TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጎንደር

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት ጎንደር ከተማ ገቡ፡፡ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ #ተመስገን_ጥሩነህ ጋር በአፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ አቀባብል ተደርጎላቸዋል፡፡ በቆይታቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የችግኝ ተከላና የሚሳተፉ ሲሆን የፋሲለደስ ግንብንም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጎንደር_አረንጓዴ_አሻራ

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ልዑካን ቡድን አባላት የአረንጓዴ አሻራ ቀንን ምክንያት በማድረግ በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ ችግኝ ተከሉ።
#ጎንደር

"የኃይሌ ሪዞርት-ጎንደር ማኔጀመንት እና ሰራተኞች በጎንደር ገነት ተራራ ላይ የ #አረንጓዴአሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደናል!"
#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

"የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል #ሠራተኞች ዛሬ እንዲህ ነበር በችግኝ ተከላው ላይ የተሳተፉት፡፡እናመሰግናለን፡፡"
#ጎንደር

የኢፌዴሪ ኘሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶችን ጎበኙ። ፕሬዘዳንቷ የፋሲል ግንብን፣ የደብረ ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን አና ጥምቀተ ባህሩን ጎብኝተዋል። በተጨማሪም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህሙማን የተመላላሽ ህክምና አዲሱን የእናቶች እና ህፃናት ማዕከልን ጎብኝተዋል። በጎብኝቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሻሸመኔ
#ሀዋሳ
#ነቀምት
#አሰላ
#አዲስአበባ
#ሽሬ
#ደብረብርሃን
#ወላይታሶዶ
#አርባምንጭ
#ጅግጅጋ
#አዳማ
#ድሬዳዋ
#ባህርዳር
#መቐለ
#ሀረር
#ጎንደር

ከሌሎች በርካታ ከተሞች ከሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች የSAT ውጤት ያልጠበቁት እንደሆነ በመግለፅ ቅሬታቸው እያሰሙ ይገኛሉ። የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበትም ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ SELAMAWIT TEKLAY በዘንድሮው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 618 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#618 #ጎንደር #ፋሲለደስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ⬆️

5ኛ የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ እንደቀጠለ ይገኛል። በቅንድል ኢትዮጵያ አማካኝነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይለው የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ጥሩ በሚባል ደረጃ እየሄደ ነው።

#ጎንደር
#ባህርዳር
#አዶላ
#ዲላ የሚገኙና በሌሎችም የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙትን አስተባባሪዎች ስልክ እንጠቁማለን። ውድ የቤተሰባችን አባላት ቤት ካሉት መፅሃፍቶቻችሁ አንዱን ለሀገራችሁ አበርክቱ!
#GONDAR

የጸጥታ ኃይሉ #ጎንደር ላይ በአጠራጣሪ እንቅስቃሴ ላይ አገኘኋቸው ያላቸውን 38 ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታወቋል። ከተያዙት ወጣቶች መካከል አንድ ግለሰብ አራት መታዎቂያዎችን፣ ሌላ አንድ ወጣት ደግሞ 7 የውጭ ሀገር ሲም ካርዶችን እንደያዘ አረጋግጫለሁ ብሏል የከተማ አስተዳድሩ የሰላምና ደኅንነት መምሪያ፡፡

‘ሰሊጥ ለመሰብሰብ ሥራ እየሔድን ነው’ በማለት በጉዞ ላይ የነበሩ ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተነሱ 38 ወጣቶች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ትናንት ጥቅምት 10/2012 ከቀኑ 10፡00 ጎንደር ከተማ ቀበሌ 15 ላይ በጸጥታ አካላትና በወጣቶች ትብብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-22-2

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዛሬ ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ወደ #ጎንደር ተቋርጦ የነበረውን የበረራ አገልግሎት እንደገና ይጀምራል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።

#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።

#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ

የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።

#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ

የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።

አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ

ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።

ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#GONDAR የጥምቀት በዓል እጅግ በድምቀት የሚከበርባት ጎንደር ከተማ ዝግጅቷ በማጠናቀው እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነው። በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰጪዎች ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል እና በክብር ለማስተናገድ ዝግጅታችንን ሁሉ አጠናቀናል ብለዋል። ዘንድሮ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። የከተማ አስተዳደሩ " የጥምቀት…
#ጎንደር

ከቀናት በኃላ ለሚከበረው የጥምቅት በዓል እንግዶች ከወዲሁ ወደ ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ መግባት መጀመራቸው ተሰምቷል።

የጎንደር ከተማ እና አካባቢው ሆቴሎች፣ ሎጂዎችና ሪዞርቶች ማኅበር ፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት በኮረና ቫይረስና በጦርነት ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ አሁን ላይ መልሶ እየተነቃቃ መሆኑን አመልክቷል።

ጎንደር እንግዶቿን በምቾት ተቀብላ ለማስተናገድ ሆቴሎቿ በቂ ዝግጅት እንዳደረጉም ተገልጿል።

ካለው ሀገራዊ የሰላም ሁኔታ ጋር ተያይዞ ለዘንድሮው ጥምቀት በዓል ወደ ጎንደር የሚገባው እንግዳ ቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል።

ይህ ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የማረፊያ እጥረት ለመቅረፍ ታሳቢ ያደረጉ የመፍትሔ ተግባራትን በከተማው ሆቴሌች እየተሰራ ስለመሆኑ ተገልጿል።

በሆቴሎች ደረጃቸውን የጠበቁ ተጨማሪ የድንኳን መጠለያ አገልግሎት ለመስጠት እንደታሰበ ከአሚኮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
የካንሰር ህክምና . . . #በኢትዮጵያ

#ጥቁር_አንበሳ

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፤ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት ወረፋ የሚጠብቁ መኖራቸውን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ክፍል ኃላፊ ኤዶም ሰይፉ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" የተለያዩ የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠብቁ ከ2013 መጨረሻ፣ 2014 ዓ.ም. እና 2015 ዓ.ም. ወረፋ ያልደረሳቸው አሉ፡፡

ይሁን እንጂ በየዕለቱ የሚመጡ ድንገተኛ የካንሰር ታካሚዎች በመኖራቸው በቅድሚያ ለእነዚህ ታካሚዎች አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል።

በሆስፒታሉ ቆይተው መታከም ይችላሉ ተብለው የተለዩት ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ሕክምና ለማግኘት እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ ጥረት እየተደረገ ነው።

ለዚህ ወረፋ መብዛት ዋነኛ ምክንያት ብለው ያቀረቡት በሆስፒታሉ የሚገኘው መሣሪያ #አንድ ብቻ መሆኑን ነው።

በዚህ ዓመት ብቻ በተደረገው ማጣራት የካንሰር ሕክምና ለማግኘት የሚጠበባቁ 5,000 ታካሚዎች ሲኖሩ፣ በማዕከሉ በቀን በአማካይ ከ300 በላይ ታካሚዎች ይስተናገዳሉ።

ከእነዚህ የካንሰር ታካሚዎች መካከል 70 በመቶ የጨረር ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሲሆኑ፣ ኬሞ ቴራፒ የሚያስፈልጋቸው የታካሚዎች ቁጥር ቀላል የሚባል አይደለም ።

በማዕከሉ አገልግሎት ለማግኘት የ2014 ዓ.ም. እና በ2015 ዓ.ም. ሕክምና ለማግኘት የተመዘገቡ ደግሞ ከ10,000 በላይ ናቸው። "

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ_ስፔሻላይዝድ_ሆስፒታል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክሊኒካል ኢንኮሎጂስት ዶ/ር አማረ የሺጥላ ምን አሉ ?

"  በሆስፒታሉ የሚሰጠው የካንሰር ሕክምና ኬሞ ቴራፒና ቀዶ ጥገና ነው።

የጨረር ሕክምና ለመጀመር የማሽን ተከላ ላይ እንገኛለን። 60 በመቶ የሚሆነው የካንሰር ታካሚ እስኪጠናቀቅ እየተጠባበቁ ነው።

በሆስፒታሉ ካንሰር ሕሙማን ሕክምና አንዱ የሆነው ኬሞ ቴራፒ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ በዛ ከተባለ ከሳምንት አይበልጥም።

ይሁን እንጂ ለካንሰር ሕሙማን የሚሰጠው የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመጠባበቅ ከስድስት ወራት እስከ አንድ ዓመት ያስፈልጋል። "

#በሐሮሚያ_ዩኒቨርሲቲ_ሕይወት_ፋና_ሆስፒታል

በሐሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ሕይወት ፋና ሆስፒታል በካንሰር ሕክምና ረዳት ፕሮፌሰር ሚካኤል ሻውል (ዶ/ር) ምን አሉ ?

" በሆስፒታሉ የኬሞ ቴራፒና የጨረር ሕክምና ለካንሰር ሕሙማን እየተሰጠ ነው።

የጨረር ሕክምና ከተጀመረ ስድስት ወራት አስቆጥሯል ፤ የታካሚዎች መጠነ መጠበቅ ከሦስት ወራት አይበልጥም።

በሆስፒታሉ በዓመት እስከ 6000 የካንሰር ታካሚዎች ሕክምና ያገኛሉ። በተለይ ደግሞ ጨረር ሕክምና ከተጀመረ በኋላ የታካሚዎች ቁጥር እየጨመረ ነው።

ሆስፒታሉ በምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ቅርብ ጊዜያት ብቸኛው የካንሰር ሕክምና መስጫ በመሆኑ ከሶማሌላንድና ከሌሎች አገሮች እየመጡ አገልግሎት የሚያገኙ ነበሩ። "

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል። - ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን…
#ጎንደር

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የገቡ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የትላንት ሰዓት እና የዛሬውን ፈተና እንዳልወሰዱ የትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ፤ በማራኪ ፣ ቴዎድሮስ ፣ ፋሲል ግቢ ለፈተና የገቡ ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ፈተናቸውን ሳይወስዱ እንደቀሩ አመልክቷል።

በዕለቱ በነበረ የተኩስ ልውውጥም 1 ፈታኝ / የፈተና አስፈፃሚ እና 2 የፌዴራል ፖሊስ አባላት ሲገደሉ ፤ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል ደግሞ ቆስሏል።

በአጠቃላይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ችግር ፈተናቸውን መፈተን ያልቻሉ 16 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ በሚመቻችላቸው መርሐ ግብር ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ጎንደር ካጋጠመው ችግር ውጭ በሌሎች የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም ፈተና ተሰጥቶ መጠናቀቁን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነገ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ? - ፈተናው ከኩረጃና ስርቆት በፀዳ መልኩ ተሰጥቶ ተጠናቋል። - ፈተናውን ለመፈተን በአጠቃላይ 868 ሺህ 74 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ ከነዚህም ውስጥ 840 ሺህ 859 ፈተናውን…
#Update

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አንድ መምህሩ ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አስፈታኝነት ተመድበው ባቀኑበት #ጎንደር ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጓል።

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት መምህር የነበሩት ታደሰ አበበ ገብረሀና (ረ/ፕ/ር) ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈታኝነት ተመድበው በሔዱበት ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ/ም ህይወታቸው ማለፉን ተቋሙ አመልክቷል።

በ38 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት መምህር ታደሰ አበበ፤ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 2009 - 2013 ዓ.ም በእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነ-ጽሁፍ ትምህርት ክፍል በመምህርነትና በኃላፊነት ያገለገሉ ሲሆን ከየካቲት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ምክትል ዲን በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡

መምህር ታደሰ አበበ ባለትዳርና የ3 ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gondar የጎንደር ግጭት ከተማዋን አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደጣላት አንድ በጎንደር ሆስፒታል የሚሰራ የቲክቫህ የቤተሰብ አባል የሆነ የሕክምና ዶክተር አሳውቆናል። የጎንደር ሁኔታ #እጅግ_አስከፊ እንደነበር የገለፀልን የህክምና ዶክተሩ " በግጭቱ ምክንያት የመጨረሻ ኢሰብአዊ ድርጊት ተፈጽሟል ፤ ሰላማዊ ዜጎች እዚህም እዚያም ተገድለዋል " ሲል አስረድቷል። በሆስፒታሉ ውሃ ፣ ኦክስጂን ፣ እንዲሁም ደግሞ…
#GONDAR

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የህክምና ዶክተር የሆነው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል በከተማው ስላለው ሁኔታ መረጃዎችን አጋርቶናል።

- ታማሚዎች በኦክስጂን እና ደም እጥረት እየሞቱ መሆኑን ገልጿል።

- ለአምቡላንስ ጨምር ምንምአይነት የትራንስፖርት አማራጭ እንደሌለ ፤ ታማሚዎች በሰው ኃይል በሸክም ወደ ሆስፒታሉ እየመጡ መሆኑን አስረድቷል።

- ወደ 20 (ሰላማዊ ሰዎች) ወደ ሆስፒታሉ ከደረሱ በኃላ እንደሞቱ እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች ተጎድተው ሆስፒታል እንደሚጡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ ሰላማዊ ሰዎች መሆናቸውን ገልጿል።

- በርከታ ሰዎች በቤታቸው ሞተው፣ ቀብራቸውም በአካባቢያቸው በተለይም በቀበሌ 4 ፣ 12 ፣ 11 እና 18 መፈፀሙን አመልክቷል።

- ባለፈው ሰኞ በነበረ ግጭት ከሆስፒታሉ የተወሰኑ ህፃዎች በመሳሪያ ቢመቱትም የተጎዳ ሰው ግን እንዳልነበር ገልጿል።

- ሆስፒታሉ ምግብ እንዲሁም መድሃኒት እያለቀበት መሆኑን አመልክቷል።

ዛሬ ጎንደር እንዴት ናት ?

አሁን ላይ በጎንደር ከተማ ከየትኛውም አቅጣጫ የተኩስ ድምፅ እየተሰማ አይደለም። ጥዋት ላይ ለጥቂት ሰከንድ ፒያሳ እና ቀበሌ 18 አካባቢ ተኩስ ተሰምቶ ነበር።

ከትላንት ማታ አንስቶ ዛሬም ጥዋት በከተማው አብዛኛው ክፍል ላይ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ያለ ሲሆን ሰራዊቱ በሆስፒታሉ አካባቢም መኖሩን ይኸው ዶክተር ገልጿል።

የህክምና ዶክተሩ ከምንም በላይ በሆስፒታል ያለው የኦክስጅን ፣ የደም እጥረት እንዲሁም የአምቡላንስ ትራንስፖርት ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

ጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ #ጎንደር ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የሆነ ግጭት ካስተናገዱ የአማራ ክልል ከተሞች መካከል አንዷ ናት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባህርዳር #ጎንደር

ባህር ዳር ከተማ ከትላንት ለሊት ጀምሮ ዝምታ ሰፍኖባት እንደምትገኝና ዛሬ የሟቾች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም እንደነበር ነዋሪዎቿ ተናግሩ።

ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ስትናጥ የነበረችው ባህር ዳር ከተማ ከለሊት ጀምሮ ፀጥ ብላ መዋሏን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ በባህር ዳር በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መዋሉን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ትላንት በቀበሌ 13 ፣ 14 እና 16 በነበረ ውጊያ በርካታ ሰዎች #መሞታቸው እና #መጎዳታቸው ተነግሯል። እነዚሁ ሟቾች ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በተለያዩ ስፍራዎች ሲፈፀም ውሏል።

ነዋሪዎቹ በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈው አብዛኞቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች መሆናቸውን ገልጽዋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ያነጋገራቸው ሁለት ዶክተሮች በውጊያው ሰላማዊ ሰዎች ስለመገደላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የባህር ዳር ነዋሪዎች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ሬድዮ በሰጡት ቃል ከከተማው ማረሚያ ቤት 2 ሺህ የሚጠጉ ታራሚዎች ሲወጡ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዳግሞ ዛሬ ከሰሞኑን የተሻለ መረጋጋት እንዳለ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የመንግሥት ጦር በከተማው ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የተደረደሩ ድንጋዮችን ሲያነሱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia