TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኒውዚላንድ🔝

በኒውዚላንድ #ክሪስትቸርች ከተማ ሁለት መስጊዶች ላይ ጥቃት በመፈፀም 49 #ሰላማዊ ዜጎችን ህይዎት በማጥፋት ከተጠረጠሩ ግለሰቦች ውስጥ አንደኛው በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ድርጊቱን የፈፀመው ተጠርጣሪ ብሬንቶን ታራንት የሚባል ሲሆን፥ በዜግነትም አውስትራሊያዊ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የ28 ዓመቱ ብሬንቶን ታራንት በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት የቀረበውም በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ነው ተብሏል።

ፅንፈኛ #ቀኝ_ዘመም_አሸባሪ የተባለው ተጠርጣሪ #ብሬንቶን_ታራንት ፍርድ ቤቱ ያቀረበበትን ክስ በዝምታና በአርምሞ አድምጧል ነው የተባለው ።

ፍርድ ቤቱ የተጠርጣሪውን የይግባኝ መብት በመከልከል ጉዳዩን በድጋሜ ለመመልከት ለፊታችን ሚያዝያ 5 ቀጠሮ ይዟል።

በሽብር ጥቃቱ የተጠረጠሩ ሁለት ተጨማሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፥ ሁለቱም ከዚህ በፊት በምን አይነት የወንጀል ተጠርጥረው  ፍርድ ቤት ቀርበው የማያውቁ መሆኑ ተገልጿል።

የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር #ጃሲንዳ አርደርን ድርጊቱን የሽብር ጥቃት በማለት ያወገዙ ሲሆን፥ በጥቃቱ የተጎዱ ዜጎችን ማንነት  የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርጣሪዎች  ድርጊቱን ለመፈፀም የተጠቀሙበት #መሳሪያ ዘመናዊና የተሻሻለ መሆኑን በመጥቀስ፥ የፀጥታ አካላት ባደረጉት #እርብርብ በፍጥነት በቁጥጥር ስር በማዋል የሚደርሰውን እልቂት ለመታደግ ተችሏል ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia