ድረስ ሁናቸው እንዴት ህይወቱ አለፈ?
ድረስ ዩናቸው የሚባል ዘንድሮ ከኮተቤ በአስተማሪነት የተመረቀ አይነስውር ባሳለፍነው ሰኞ ለአንድ ጉዳይ አቃቂ ክፍለ ከተማ ይሄዳል። ድረስ የሄደበትን ጉዳይ ጨርሶ ድካም ስለተጫጫነው ሊፍት በመጠቀም ከነበረበት ፎቅ ለመውረድ #አሳንሰሩን ያዘዋል አሳንሰሩ ከመጣለት በኋላ ግን የሆነው ሌላ ነው፤ ወደ አሳንሰሩ በሚገባበት ወቅት አሳንሰሩ #ወለል አልነበረውም ወጣቱ አይነስውር ድረስም ከነበረበት ፎቅ በመውደቅ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርኩት ከድረስ ጋር አብሮት የተማረ እንዲሁም በቅርበት የሚያውቀው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ይህን ብሏል፦
"መንግስት ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት ይስጥ ለአካል ጉዳተኞች፤...ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት ተሰጠ የሚባለው #በወሬ እንጂ በተግባር የለም። ይሄ እንደ አብነት ተጠቀሰ እንጂ ብዙ ባለጉዳዮች አሉ ጉርጓድ ውስጥ እየገቡ ህይወታቸው ያለፈ፤ የዚህ ግን አካሄዱ በጣም ያሳዝናል። በመንግስት ቢሮ መሆኑ ደግሞ የበለጠ ያሳዝናል፡ ለግሉስ ምን አይነት መልዕክት ነው የምታስተላልፈው። ይሄ አደጋ የደረሰው በመንግስት መስርያ ቤት ቸልተኝነት ነው። የመንግስት ቢሮ እንደዚህ አይነት ሊፍት የሚያስገጥም ከሆነ ለግሉ ቢሮ ምን ብለህ ነው አርዓያ የምትሆነው? መንግስት መጀመሪያ ስራውን ይስራ። ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት ይስጥ። መንግስት በዚህ ዙሪያ/በደረስ ሞት/ ምንም ያለው ነገር የለም፡ ቤተሰቦቹን ሊያናግር ሊያወያይ ይገባል፤ ካሳም ሊከፍላቸው ይገባል።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia