TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EPRDF #NEBE #ProsperityParty

በቅርቡ ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግ እህትና አጋር ፓርቲዎች በኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የውህደቱ አካል ለሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት ተሰጥቶ የነበረውን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሰርዝና በአዋጅ አንቀጽ 91(4)ሀ መሰረት በውህደት የተመሰረተውን የብልጽግና ፓርቲን እንዲመዘገብና ዕውቅና እንዲያገኝ የሚያስፈልጉ ሰነዶች ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስረከቡን ፓርቲው ገልጿል።

(EPRDF Official)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty #TPLF

"ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያቋቋሙት ብልፅግና የሚባለው ፓርቲ የውሸት ፓርቲ ነው፡፡ እስካሁንዋ ደቂቃ በህግ የሚታወቅ ብልፅግና የሚባል ፓርቲ የለም፡፡ ግን በየቦታው የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ የሚባሉ ሰዎች እየሰማን ነው፡፡ እንደ ትግራይ ሳወራ የትግራይ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የሚነካ ውሳኔ ከአራት ኪሎ ይምጣ ፣ ከዋይት ሃውስ ይምጣ ፣ ከባንኪንግሃም ፓላስ ይምጣ ፣ ከዌስት ሚኒስትር አብይ ይምጣ ማንም ሰው ሊቀበለው አይችልም፡፡ እኔ ይሄንን አልቀበልም ፤ እኔ በማውቀው ልክ ይህንን የሚቀበል የትግራት ተወላጅ የለም፡፡ እኔ እንደማውቀው ይህንን የሚቀበል የአማራ ተወላጅ አለ አልልም ፤ መኖርም የለበትም፡፡ ከአራት ኪሎ በሚመጣው ትእዛዝ ራስን በራስ የማስተዳደር መብትህ ለጊዜው ታጥፈዋል የሚባል ኦሮሞ ይኖራል ብየ አላምንም ፤ የሚኖርም አይመስለኝም፡፡”- አቶ ጌታቸው ረዳ (የህወሓት/ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ አባል)

#TMH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል ነባራዊ ሁኔታ እስካሁን ትርጉም ባለው መልኩ እንቅስቃሴ እንዳልተደረገ የገለጹት አቶ አወሉ፤ ነገር ግን አሁን በአዲስ መልክ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ተቋቁሞ ሥራውን እየሰራ ስለሆነ በቅርብ ጊዜ በክልል፣ በዞኖች፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ እንቅስቃሴ ይደረጋል ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#ProsperityParty ብልጽግና ፓርቲ [Prospertity Party] በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ ገለጹ፡፡ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አወሉ አብዲ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ…
#TPLF #ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቢሮ እንደሚከፍት ያስታወቀ ቢሆንም የክልሉ መንግስት ግን የሚያዉቀዉ ነገር እንደሌለ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸዉ ረዳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

ብልጽግና ፓርቲ ለትግራይ ክልል የተሾሙ ግለሰቦች እንዳሉ ሰምቻለሁ እነማን እንደተሾሙ ግን ወደ ፊት የሚሆነዉን የምናይ ይሆናል፡

ብልጽግና በትግራይ ክልል ብዙ ደጋፊ አለው ብዬ አላምንም፤ ማንኛዉም ፓርቲ ህጋዊ እስከሆነ ድረስ ግን በትግራይ ክልል የመንቀሳቀስ መብት አለዉ።

#EthioFM #አባቱመረቀ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ግዙፍ የተባለ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እንደሚያካሂድ ዋዜማ ራዲዮ ዘገበ። በቅዳሜው መርሀ ግብር ላይ እንዲሳተፉም በርካቶች ጥሪ ተደርጎላቸዋል ነው የተባለው። ባለሀብቶች፣ ምሁራንና የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች እንደሚገኙም ተነግሯል።

የቅዳሜው የሚሊኒየም አዳራሽ መርሀ ግብር “የብልጽግና ፓርቲ የማጠናከሪያ ድጋፍ ማሰባሰቢያ የመጀመርያው ምእራፍ ማብሰሪያ የእራት ግብዣ” የሚል ስያሜ አለው ነው የተባለው። በቅዳሜው የእራት ግብዣ ላይ ለብልጽግና ፓርቲ በይፋ ገንዘብ የማሰባሰብ መርሀ ግብር የማከናወን እቅድ ይኑር አይኑ መረጃ ማግኘት እንዳልተቻለ ሬድዮ ጣቢው ጨምሮ ገልጿል።

ለምርጫ ዘመቻ የፖለቲካ ስራ ገንዘብን በተለያየ መልኩ በድጋፍ ማሰባሰብ በሌሎች ባደጉ ሀገራት የተለመደ ቢሆንም አሁን በብልጽግና ፓርቲ በኩል እየተደረጉ ያሉ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎች ግን በተቋማትና ግለሰቦች ላይ ጫና በመፍጠር የተከናወኑ ናቸው በሚል ከዚህ ከዚያም ወቀሳዎች ይደመጣሉ።

ምንጭ፦ ዋዜማ ሬድዮ ጣቢያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መመደባቸው ተገለፀ።

የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አወሉ አብዲ እና የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም አቶ ነብዩ ስሁል ሚካኤል የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ምደባ መካሄዱንም ነው የገለፁት።

በቀጣይም የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት በአዲስ አበባ፣ በመቐለ እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዞኖች እና ወረዳዎች እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ProsperityParty

ዛሬ የገዢው ፓርቲ ብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፓርቲ ኃላፊነታቸው መሸኘታቸው ተገልጿል።

የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፤ " የአመራር የመተካካት መርኅን እና የአሠራር ሥርዓት በመከተል አቶ ደመቀን በክብር ተሸኝተዋል " ሲል ገልጿል።

አቶ ደመቀን መኮንንን በመተካት የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልጽግና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

አቶ ደመቀ ከፓርቲው አመራርነታቸው መሰናበት በአገሪቱን መንግሥት ውስጥ ይዘው ከሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቦታን ሊለቁ እንደሚችሉ አመላካች ሊሆን ይችላል ተብሏል።

አቶ ደመቀ የም/ጠቅላይ ሚኒስትርነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታንም ይለቃሉ የሚሉ መረጃዎች ያሉ ቢሆንም እስካሁን የታወቀው በይፋ ከፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዜዳንትነት ቦታ መሸኘታቸው ነው።

አቶ ደመቀ መኮንን ለረጅም ዓመታት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን በመተካት ነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ቦታ ደርበው የያዙት።

በቀድሞው ኢህአዴግ እና በአሁኑ ብልጽግና ፓርቲው ውስጥ ቁልፍ ሥልጣንን ይዘው የቆዩት አቶ ደመቀ ፤ በብልፅግና ፓርቲ ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች መካከል አንዱ ነበሩ።

@tikvahethiopia
#ProsperityParty #TPLF

ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል።

ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል።

ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል።

" ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ፦

- " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

- ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

- የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል።

- የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

#ProsperityParty #TPLF

@tikvahethiopia