TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

በካናዳ ሀገር የቅርብ ጓደኛውን በመግደል የተጠረጠረው የ26 ዓመቱ ግለሰብ በአየር ትራንስፖርት ወደ #ኢትዮጵያ ማምለጡን የካናዳ ሃሚልተን ፖሊሰ አስታወቀ። በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው ኢብራሂም ኢሳክ ሁሴን የተባለው ግለሰብ፣ ከቶርንቶ ወደ ኢትዮጵያ ማምለጡን ተረጋግጧል ያለው ፖሊስ፣ የ29 ዓመቱን ኦብሳ ጁነዲ የተባለውን የቅርብ ጓደኛውን በመግደል መጠርጠሩ ታውቋል።

ሟች በጭንቅላቱ ላይ #በተተኮሰ_ጥይት የሞተ ሲሆን ወዲያውኑ ሕይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ ከግድያው 20 ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል አለመግባባቶች እንደነበሩ ማስረጃዎች አሉኝ ያለ ሲሆን ይህንንም በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች ማረጋገጡን ገልጿል።

የአለመግባባቱ ምንጭ ምን እንደሆነ ባይረጋገጥም ፓሊስ ባደረገው ፍተሻ በተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት አደንዛዥ ዕፅ መገኘቱን ይፋ አድርጓል። በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው #ካናዳዊው ግለሰብ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ቢሆንም ለምን ወደ ኢትዮጵያ ሊያመልጥ እንደቻለ አልታወቀም። ተጠርጣሪው ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት መሆኑንም ፖሊሰ ገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia