TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ገለፀ። ፋብሪካው በኢትዮጵያና በሞሮኮ መንግሥታት ትብብር በ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይገነባል ነው የተባለው። ፋብሪካውን በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ ለመገንባት የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶችና ግንባታውን የሚከውነውን ኩባንያ ለመምረጥ ጨረታ ወጥቶ የመለየት ስራ እየተሰራ መሆኑን የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ #ተባባል_ውድነህ ለኢዜአ ገልጸዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia