TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተመራቂዎቹ ጥያቄ....

"ሰላም ፀግሽ ...ዶክተር ሳ__ እንባላለሁ ከመቀለ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 16 ነበር የተመረቅኩት እስካሁን ስራ አልመደቡንም፤ ከዚህ በፊት ከሁለት ሳምንት በኃላ ነበር የሚመድቡት #FOMH አናግረን ነበር እናም ሁሉም ክልል ለሀኪም የሚሆን #በጀት_የለንም ብለዋል፤ ጠብቁ የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን። 7 አመታትን በአድካሚ የትምህርት ስርዓት አልፈን ይህ መሆኑ አሳዝኖኛል።"

ይህን መሰሉ በርካታ ተመሳሳይ መልዕክቶች እየመጡ ናቸው፤ ተመራቂ ዶክተሮቹ መንግስት #አፋጣኝ_ምላሽ እና #መፍትሄ እንዲፈልግላቸው እየጠየቁ ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢንጂነር_ታከለ_ኡማ

በአዲስ አበባ ከተማ #በ2012 የተመደበው #በጀት በአግባቡ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚደረግ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 6ተኛ አመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ማጠቃለያ ጉባኤውን የከተማ አስተዳደሩን የ2012 በጀት በማጽደቅ አጠናቋል፡፡

ምክር ቤቱ በ2012 በጀት አመት ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መድቧል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ያሉባትን ችግሮች ለሚቀርፉ ፤ነዋሪዎቿን በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ለተባሉ እንዲሁም አንገብጋቢ ለተባሉ የልማት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት ለሚችሉ ዘርፎች ልዩ ትኩረት የሰጠ በጀት ምደባ ነው ተብሏል፡፡

በጀት ከመመደብ ባለፈ አጠቃቀሙ ላይ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በጀቱን አዋጪ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የአስፈፃሚ ተቋማትን አቅምና አደረጃጃት የማስተካከል ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የተመደበው በጀት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

Via #AddisTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

" ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " - ዶ/ር ፋና ሀጎስ (የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት)

ከትላንት ምሽት አንስቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መቐለ ዩኒቨርሲቲን የሚመለከቱ መረጃዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

እነዚህ መረጃዎች ፦
- ዩኒቨርሲቲው ወደ መማር ማስተማር ስራው እዲመለስ መወሰኑ፣
- በጦርነቱ አቋርጦ የነበረውን ስራ ከመጪው ሳምንት አንስቶ እንደሚጀምር፣
- በመንግስት በኩል አስፈላጊው #በጀት እንደተለቀቀለት፣
- 24 ሺህ ነባር ተማሪዎችን በቀጣይ 4 ወር ትምህርት እንዲያጠናቅቁ እንደሚያደርግ
- ከመስከረም 2016 ጀምሮ አዲስ ተማሪዎችን እንደሚቀበል የሚገልፁ ናቸው።

ነገር ግን ይህ የተሳሳተ መረጃ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ገልጸዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲም ቢሆን በይፋዊ የፌስቡክ እና የትዊተር አካውንቱ ላይ ምንም አይነት መረጃ አልለጠፈም።

የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፋና ሀጎስ ለ" ኢትዮጵያ ቼክ " መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ ዩኒቨርሲቲው ስራ ለመጀመር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እየሰራ ቢሆንም በዩኒቨርሲቲው ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን የራሱን ጊዜና ሂደት እንደሚወስድ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና " ዩኒቨርሲቲው ሥራውን ይጀምራል ነገር ግን በሚቀጥለው ሳምንት አይደለም ፤ በእርግጥ ይህን ለማድረግ ወራትን ይወስዳል " ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ፋና እስካሁን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለተማሪዎች ጥሪ እንዳላደረገ ገልፀው " እኛ (ዩኒቨርሲቲው ወይም የትምህርት ሚኒስቴር) ተማሪዎቻችንን እንደገና ለመቀበል ዝግጁ ስንሆን ይፋዊ መግለጫ እንሰጣለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

Credit : ethiopiacheck.org

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ህወሓት ከሽብርተኛ ድርጅትነት #ተሰረዘ። የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከሽብርተኛ ድርጅት እንዲሠረዝ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባሄደው ልዩ ስብሰባ ህወሓትን ከሽብርተኛ መዝገብ ለማንሳት በቀረበለት የውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔውን አፅድቋል። #ኤፍቢሲ @tikvahethiopia
#Tigray

" በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ ነው " - ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

ዛሬ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በትግራይ ክልል ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህ መግለጫቸው በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን አሳውቀዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ የፌዴራል መንግስት ህወሓትን ከሽብርተኝነት ፍረጃ መሰረዙ በህወሓት ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዜዳንትነት የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር ወደ ትግበራ ለመግባት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ስለመግለፃቸው ከድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ህወሓት ከሽብርተኝነት መዝገብ ስለመሰረዙ ምን አሉ ?

" በዛሬው ዕለት ህወሓት ከሽብር መዝገብ ተሰርዟል። ስለሆነም ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራው የሚጀምርበት ሁኔታ ተሟልቷል።

#በጀት የማዘጋጀትም ይሁን ሌሎች #ከእስረኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የወንጀል ክሶችን በማንሳት እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ በሁለቱም ወገን በኩል ግኝኑነት ተጀምሯል።

በመሆኑም በበኩላችን በጓድ ጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደራችን ስራዎቹ እንዲሳኩ ለማድረግ ሁሉንም አቅማችንን በማቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እናደርጋለን።

የትግራይ ህዝብም በሁሉም አቅሙ የጊዜያዊ አስተዳደራችን ደግፎ እንዲሰማራ ጥሪ እናቀርባለን። "

ዶ/ር ደብረፅዮን ስለ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምን አሉ ?

" የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፋጠን አሸባሪነት የሚለው ሳይነሳ ቀድመን ነው እየሰራን የመጣነው። ጊዜያዊ መንግስቱን ለማቋቋም በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መምጣታቸውን ሁሉም ሲከታተለው የነበረ ጉዳይ ነው።

ኮሚቴ ከማቋቋም ጀምሮ ሁሉም ጊዜያዊ አስተዳደሩን በተመለከተ አጀንዳው አድርጎ እንዲሰራ በውስጥም በውጭም መድረኮችን በማዘጋጀት ተሰርቷል።

ኮንፈረንስ በማዘጋጀት እና ከኮንፈረስን በኃላ ምርጫዎችን በማካሄድ ሊያካትታቸው የሚገባ ፈፃሚ አካላት እንዲመረጡ ተደርጓል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ #ህወሓት እና #ባይቶና ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የትግራይ ሰራዊት ፣ የትግራይ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚሳተፉ አካላት ተሟልተን ለማዕከላዊ መንግስቱ አሳውቀናል። "

ዶ/ር ደብረፅዮን #ህወሓትን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ድርጅታችን ህወሓት የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ለማረጋገጥ ሰላም የሰፈነባትና ብሔራዊ ክብሯ የተጠበቀች ትግራይን ለመገንባት ሁሉንም አቅሙን በማቀናጀት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እንደሚታገልበት ማረጋገጥ እፈልጋለሁ። ዘላለማዊ ክብር ለጀግኖች ሰማዕታት!! "

@tikvahethiopia
#Tigray

" ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድንገተኛ ህክምና የምንገለገልባቸው አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው " - አቤኔዘር እጸድንግል (ዶ/ር)

የአምቡላንሶች ቁጥር በጦርነቱ ወቅት መመናመንና፣ ደመወዝ ያልተከፈላቸው የጤና ባለሙያዎች ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ፈተና እንደሆነበት የትግራይ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የጤና ቢሮው የድንገተኛ ሕክምና አስተባባሪ አቤኔዘር እጸድንግል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ምን አሉ ?

- የድንገተኛ ሕክምና ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ ችግር ነበር። ከሁሉ በላይ ደግሞ የወላድ እናቶች በቂ አገልግሎት ሲሰጥ አልነበረም። ዋነኛው፣ አንደኛውና ቀደኛ ምክንያቱ የአምቡላንስ እጥረት ችግር ነው። ያለ አምቡላንሶች ድንገተኛ ሕክምና የለም።

- ትግራይ ውስጥ 269 አምቡላንሶች ነበሩ ለቅድመ ሆስፒታል ድገተኛ ሕክምና የምንገለገልባቸው፤ አሁን በእጃችን ያሉን 90 ብቻ ናቸው። በጣም ጥቂት አምቡላንሶች ናቸው የቀሩን።

- በአስተዳደራዊ፣ በነዳጂ፣ በበጀት ችግሮችና በተለያዩ ምክንያቶች 90ዎቹ አምቡላንሶችም ራሱ ለሁሉም አካባቢዎች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

- ኅብረተሰቡ ሊያገኝ የሚገባው አገልግሎት እጅግ በጣም ቀንሶ ነው ያለው። ከዚህ በፊት በአንድ ጊዜ  በኳርተር ኦልሞስት እስከ #500,000 የሚጠጉ ድገተኛ ታካሚዎች ናቸው የነበሩን፤ አሁን በተመሳሳይ ወቅት ወደ ሕክምና ተቋማት የሚመጡት ድንገተኞች #40,000ም አይሞሉም። በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ታካሚው ቀንሷል።

- የጤና ባለሙያዎችም ከቦታ ቦታ መሰደድ በሕክምና አገልግሎት ላይ ፈተና ሆኗል።

- የጤና ባለሞያዎቹ የተሻለ ኑሮ ለመኖር ሲሉ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች ማለትም ወደ መሀል አገር ይሰደዳሉ ፤ ይህን የሚያደርጉት ደግሞ #በጀት ስለሌለ #በቂ ደመወዝ ስለማያገኙ ነው።

* ይህ ሁሉ ተደማምሮ የአገልግሎት ጥራት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅእኖ አድርጓል። ለቀጣይ ይሻሻላል፣ ለመሻሻልም ጊዜያዊው መግሥትም ብዙ እየሰራ ነው።

የአምቡላንሶቹ ቁጥር የቀነሰው በጦርነቱ ወቅት ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው አቤኔዘር (ዶ/ር) ፦

" አዎ በጦርነቱ ወቅት በርከት ያሉ አምቡላንሶች ተወስድልውብናል። በርከት ያሉ ደግሞ ተቃጥለዋል። በእኛ እጅ ያሉት 90 ብቻ ናቸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት ከ80 በላይ የጤና ተቋማት፣ እንዲሁም የሕክምና መሣሪያዎች ላይ ደረሰ የተባለውን ውድመት ተከትሎ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ወዲህ የተሻለ ቢሆንም የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ፈተኝ ችግሮች ማጋጠማቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

መረጃው አዘጋጅቶ ያቀረበው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኦዲት #ኢትዮጵያ (ከ2015 የበጀት ዓመት የፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት) ➡️ የበጀት አጠቃቀም ፦ ኦዲት በተደረጉ መስሪያ ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በስራ ላይ ያዋሉት ሂሳብ ሲነጻጸር ከበጀት በላይ ወጪ የተደረገበት ፣ በርካታ ያልተሰራበት በጀት ተገኝቷል። በ20 መ/ቤቶች በልዩ ልዩ የሂሳብ መደቦች በደንቡ መሰረት #ሳያስፈቅዱ ለእያንዳንዱ የበጀት ኮድ ከተደለደለው በላይ…
#ኦዲት

ያልተሰራበት በጀት !

ገንዘብ ሚኒስቴር እና ጤና ሚኒስቴር የተመደበላቸውን በቢሊዮን የሚቆጠር በጀት ስራ ላይ ካላዋሉ ተቋማት ዋነኞቹ መሆናቸው ተሰምቷል።

በ2015 በጀት መስሪያ ቤቶች የተፈቀደላቸውን በጀት በአግባቡ ስራ ላይ ማዋላቸውንና መጠቀማቸውን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ በሂሳብ ኮዶች ከተደለደለው በጀት ከ10% በላይ #ያልተጠቀሙበትን ብቻ ተወስዶ 101 መስሪያ ቤቶች ፦
° መደበኛ በጀት 5.3 ቢሊዮን
° ከውስጥ ገቢ 207.6 ሚሊዮን
° ከካፒታል ብር 13.7 ቢሊዮን
በድምሩ 19.2 ቢሊዮን ብር #ያልተሰራበት_በጀት ተገኝቷል።

የተደለደለው በጀት ስራ ላይ እንዲውል #ካላደረጉት መስሪያ ቤቶች መካከል ፦

🔴 የገንዘብ ሚኒስቴር 8 ቢሊዮን ብር

🔴 ጤና ሚኒስቴር 1.9 ቢሊዮን ብር

🔴 የግብርና ሚኒስቴር 1.2 ቢሊዮን ብር

🔴 የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን 818.4 ሚሊዮን

🔴 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 727 ሚሊዮን ብር

🔴 ትምህርት ሚኒስቴር 724.2 ሚሊዮን ብር

🔴 የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር 613.6 ሚሊዮን ብር ... ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

#በጀት_ተፈቅዶ እያለ አለመጠቀም የታሰቡ ስራዎች እንዳይሰሩ ፤ መስሪያ ቤቱ አላማውን እንዳያሳካ ሊያደርግ ስለሚችል በበጀት ዝግጅት እና አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲል የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት አሳስቧል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia