TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"መረጃው ሀሰት ነው" የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዘዳንትን #ለማስመለጥ የሞከሩ ሰዎች ተያዙ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ሃሰት መሆኑን የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ።

በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገረመው አያሌው እንዳሉት ዘገባው ትክክል እንዳልሆነ ተናግረዋል። አቶ ገረመው የተፈጠረውን ነገር እንዲህ ሲሉ አስረድተዋል፦

"ባሳለፍነው ሰኞ እለት የአዲስ አበባ ፖሊስ በአካባቢው በወንጀል የሚፈልገውን አንድ ተጠርጣሪ ለመያዝ ባደረገው ጥረት በስፍራው ተጠርጣሪው እጅ ላለመስጠት ሽጉጥ ወደ ፖሊሶቹ በመተኮሱ ምክንያት የተፈጠረ ግርግር ነበር እንጂ ከቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዘዳንት መሃመድ ኡመር ጉዳይ ጋር አይገናኝም" ብለዋል።

ምንጭ፦ #ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia