TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Election2013

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር የጎንደር ከተማ ሕዝብን ወክለው ለክልል ምክር ቤት ለመወዳደር በእጩነት ተመዘገቡ።

ፕሬዜዳንቱ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው ነው በጎንደር ከተማ በሚገኘው ምርጫ ክልል 2 ነው በእጩነት የተመዘገቡት።

አቶ አገኘው ተሻገር በምዝገባው ወቅት የምርጫ ክልሉ ሠራተኞች በአግባቡ እንዳስተናገዷቸው ተናግረዋል።

አቶ አገኘሁ ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን አንድም እንደ መንግሥት ሁለትም እንደ ፓርቲ ኀላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የጎንደር ከተማ ምርጫ ክልል 2 ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ካሳይ እስካሁን በምርጫ ክልሉ የተመዘገቡ እጩ አቶ አገኘሁ መሆናቸውን በመጠቆም ሌሎች 3 እጩዎች በቀሪ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ ማቅረባቸውን አብመድ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2013

በደ/አፍሪካ እየታተመ ያለው የድምፅ መስጫ ወረቀት !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች እና ሚዲያዎች የተወጣጣ የልኡካን ቡድን ወደደቡብ አፍሪካ በመላክ የድምጽ መስጫ ወረቀት ህትመትን እንዲጎበኙ ማድረጉን አሳውቋል።

በቦርዱ ከፍተኛ አመራር ፍቅሬ ገብረ ሕይወት የተመሩት ከፓርቲዎች እና ከሚዲያዎች ለተውጣጡ ተወካዮች የድምፅ መስጫ ወረቀት የኅትመት ሂደቱን፣ የቴክኒክና የደኅንነት አጠባበቅ ሥርዓቱን በዝርዝር አይተዋል ተብሏል።

የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመት ስራ የሚከናወነው በሁለት የኅትመት ድርጅቶች ሲሆን አንዱ በደቡብ አፍሪካ በሚገኝ የሬን-ፎርም ኅትመት ማኅበር የሚሰራ ነው።

በጉብኝቱ የሥራ ሂደትና የኅትመቱ የደኅንነት አጠባበቁን ምን እንደሚመስል በኅትመት ኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ተሰጥቷል።

ጎብኝዎች ግልፅ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉትን ነገር በሥራ ኃላፊዎቹና በቦርዱ አመራር ፍቅሬ ገብረ ሕይወት አማካኝነት ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።

በደ.አፍሪካ የሚካሄደው ኅትመት የድምፅ መስጫ ወረቀት ኅትመቱን 45% የሚሸፍን ሲሆን፤ ይህውም ፦

- የደ/ብ/ብ/ክ፣
- የአማራ ክልል፤
- የሲዳማ ክልልና የደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ሕዝበ ውሣኔን ያካትታል።

ቀሪው 55% የሚሸፍነው የኅትመት ሥራ ዱባይ በሚገኘው አል-ጉህራር ማኅበር እየተከናወነ ይገኛል።

ለ4 ቀናት በቆየው ጉብኝትም የብልጽግና ፓርቲ፣ አብን፣ ህብር ኢትዮጵያ ፣ ኢሶዴፓ እንዲሁም የመኢአድ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢው እና የሚዲያ አካላት ስለመሳተፋቸው ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Election2013

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለምርጫ ምዝገባ ተጨማሪ ጊዜ መሰጠቱን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ በኢንተርኔት እንደሚከናወን ማሳወቁ እንዲሁም ይህንን ተከትሎ ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር አስታውሷል።

በየምርጫ ጣቢያዎቹ የሚደገረው መራጮች ምዝገባ ቢጠናቀቅም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተጨማሪ የምዝገባ ጊዜ መሰጠት እንዳለበት ቦርዱ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ድረስ https://www.ovrs.gov.et በሚገኘው የመመዝገቢያ ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጿል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምዝገባ ሊንክ በቦርዱ ድረገፅ www.nebe.org.et ላይ እንደሚገኝም አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#Election2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባን በአጠቃላይ ያጠናቀቀ ቢሆንም ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር አስታውቋል።

በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ላይ ያለው የመራጮች ምዝገባ ትላንትና በይፋ መጠናቀቁን አሳውቋል።

የመራጮች ምዝገባ በትላንትና ግንቦት 13 ቀን 2013 የተጠናቀቀባቸው ቦታዎች፦

• በምእራብ ወለጋ ዞን ( ለቤጊ እና ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል ውጨ)
• በምስራቅ ወለጋ ዞን ( ከአያና እና ገሊላ ምርጫ ክልል ውጪ)
• በቄለም ወለጋ ዞን ( ጊዳም ምርጫ ክልል ውጪ)
• በሆሮ ጉድሩ ዞን ( ከአሊቦ እና ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል ውጪ) የሚገኙት 24 የምርጫ ክልሎች ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሲከናወን የነበው ምዝገባ እና የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠናቋል።

በዚህም መሰረት በነዚህ ምርጫ ክልሎች የመራጮች መዝገብ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ድረስ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ሲሆን የመራጮች መዝገባ ቀን ከተጠናቀቀበት ቀን በኋላ ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ አይቻልም።

@tikvahethiopia
#Election2013

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል።

የመከላከያ ሚኒስቴር ምርጫው #ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ገልጸዋል፡፡

ከምርጫው በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት እንዲከናወን እና በመላው ሀገሪቱ ወንጀለኛን አድኖ ለመያዝ የመከላከያ ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ምርጫው በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲጠናቀቀቅ ሁሉም የበኩሉን ሃላፊነት እንዲወጣ ጥሪ መቅርረቡን አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 ዘግቧል።

PHOTO : FILE
@tikvahethiopia
#HappeningNow #Election2013

ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ 1133/2011 አንቀጽ 7 መሰረት የደምፅ አሰጣጡን የተረጋገጠ ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ምርጫ ቦርድ በሂደቱ ላይ የነበረው በጎ ጅምር፣ ተግዳሮት፣ ማሻሻያና ተስፋ ላይ የሚመለከታቸው አካላት ፣ የሂደቱ ተሳታፊዎች እና ሌሎች ለምርጫው ሂደት መሳካት አስተዋእጾ ያደረጉ አካላት የሚገኙበት ኮንፍረንስ በስካይ ላይት ሆቴል እያካሄደ ይገኛል።  

ዝግጅቱን የሚከታተሉ የቤተሰባችን አባላት በቦታው ተገኝተዋል።

መደበኛ መርኃግብሩ ሲጀምር በ VoiceChat መከታተል እንደምትችሉ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia