TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የተስተካከለ

የHIV/AIDS ስርጭርት መጠን አሁንም አልቀነሰም!

በደቡብ ክልል የኤች አይ ቪ አድስ ስርጭርትን መቀነስ አልተቻለም፡፡ የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ መጠን ከሚታይባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች አንዱ የሆነው የደቡብ ክልል የቫይረሱ ስርጭት መጠን ለመቀነስ የተለያዩ ስራዎችን ቢሰራም የስርጭት መጠኑን መቀነስ እንዳልተቻለ የክልሉ ጤና ቢሮ ተናግሯል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የፕላንና ፕሮግራም ዳሬክተር አቶ ፍስሃ ለዕመንጎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በክልሉ የነበረው የሰላም መደፍረስም ለቫይረሱ ስርጭት በተወሰኑ ቦታዎች ላይ እንዲያንሰራራ ምክንያት ሆኗል ነው ያሉት፡፡

ከ2011 ዓመታዊ ሪፖርት ስንመለከትም የስርጭት መጠኑ 4% ወይም ከመቶ ሰዎች ውስጥ አራቱ ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ወስጥ የወንዶች የስርጭት መጠን 0.17 በመቶ፤ የሴቶች 0.25 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን አቶ ፍስሐ ተናግረዋል፡፡ ምንም አንኳን የክልሉ ኤች አይ ቪ አድስ የስርጭት መጠን 0.4 በመቶ ቢሆንም በክልሉ በሚገኙ እንደንድ አከባቢዎች ላይ የስርጭት መጠኑ ወደ 1.9 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

የክልሉ ርእሰ መዲና በሆነችው #ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ የተለያዩ አካበቢዎች ታላላቅ ፕሮጀክቶች በሚካሄድባቸው ፋብሪካዎችና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የበሽታው ተጋላጭነት #እየሰፋ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

Via #ኢትዮኤፍኤም

🏷ማስተካከያውን ለTIKVAH-ETHIOPIA የሰጡት የክልሉ ጤና ቢሮ የፕላንና ፕሮግራም ዳሬክተር አቶ #ፍስሃ_ለዕመንጎ ናቸው። ለኢትዮኤፍኤምም ማስተካከያውን ይድረስ ተብለናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- በአሜሪካ በ24 ሰዓት ውስጥ 1,169 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎችም ከ245,000 በላይ ደርሰዋል።

- በሩስያ ተጨማሪ 600 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በቤልጂየም ተጨማሪ 132 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል።

- በስፔን በ24 ሰዓት ውስጥ 932 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሞተዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 10,935 ደርሷል። 117,710 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በዓለም ላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1,030, 325 ደርሷል። ከ54,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል፣ ከ219,000 በላይ ሰዎች አገግመዋል።

#የተስተካከለ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia