TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የሞተው የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም" የካፕቴን ያሬድ የ11 አመት ጓደኛ
.
.
ከትናንት በስቲያ የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ET 302 ዋና አብራሪ የነበረው ያሬድ ጌታቸውን ለአስራ አንድ ዓመታት የሚያውቀው ኡጋንዳዊ ጓደኛው ሃሰን ካቴንዴ ያሬድ ራግቢ በጣም ይወድ እንደነበር ይናገራል።

ያሬድና ሃሰን የሚተዋወቁት ከዓመታት በፊት ቦሌ አካባቢ በሚገኝ አንድ ህንፃ ፀጉር ቤት ያሬድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ የበራሪ ፅሁፍ ወረቀት ይዞ ሃሰን [ፓይለት ነህ] ብሎ ያሬድን በጠየቀበት አጋጣሚ ነበር።

ያሬድ ኬንያ እንደተወለደ ነግሮት ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ ያወሩት በስዋሂሊ እንደነበር ሃሰን ያስታውሳል።

ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ስፖርት የሚወድ አይነት ሰው የነበረ ሲሆን ለራግቢ ግን ልዩ ፍቅር ነበረው።

ያሬድና ሃሰን አዘውትረው ይገኛኙ የነበረው ግእዝ የሚባል የፈረንሳይ ሬስቶራንት ተገናኝተው ነበር ራግቢ የሚመለከቱት።

መጀመሪያ አካባቢ ሀሰንም መኪና ስላልነበረው አብዛኛውን ጊዜ ያሬድ ያሽከረክር የነበረውን የአባቱን አሮጌ መኪና እየሾፈረ ብዙ ቦታዎች መሄዳቸውንም ሃሰን ያስታውሳል።

ያሬድና ሃሰን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት የነበረ ሲሆን በሎሜ ስካይ አየር መንገድ ስራ ስላገኘ ጓደኛቸው ነበር ያወሩት።

ያሬድ የተወለደው ኬንያ ውስጥ ሲሆን እናቱ ኬንያዊ ሲሆኑ አባቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። የልጅነት ጊዜውን በኬንያ ያሳለፈ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ተከታትሎ የኢትዯጵያ አየር መንገድ አቬሽን ትምህርት ቤትን ተቀላቅሏል።

ሃሰን እንደሚለው ያሬድ ኢትዮጵያዊም ኬንያዊም ማንነቱን ይወድ ነበር። ያሬድ አማርኛ ፣ ስዋሂሊና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን ጥርት አድርጎ ይናገር እንደነበር ሀሰን ገልፆልናል።

"ብዙ ጊዜ ማንነቱን የሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያዊ ነህ ሲሉት [ኢትዮጵያዊና ኬንያዊ]ብሎ ይመልስ ነበር] በማለት ነገሩ አንዳንድ ጊዜም ያሬድን ያስቆጣው እንደነበር ሃሰን ይናገራል።

ሃሰን የአደጋውን ዜና የሰማው ከማህበራዊ ሚዲያ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ጓደኛው በአደጋው ስለመሞቱ ያወቀው ነገር አልነበረም።

"የአደጋውን ዜናና የአውሮፕኑን ሰራተኞች ስም ዝርዝር ስመለከት ያሬድ የሚል ስም ባይም የተለመደ ስም ስለሆነ ሌላ ያሬድ ነው ብዬ አሰብኩ። የኔ ያሬድ ነው ብዬ አላሰብኩም። ቆይቶ ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ሌላ ጓደኛችን ስለ ያሬድ ሰማህ ወይ? ምንድነው ምንትለው? ያሬድ ምን ሆነ ነው ያልኩት። በጣም አሰቃቂ ነው" ብሏል ሃሰን።

ከዚያም ጓደኛው የተከሰከሰው አውሮፕላን አብራሪ የእነሱ ጓደኛ ያሬድ እንደሆነ ሲነግረው ለማመን በጣም እንደከበደውና ሊሆን አይችልምም የሚል ስሜት እንደተሰማው ይናገራል።

"ለማመን የሚከብድ ነገር ነው። መተኛት አልቻልኩም እስካሁን #ድንጋጤ ውስጥ ነኝ"

እሱ ብቻ ሳትሆን የሀሰን እናትም በድንጋጤ ውስጥ እንዳሉ ይናገራል።

ያሬድ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ይመለከት እንደነበር የሚናገረው ሃሰን "በሚገባ #የሰለጠነ አብራሪ ነው። እርግጠኛ ነኝ #እስከመጨረሻዋ ሰዓት ብቃቱን እንደተጠቀመ" በማለት ጓደኛው ያሬድ እንደ ጀግና እንዲታወስ እንደሚፈልግ ይናገራል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia