛሬ ለአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ገለፃ ተደርጓል።

በኪኒሻሳ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የተካሄደውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ በተመለከተ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች ገለጻ አድርገዋል።

በዚህም ወቅት በኪንሻሳው ስብሰባ ውይይት የተደረገባቸውን ጉዳዮች እና የኢትዮጵያን ዕይታ በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል።

በዛሬው ገለፃ ዶክተር ኢ/ር ስለሺ ፥ ግብጽና ሱዳን የህዳሴውን ግድብ የአረብ አገሮች የውሃ ደህንነት ስጋት አድርገው የሚያቀርቡት ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል። የአባይ ተፋሰስ አገራት ሁሉ አፍሪካዊ ሆነው ሳሉ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል የሚያራምዱት አቋም ተቀባይነት የሌለውና ሁሉም በአጽንኦት ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል።

በሌላ በኩል ፥ ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወቅታዊ የድርድር ሁኔታ በተጨማሪ ለአምባሳደሮቹ የኢትዮጵያ-ሱዳን ወቅታዊ የድንበር ሁኔታን በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረጉ ስምምነቶች እና ባሉት የድንበር አሰራር ማዕቀፎች አማካኝነት በድርድር ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ገልጻለች።

* ዝርዝር መረጀው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia