አ.ሳ.ቴ.ዩ‼️
#የአዳማ_ሳይንስና_ቴክኖሎጂ_ዩኒቨርሲቲ ከጥር 12 እስከ 14 ቀን 2011ዓ.ም. ሁሉም የመደበኛ ቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ፣ ተማሪዎቹና የዪኒቨርሲቲው አስተዳደር እየተወዛገቡ ነው። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት #ለሚ_ጉታ (ዶ/ር)የተላለፈው ውሳኔ ትክክል ነው ሲሉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ተማሪዎቹ ግቢውን ለቀው እንዲወጡ የተወሰነው ውሳኔ ሕጉን መሠረት ያደረገ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ያስረዱ ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ የተወሰደው ዕርምጃ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ከግምት ያላስገባ ነው በማለት #ተቃውመውታል።
ዩኒቨርሲቲው ከጥር 15 ቀን ጀምሮ ለቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የሚሰጠውን ማንኛውንም አገልግሎት እንደሚያቋርጥ ጥር 12:በዩኒቨርሲቲው ሰሌዳ ባወጣው ማስታወቂያ ይፋ አድርጓል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ሴኔት መመሪያ መሠረት አንድ ተማሪ በሴሚስተር መከታተል ያለበት ቢያንስ ሰማንያ በመቶ የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ በሴሚስተሩ ከተቀመጠው የትምህርት ክፍለ ጊዜ 34.4 በመቶ እንዳልተከታተሉ፣ በመመሪያው አንቀጽ 101.2 እና 231.3መሠረት በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ውሳኔ ዕርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ ዕርምጃው መወሰዱን በዩኒቨርሲቲው የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ይፋ የሆነው ማስታወቂያ ይገልጻል፡፡
ይህን ያህል የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሊከታተሉ ያልቻሉት በተደጋጋሚ ለተቃውሞ ሠልፎች በመውጣታቸው እንደነበር ተማሪዎቹ ገልጸው፣ ከወር በፊት በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሦስት ተማሪዎች ሕይወት ማለፉ ለተቃውሞዎቹ መራዘም ምክንያት መሆኑንም አክለዋል፡፡ በዚህ ክስተት ማግሥት ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የአጋማሽ ፈተና እንዲወስዱ ማስታወቂያ ወጥቶ እንደነበር፣ ፈተናውን መውሰድ እንደማይችሉ ቢገልጹም ሰሚ አለማግኘታቸውን ተማሪዎቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የመማር ማስተማር ሒደቱ ተቋርጧል በማለት የተላለፈውን ውሳኔ ተቃውመዋል፡፡
‹‹ይኼንን ፈተና መውሰድ ያልቻልነው በሦስቱ #ወንድሞቻችን ላይ የደረሰው ድንገተኛ ሞት ምክንያት በደረሰብን መሪር #ሐዘንና #ድንጋጤ እንዲሁም ሥርዓተ ቀብር ለመፈፀም ወደ የትውልድ ቦታቸው (አሰላ፣ አለታ ወንዶና ባህር ዳር) በመጓዛችን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ተገቢውን ዝግጅት አላደረግንም፤›› ሲሉ ፈተናው እንዲራዝም የጠየቁበትን ምክንያት ለሪፖርተር ያስረዱ ሲሆን ‹‹ዋናው ጥያቄያችንም የደኅንነት ጥያቄ ነው›› ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የሞቱትን ተማሪዎች በሚመለከት ከአዳማ ፖሊስ መምሪያና ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአስክሬን ምርመራ ውጤት እንደደረሳቸው ወዲያውኑ ለተማሪዎች ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱም ይህ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት ተማሪዎቹ የሁለተኛና የሦስተኛ ዲግሪ ዕድል ይመቻችልን እንዲሁም የሥራ ዕድል ትስስር ከኢንዱስትሪዎች ጋር እንደሚፈጠርልን ቃል ተገብቶልን ነበር በሚል ከሦስት ሳምንት በላይ ትምህርት አቋርጠው እንደነበር ተናግረዋል፡፡ እነዚህ ቀናት ሁሉ ባክነው የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት ዕቅድ ማሳካት ስለማይቻል እንደ አዲስ የመማር ማስተማሩ ሒደት የካቲት 25 እና 26 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲጀመር በሴኔቱ ተወስኗል ብለዋል፡፡ የባከነውን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ለማካካስም አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መልሰን ለመጥራት ርብርብ እያደረግን እንገኛለን ሲሉም አክለዋል፡፡
ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ👆
በማህበራዊ ሚዲያ የታዛቡ መረጃዎች እየወጡ ስለሆነ ይህን እውነታ እወቁልኝ ብሏል ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ፦
1ኛ. ሰሞኑን ከውሃ አቅርቦት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ቅሬታ በዩኒቨርሲቲው ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
2ኛ. የሞተ ተማሪም ሆነ ፀጥታ አስከባሪ የለም
3ኛ.ሶስት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና ም/ፕሬዚዳንቶችን ስማቸውን እየቀያየሩ #በሽጉጥ ሰው መትተዋል የሚል የሀሰት መረጃዎች ተለቀዋል እናም ሀሰት ነው፡፡
4ኛ. በጥይት የተመታ ተማሪም የለም
5ኛ. አንድ ተማሪ መፋሰሻ ( ዲች )ላይ ወድቆ እግሩ ላይ ጉዳት ደርሶበት ወደባህር ዳር ሪፈር ተብሏል፡፡ በጥይት ተመታ እየተባለ የሚወራው መረጃ ሀሰት መሆኑን የህክምና ማስረጃው ያስረዳል፡፡ ጉዳቱ እንደሚያሳየው የአጥንት ስብራት መድረሱን ነው
6ኛ. በትናንትናው ዕለት ከበትር ውጭ ሌላ መከላከያ ያልያዙ 16 የፀጥታ ሀይል ላይ በተወረወረባቸው ድንጋይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሷል፡፡
7ኛ. አንድም ተማሪ የታሰረ የለም
8ኛ. ውሃውም ከትናንት ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ ነው
9ኛ. በአሁኑ ስዓት በግቢው ዙሪያ ካልሆነ በስተቀር አንድም የፀጥታ አካላት በግቢውስጥ የለም፡፡
10ኛ. በዚህን ወቅት ተማሪዎች እራታቸውን እየተመገቡ ነው
11ኛ. የተማሪዎች ህብረት፣ የሰላምፎረም፣ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ ም/ሰብሳቢ አቶ ወልደትንሳኤ መኮንን፣ የክልሉ ልዩ ሀይልና፣ አድማ በታኝ ሀላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ውይይት አካሂደዋል፡፡
12ኛ. በነገው እለትም ከተማሪዎች ጋር ውይይት ይካሄዳል፡፡ ያለው #እውነታ ይሄው ነው፡፡
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 5/2011ዓ.ም

TIKVAH-ETHIOPIA
* አዲስ አበባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ። የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ የካቲት 30 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ያስታወሰው አስተዳደሩ፤ ማንኛውም…
የቤት ኪራይ ጉዳይ . . .
የነዋሪዎች ድምፅ !
በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል።
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን በክትትል ደርሼበታለሁ ፤ ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መጨመር / ተከራይን ማስወጣት እንደማይችል ይወቀው " ካለ በኃላ ነው።
የከተማ አስተዳደሩ መመሪያ " እየተራዘመ " ዛሬ ድረስ የመጣ ሲሆን የእስካሁን ተግባራዊነት ምን ይመስል ነበር ? አሁንስ የቤት ኪራይ ጉዳይ ምን ላይ ነው ? በሚል ለአ/አ ቤተሰቦች ባቀረብነው ጥያቄ ከተከራዮች እንዲሁም ከአከራዎች በሺዎች የሚቆጠሩ መልዕክቶች መጥተዋል።
ከብዙ በጥቂቱ በዚህ አሰባስበን አስቀምጠናል።
ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-23

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
የቤት ኪራይ . . . የነዋሪዎች ድምፅ ! በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከወቅቱ የቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ መሬት ላይ ያለውን #እውነታ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ መልዕክቶችን ልከዋል። የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ የሚገልፁ መልዕክቶችን የላኩት ፤ ከቀናት በፊት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፤ " ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር " ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች…