TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የሱዳንን አብዮት የመሩት ሴቶች ናቸው" - የአፍሪካ ህብረት ልዑክ
.
.
የሱዳን አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የመረጧቸውን የካቢኔ አባላት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

እጩዎቹን ለማጥናት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጨማሪ ጊዜ መስጠት በማስፈለጉ እነርሱን ይፋ የማድረጊያው ጊዜ ዘግይቷል ነው የተባለው፡፡

በሱዳን ወታደራዊ እና ተቃዋሚ ቡድኖች በተፈረመው የአገሪቱ ህገ-መንግስት ማሻሻያ አዋጅ መሠረት 40 ከመቶ የሚሆነው የሚኒስትሮች እና የመንግስት የስራ ቦታዎች በሴቶች አንደሚያዙ ነው የተገለፀው፡፡

የአፍሪካ ህብረት የሴቶች የሰላምና ደህንነት ልዩ መልዕክተኛ #ቢኒታ_ዲዩፕ በካርቱም የሚገኙ ሲሆን መንግስት 40 ከመቶ የሚሆኑ ሴቶችን በካቢኔው በሚያካትትበት አግባብ ላይ ከሱዳን ሴት ፖለቲከኞች ጋር ተወያይተዋል፡፡ "አብዮቱን የመሩት ሴቶች ናቸው" ሲሉ መልዕክተኛዋ ለቢቢሲ ኒውስዴይ ተናግረዋል፡፡

ሴቶቹ ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መገናኘታቸውን የገለፁት መዝ ዲዩፕ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

"እሷ አጋር መሆኗን አረጋግጠዋል፤ ስለ ሥርዓተ-ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን ስለማብቃት ያውቃሉ፤ ከወታደራዊው ኃይል ጋር ለመደራደር የሚያስችል ኃይልም ያላቸው ይመስለናል" ብለዋል መዝ ዲዩፕ፡፡

ምንጭ᎓- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia