TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መከላከያ ሚኒስቴር‼️

የሰራዊቱን አቅም ግንባታን መሰረት ያደረገ እና ሀገራዊ ለውጡን ማራመድ የሚችል ሪፎርም መደረጉን የመከላኪያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው መግለጫም መንግስት እየወሰደ ላለው የለውጥ እርምጃ የበኩሉን እንደሚወጣ ገልጿል።

በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ውስጥ በወንጀል የተጠርጣሩ አመራርና ፈጻሚዎች ጋር በተያያዘ ሰራዊቱን የሚፈርጁ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል።

ተጠርጣሪዎችን የማጋለጥና በቁጥጥር ስር ማዋል ስራ የሚኒስቴሩ አንዱ የሪፎርሙ አካል ሆኖ እየተሰራበት መሆኑም ነው የተመላከተው።

ሰሞኑን በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እንዲሁም በሌሎች ተቋማት ውስጥ በወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋልም ሚኒስቴሩ አብሮ እየሰራ መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኢንዱክትሪኖሽንና ህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀነራል #መሀመድ_ተሰማ ገልጸዋል።

በህዝባዊ ወገንተኝነት ህዝብ በማገልገል ላይ የሚገኘው ሰራዊቱ ለእንዲህ አይነት የወንጀል ተግባር ራሱን መስዋት እስከማድረግ የሚታገል መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ከላይ ከጠተቀሱት ተጠርጣሪዎች ጋር የመፈረጁን ተግባርም እንደሚያወግዝና ግለሰቦቹን #ተጠያቂ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

አሁን ሀገሪቱ ላይ የመጣውን አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት ወደ ተሻለ ምዕራፍ እንዲሻገር ሰራዊቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ይሰራል ብለዋል።

ሀገራዊ ለውጡ በምንም አይነት መንገድ እንዳይቀለበስ የሚያስችል አቋም መፍጠር መቻሉንም የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ለመቆጣጠር በተለያየ ቡድን የተዋቀረ ኮማንድ ፖስት መሰማራቱን እና በአንድ ወር ውስጥ ተጨባጭ ውጤት እንዲያመጡ አቅጣጫ ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

#በከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማት አካባቢ የተፈጠሩ ችግሮች አሁን መረጋጋት ቢታይባቸውም፤ የተዛባ መረጃ #በሚሰራጩ ግለሰብና ቡድኖች ላይ
ህጋዊ #እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቁመዋል።


ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia