TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰዎች_ለሰዎች

ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል።

በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት በአርባ ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መመደቡን አስታውቋል።

በዚህም 15 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 900 ሚሊዮን ብር በጀት ጸድቋል። ድርጅቱ ዘንድሮ የተቋቋመበትን 40ኛ ዓመት ያከብራል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰዎች_ለሰዎች ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ መድቧል። በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም እ.ኤ.አ 1981 ዓ.ም የተመሰረተው ሰዎች ለሰዎች (Menschen for Menschen) ድርጅት በ2014/15 በጀት ዓመት በአርባ ዓመት ታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መመደቡን አስታውቋል። በዚህም 15 ሚሊዮን ዩሮ ማለትም 900 ሚሊዮን ብር በጀት…
#ሰዎች_ለሰዎች

ሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት አውሏል።

ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ድርጅት የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ በሆኑት በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም ተቋቁሞ ላለፉት 40 ዓመት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እና ድጋፎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

ድርጅቱ እስካሁን በኢትዮጵያ በቆየባቸው 40 ዓመታት ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ለልማት ማዋሉን ጠቅሷል። በዚህም 6 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ማድረጉን ገልጿል።

በዚህ ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን በጀት መድቦ በአምስት የተለዩ ተግባራት ላይ እንደሚሰራ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የጀርመን ሥራ አመራር ቦርድ ተጠሪ ዶክተር ሰባስቲያን ብራንዲስ ትላንት በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/MFM-02-23