TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀረር

በሐረር ከተማ #ከአራተኛ እስከ #ሐማሬሳ የጎዳና ላይ ጽዳት ዘመቻ ተካሄደ። በክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት በክልሉ የሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች የሀገር መከላከያ፣ የክልሉ ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የሚኒሻ አባላት፣ የማረሚያ ኮሚሽን፣ ቄሮ፣ ቀሬ፣ የክልሉ ወጣቶች እና የሀይማኖት አባቶች በጋራ በመሆን በዛሬው እለት ከጥዋቱ 12 ጀምሮ ከአራተኛ እስከ ሐማሬሳ የጎዳና ላይ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል። የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ እንደገለጸው ሐረር ከተማ ለነዋሪዎቻ ምቹ ከተማ እንድትሆን ብልሹ አመለካከትና አሰራርን ከክልሉ እናስወገድ በሚል መሪ ቃል የጽዳት ዘመቻው እንደተካሄደ ተገልጿል። ቢሮው እንደገለጸው በሌሎች አካባቢዎች ተመሳሳይ የጽዳት ዘመቻ እንደሚካሄድ ገልጾ የክልሉ ህብረተሰብ አካባቢውን ማጽዳት እንደሚጠበቅበት ገልጻል።

Via #AD
@tsegabwolde @tikvahethiopia