TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#US_EMBASSY

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በጋምቤላ ክልል ሁለት የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች የገደሉ ታጣቂዎችን መንግሥት በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠየቀ። አክሽን አጌይንስት ኸንገር የተባለው ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅት ሰራተኞች ጥቃት የተፈጸመባቸው በጋምቤላ ክልል ደቡብ ሱዳናውያን ስደተኞች ከሚኖሩበት ኙንዬል ከተባለ የመጠለያ ጣቢያ (Nguenyyiel Refugee Camp) ሥራቸውን አጠናቀው በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደነበር ድርጅቱ አስታውቋል። በጥቃቱ የመስክ ሰራተኛ እና አሽከርካሪ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የግብረ-ሰናይ ሰራተኞች መሆኑን የሚጠቁም ምልክት በነበረው ተሽከርካሪ ላይ ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግብፅ🤔

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ከስምንት አመታት በፊት በአገራቸው #የጸደይ_አብዮት ባይነሳ ኖሮ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ባልሰራች ነበር ሲሉ ተናገሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ AhramOnline👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-7

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኬንያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት የምረጡኝ ዘመቻዋን በይፋ ጀምራለች። ኬንያ ብቸኛዋ የአፍሪካ እጩ ሆና ለመቅረብ የነበራትን ፍላጎትና በአፍሪካ ኅብረት የተላለፈውን ውሳኔ ጅቡቲ ውድቅ አድርጋለች።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
«ግብፆች የኅዳሴ ግድብ በየአመቱ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሐ የመልቀቅ ስምምነት እንዲደረስ ይፈልጋሉ። ይኸ ደግሞ ተገቢ አይሆንም። ያንን ያህል ውሐ ወደ ታች የማስተላለፍ ግዴታ ልንስማማ አንችልም» የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር #ስለሺ_በቀለ

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግብፅ

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል–ሲሲ ኢትዮጵያ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ለመገንባት ስትነሳ አመርቂ ጥናት #አልሰራችም ሲሉ ከሰዋል። በግድቡ ላይ የሚደረገው ድርድር ፈቅ ሳይል መቀጠሉ በቀጠናው መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ሲሉ #አስጠንቅቀዋል

የግብፁ ፕሬዘዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተባበሩት መንግስታት መደበኛ ጉባኤ ያላይ ያደረጉትን ንግግር ከዚህ በታች በምታገኙት የዩትዩብ ሊንክ ገብታችሁ ማድመጥ ትችላላችሁ፦ "President Abdel Fattah el-Sisi Speech at 74th UN General Assembly" https://youtu.be/ibx4s7ZAs78

ከ12ኛው ደቂቃ ጀምሮ...

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EGYPT vs #ETHIOPIA | ግብጽ በይፋ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀምራለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ #ሳሜሕ_ሽኩሪ በካይሮ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ በድርድሮቹ ኢትዮጵያ «ግትር» ሆናለች ሲሉ መውቀሳቸውን አል ሞኒተር የተባለው የግብጽ ጋዜጣ ዘግቧል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሐምዲ ሎዛ በበኩላቸው መቀመጫቸውን በካይሮ ካደረጉ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ የሌሎች አገሮችን ጥቅም ችላ በማለት የራሷን አተያይ ብቻ ለመጫን ጥረት እያደረገች ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትንሹ 6,000 ኤርትራውያን፣ ኢትዮጵያውያን፣ ሶማሊያውያን እና ሱዳናውያን ስደተኞች #በማሰቃየት እና #በማጎሳቆል በሚከሰሱ የሊቢያ ታጣቂዎች በሚያስተዳድሯቸው እስር ቤቶች እንደሚገኙ አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ItsMyDam #GeduAndargachew

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካ ግምዣ ቤት በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያወጣው መግለጫ "ተቀባይነት የሌለው እና እጅጉን ለአንድ ወገን ያደላ ነው" ሲሉ ወቅሰዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኅዳሴ ግድብ ድርድር ሁሉም ወገኖች መደመጣቸውን፣ አሜሪካም ወገንተኛ አለመሆኗን ለማረጋገጥ ምን እያደረጋችሁ ነው ተብለው የተጠየቁት የአሜሪካ ግምዣ ቤት ሴክሬታሪ ስቴቨን ምኑችን ጥያቄውን በቀጥታ ሳይመልሱ ቀርተዋል።

የኔቫዳው የኮንግረስ አባል ስቴቨን ሖርስፎርድ ሚዛናዊ ብትሆኑ ኢትዮጵያ ወደ ድርድሩ ልትመለስ ትችላለች ብዬ አስባለሁ ሲሉ ለምኑችን ነግረዋቸዋል።

ከግብጽ በተጨማሪ ሱዳን ከስምምነት ሳይደረስ ግድቡ በውኃ ሊሞላ አይገባም የሚል አቋም እንዳላት ምኑችን በአሜሪካ ኮንግረስ Ways & Means Committee ኮሚቴ ተናግረዋል። ኮሚቴው ከውጭ ግንኙነት ጋር የማይቀራረብ የመንግሥት በጀት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ነው።

#EsheteBekele #LamFilmona

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሹመት!

አቶ ሙሉቀን አማረ የፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከየካቲት 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ተሹመዋል፡፡አቶ ሙሉቀን በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ከ 2003 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙን አገልግለዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia