የመማሪያ መፃህፍትን ለግሱ!
√#አዲስ_አበባ
👉ዮናስ ገ/መስቀል
0970514616
👉መባ
0924140293
√#ሰበታ
👉ያሬድ ለማ
0932540523
👉ያብስራ ካሳ
0921421493
√#መቐለ
👉ኤርሚያስ ደጀኔ
0912178520
👉ፊራኦል መስፍን
0923602445
√#ራያ_ቆቦ
👉ሉላይ
+251949256094
√#ድሬዳዋ
👉መሃሪ
0915034762
√#አዳማ
👉ሰላም
0949377735
5ኛው አመት የTIKVAH-ETHIOPIA የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#update ኢትዮጵያ ግብፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ይዛ የመጣችውን አዲስ ሃሳብ እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡ ግበፅ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተለያዩ ሃሳቦችን ይዛ ብቅ ማለቷን ተከትሎ፣ የኢትዮጲያ መንግስት ቀደም ሲል ከተቀመጠዉ መርህና አሰራር ውጪ በግብፅ የሚነሱ ሃሳቦች ተቀባይነት የላቸውም ብሏል፡፡
ግብፅ ከ ሰሞኑ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት በሰባት አመታት ውስጥ ይሁንልኝ ብላለች፡፡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ኢትዮጲያ ያላት አቋም በ2012 የዉሃ ሙሌቱ ይጠናቀቃል የሚል ነዉ፡፡ ከምንከተለዉ መመሪያና የተፋሰስ ሃገራቱ ካስቀመጧቸው የመደራደሪያ ነጥቦች ውጪ በግብጽ የሚነዳዉ ሃሳብ ተቀባይነት እንደሌለዉም አስታውቀዋል፡፡
ሱዳንን ጨምሮ ሶስቱ ሃገራት በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ የሚያካሂዱትን የሶስትዮሽ ድርድር በሱዳን የፓለቲካ ቀውስ ምክንያት መስተጓጎሉን ጠቅሰዉ፣በቀጣይም ድርድሩ የሶስቱንም ሃገራት የጋራ ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ውጪ ከሱዳንም ሆነ ከግብፅ የሚነሱ ምክንያታዊ ያልሆኑ አሉታዊ መግለጫዎች በኢትዮጵያ በኩል ተቀባይነት እንደማይኖራቸዉ አቶ ነብያት ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቀጣዮቹ 5 አመታት የሚያገለግል ስትራቴጅካዊ ረቂቅ እቅድ ማዘጋጀቱን ገልጿል። የከፍተኛ ትምህርት አማካሪ ምክር ቤት ሁለተኛው ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩም በጉባኤው ላይ ለቀጣዮቹ 5 አመታት የሚያገለግለውን እና ያዘጋጀውን ስትራቴጅካዊ ረቂቅ እቅድ አስተዋውቋል።
በቀረበው ረቂቅ እቅድ ላይም በጉባኤው ባለድርሻ አካላት እየመከሩበት ይገኛል። እቅዱ የከፍተኛ እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ያሉባቸውን ክፍተቶች ለማስተካከል የሚያግዝ ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈም አዳዲስ አሰራሮችን ለመዘርጋት እንደሚያግዝም ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።
ረቂቅ እቅዱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በቅንጅት መስራት ላይ ያሉባቸውን ችግሮች በምን መልኩ መፍታት ይገባል የሚለውን ተመልክቷልም ነው የተባለው፡፡ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ዙሪያ የሚታየውን የጥራትና ፍትሃዊነት ጥያቄዎችን ለማሻሻል እንደሚረዳም ታምኖበታል።
Via #FBC

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በከፍተኛ ዲፕሎማቶቻቸው የሚመራ የጋራ ኮሚቴ ለመመስረት ተስማሙ፡፡ ሁለቱ አገራት ከዚህ ስምምነት ላይ የደረሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጄኢን ጋር ዛሬ በሶል በተገናኙበት ወቅት፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ሃይ” ባይ የሚሻው የዋጋ ንረት!
አሁን ያለው የገበያና ግብይት ሁኔታ ማነጋገር ከጀመረ ሰንብቷል። በተለይም በከተሞች ያለው የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ የሸማቹን አናት እያዞረ፤ አቅሙን እያሽመደመደ፣ ኑሮውን አደጋ ላይ እየጣለና ህልውናውን እየተፈታተነው ይገኛል።
የሰሞኑንም ሆነ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ሲከሰቱ የነበሩትን ያልተገቡ የዋጋ ጭማሪዎችንና ንረትን ቀረብ ብሎ ለተመለከተ በአንድ የገበያ ስርአት ውስጥ አበይት የሆኑ ባህርያትን – መንግስት፣ ህዝብና ነጋዴው – እየተናበቡ ሳይሆን እየተገፋፉ፣ እየተቀራረቡ ሳይሆን እየተራራቁ መሆናቸውን፤ ይህም የገበያ ስርአት አልበኝነትን ሳይፈጥር እንዳልቀረ መረዳቱ የግድ ነው። ለዚህ ደግሞ የግብይት ስርአቱ ሙሉ ለሙሉ በአንድ ወገን ተፅእኖ ስር መውደቁን ያሳያል።
የዚህ ስርአት አልበኝነት መንሰራፋት ለህገ ወጦች በተለይም ለደላላው ክፍል ሰፊ የመፈንጫ ሜዳን ያመቻቸ፣ ለሰው ሰራሽ የዋጋ ጭማሪ መልካም አጋጣሚን የፈጠረ ሲሆን የእነዚህ ድምር ውጤትም ሸማቹን እያማረረው ይገኛል። በዚህ ላይ የገንዘብ ግሽበት፣ የገበያ አሻጥር፣ ድህነት ወዘተ ሲጨመርበት ደግሞ ጉዳዩ ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።
የመጫወቻ ካርዱን “ነፃ ገበያ” ካደረገው የአገራችን የንግድና ግብይት ስርአት የታሪፍ ህዳግም ሆነ የምርቶችና የአገልግሎቶች የመናሻ ዋጋ የሌለው መሆኑ የመግዛት- መሸጡን ሂደት ቅጣንባሩን አጥፍቶታል። ይህም ለህገ- ወጥ ደላላውና በገንዘብና ንግዱ ዘርፍ የበላይነትን ለያዙ ጥቂት ወገኖች ምቹ የመፈንጫ ሜዳን ፈጥሮላቸዋል። ለሸማቹ ደግሞ በተቃራኒው።
#አዲስ_ዘመን
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-26

አሳዛኝ ዜና!
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት አካባቢ 12 ሰዎች ተገደሉ!
በሰሜናዊ ኬንያ ማርሳቤት ግዛት 12 ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ታወቀ። ፈረንሳይ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው በአካባው በተቃጡ ኹለት ጥቃቶች 12 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከሟቾችም ውስጥ ሦስቱ ሕፃናት እንደሆኑ ገልጿል። ጥቃቱን በሚመለከት የኬንያ ፖሊስ ጥቃት አድራሾች የኢትዮጵያ የቦረና ጎሳዎች ናቸው ሲል አስታውቋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከግድያውም ባለፈ 5መቶ ቀንድ ከብቶች እንዲሁም 1 ሽሕ ፍየሎችም መወሰዳቸውን ጨምሮ ገልጿል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ
@tsegabwolde @gikvahethiopia

በሀዋሳ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ እገዳ ተነስቷል!
ባለፈው ወር በሀዋሳ ከተማ ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በኮማንድ ፖስቱ ተጥሎ የነበረው የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ እገዳ ከዛሬ ጀምሮ ተነስቷል። ነገር ግን ሞተር ማሽከርከር የሚቻለው ከጥዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ብቻ መሆኑ ነው የተገለፀው። ከምሽቱ 12 ሰዓት በኃላ ከፀጥታ አካላት ውጪ የትኛውም አካል ሞተር ሳይክል ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም ተብሏል።
Via #SRTA/የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን/

#update የኢትዮጵያ ሲምካርድ ከአገር ውጪ በዝቅተኛ ክፍያ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ። ድርጅቱ በሮሚንግ አገልግሎት ላይ የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን ገልጿል። የሮሞንግ አግልግሎት ኢትዮጵያዊያን ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ለስራ፣ ለትምህርት እንዲሁም ለተለያዩ ጉዳዮች ከሀገር ሲወጡ ሲም ካርድ መቀየር ሳያስፈልጋቸው በሄዱበት ሀገር በዓለም አቀፍ ደረጃ መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ ከዚህ በፊትም የነበረ ቢሆንም ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህ ቀደም ደንበኞች ይህ አገልግሎት ውድ ነው በሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱበት ነበር። ኢትዮ ቴሌኮም ይሄነን ቅሬታ ለመፍታት ከተለያዩ ሀገራት ኦፕሬተሮች ጋር በመነጋገር የክፍያ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰላም፣ልማትና ዴሞክራሲ የሰፈነባትን ሃገር ለመገንባት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል"—ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
ሰላም የሰፈነባት ፣ ህዝቦቿ እንደታሪካቸው በመከባበር የሚኖሩባትን ሀገር ለመገንባት ሁላችንም የድርሻችንን ማበርከት ይጠበቅብናል ሲሉ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለጹ።
ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ ይህን የተናገሩት “ህገ-መንግስትና ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓትን ማዳን ለዴሞክራሲያዊ ሀገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ በመቀሌ ከተማ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ሲከፍቱ ነው።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት አንዣብቦ በታየው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የዜጎች መብቶች በአደባባይ ሲጣሱ የታየበት ፣ ህዝቦች በነፃነት ተንቀሳቅሰው መስራት የማይችሉበት፣ ሃብት ለማፍራት የተቸገሩበት ፣ ለጥቃት የተጋለጡበትና የህግ የበላይነት አደጋ ላይ የወደቀበት መሆኑንም ተናግረዋል።
“ይህ አስከፊና አደገኛ ሁኔታ ለዜጎች ህይወት መጥፋት ፣ ጉስቁልናና የወደፊት ተስፋ መታጣት ምክንያት ሆኗል” ያሉት ዶክተር ደብረፅዮን በዚህ ከቀጠለ በአገሪቱ አንድነትና ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ላይ የከፋ አደጋ እንዳይከሰት ስጋት መፍጠሩንም አስረድተዋል።
“እየታየ ያለውን ከፍተኛ ስጋትም ሁላችንም ተባብረን በመታገል ህዝቦቻችን የሚፈልጉትን ሰላም ፣ ልማትና ዴሞክራሲ ለማስፈን ችግር የሚፈጥሩ አካላትን በብቃት መመከት አለብን” ብለዋል።
“አሁን በአገሪቱ በስፋት እየተከሰቱ ያሉትን ቸግሮች ህገ-መንግስቱን ካለማክበርና የህግ የበላይነትን ካለማረጋገጥ የሚመነጩ ናቸው” ብለዋል።
https://telegra.ph/ETH-08-26-2

የኢፌዴሪ ቆንስላ ፅ/ቤት!
"የዘንድሮውን የሀጅ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርአት ለመፈፀም ከአገራችን የመጡ ታዋቂ እንግዶችን ለማስተዋወቅ እና ለማመስገን በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ለመታደም የተገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ነሀሴ 12 ቀን 2011 በመካ ከተማ ከለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማ በፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው..." ታውቋል። ደብዳቤው የተፃፈው ጅዳ በሚገኘው የቆንፅላ ፅ/ቤት ነው።
Via Elias Mesert

የሱዳን ህዝብና መንግስት ያጋጠማቸው ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ሚና መጫወቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመንግስት ምስረታው የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ድል ነው ብሏል። የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ኃይሉ በኢትዮጵያ አደራዳሪነት ከቀናት በፊት የሽግግር መንግስት ለመመስረት መስማማታቸው ይታወሳል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ ሦስተኛ ደረጃ መድኃኒት የተሻገረው ኤችአይቪ ኤድስ!
በዓለም ከሚገኙ ጥቂት ወግ አጥባቂ አገሮች ተርታ ኢትዮጵያ በግንባር ቀደምነት ትጠቀሳለች። የሕዝቦቿ ወግ አጥባቂነት አንዳንዴ ዘመናዊነትንየመጥላት፣ የመገዳደር ያህል የተጋነነ ሊመስል ሁሉ ይችላል፡፡
ብዙ አዳዲስ አስተሳሰቦችና ፈጠራዎች በአገሪቱ ተግባራዊ ከመደረጋቸውአስቀድሞ በባህልና ሃይማኖት መነጽር ማኅበረሰቡ እንዴት ሊመለከተውእንደሚችል በቅድሚያ በጥልቀት ይጤናል፡፡
ቁሳዊና ትውፊታዊ ባህሎቿ፣ ወጓ ሃይማኖታዊ መሠረት ያላቸው፣በትውልድ ቅብብሎሽ ዘመናትን የተሻገሩና በጊዜ መተካካት የበሰሉናቸው፡፡ ሐሳቡን በቀላሉ ለማስረዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ምዕራፍ፣ የቅዱስቁርዓን ሱራ ማጣቀስ የሚቀናው ሕዝቧ፣ አገሪቱ የጠኔ ምድር ብቻ ሳትሆንለፈጣሪ የተገዙ ፃድቃን መኖሪያም ሆና በዓለም ትታወቅ ዘን ረድቷታል፡፡
በሃይማኖት ላይ የፀናው የኢትዮጵያ የኋላ ታሪክ፣ የአሁን ህልውና ቅድስትአገር የሚል ቅጽል ታገኝ ዘንድም ምክንያት ሆኗል፡፡
በቀሪው ዓለም ብዙ ባህልና ልማድ ከጊዜው ጋር እንዲሄድ ተደርጎእየታደሰ፣ እየተከለሰና እየተቀነሰ የዘመናዊነት ቁንጮ የሆኑ አሁናዊባህሎች ተቀርዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-26-3

#update የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ከሃይማኖት መሪዎች ጋር በሀገር ደረጃ በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አልማዝ መኮንን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና ብጹአን ሊቃነጳጳሳት ተሳትፈዋል፡፡ አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በእምነት ተቋማት ላይ እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ተዋያይተዋል፡፡
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ኢ/ር ታከለ ኡማ ከትራንስፖርት ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ጋር በመሆን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንዚት አገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶስተኛው ዙር የከተሞች መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አሀድ የመጀመረያው ዓመት አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ተጀምሯል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ይገመገማሉ። መድረኩን በንግግር የከፈቱት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ታዜር ገ/እግዚያብሄር ሲሆኑ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹና በቂ የመሰረተ ልማት የተሟሉላቸው እንዲሆኑ ከተፈለገ የበላይ አመራሮችና የህብረተሰቡ የተቀናጀ ርብርብ ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀጣይ ተግባራዊ የሚደረገው የከተሞች የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም ከዚህ በፊት ከነበሩት በተጨማሪ አዳዲስ 73 ከተሞችን በመጨመር 117 ከተሞችን አካቷል። 6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።ለዚህም ከዓለም ባንክና ከፈረንሳይ የልማት ድርጅት 611 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ከክልሎችና ከተሞች 248 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በድምሩ 859 ሚሊዮን ነጥብ9 ሚሊዮን ዶላር የመቀናጆ በጀት ፀድቆለታል።
ይህ ፕሮግራም ከጊዜ ወደ ጊዜ አፈፃፀሙን በማሳደግ ላይ ሲሆን የፌዴራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርም በክልሎች የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከዚህ ፕሮግራም ጋር በማቀናጀት በከተማ ፕላን ዝግጅት፣ በመሬትና ቤቶች አቅርቦት፣ በከተሞች ገቢ አሰባሰብና በከተሞች የማስፈፀም አቅም እንዲሁም ከኮንስትራክሽንና መሰል ዘርፎች ጋር በማቀናጀት እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ይበልጥ የሚያሳድገው መሆኑም ዛሬ በተከፈተው የሶስተኛው ዙር የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ ላይ ተመልክቷል። በዚሁ መድረክም የከተሞች አፈፃፀም በዝርዝር ቀርቧል።
Via Negede

#ኢመደኤ
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) ወደ ሀገር ዉስጥ በሚገቡ እና ከሀገር በሚወጡ የቴክኖሎጂ እቃዎች ላይ ከአጋር አካላት ጋር የተቀናጀ የደህንነት ቁጥጥር በማድረግ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ ሥራ መስራቱን ገለጸ፡፡ የኢመደኤ የሴኪዩሪቲ ክሊራንስ ማዕከል ሃላፊ አቶ መስፍን ሙሉነህ እንደገለጹት ኤጀንሲዉ በ2011 በጀት አመት የተለያዩ በገንዘብ የማይተመን ጥቃት ሊያደርሱ የሚችሉ መሳሪያዎች ወደ ሃገር ዉስጥ እንዳይገቡ ቅድመ ቁጥጥር በማድረግ በቴክኖሎጂዎቹ አማካኝነት የሚከሰቱ የተጋላጭነት ስጋት እና ጥቃት በመግታት ብሔራዊ ሠላምን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ ስራ መሰራት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
Via #AMN
@tsegabwoldw @tikvahethiopia

#update የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአይቢኤ ኢትዮጲያና ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ አህጉራዊ የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ንቅናቄ ‹‹አፍሪካ ኢኖቬሽን ሳምንት›› በሚል ርዕስ ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22/2012 ድረስ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#G7
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለሥልጣን በቡድን 7 ሃገራት ስብሰባ ላይ ድንገት በመገኘት ብዙዎችን አጀብ አሰኝተዋል።
ሞሐመድ ያቫድ ዛሪፍ ፈረንሳይ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድን 7 ውይይት ላይ ድንገት መገኘታቸውን የሚያሳብቅ አንድ ፎቶ ማሕበራዊ ድር አምባ ላይ ለቀዋል።
የሰባቱ ሃገራት መሪዎች ከሚያከናውነት ስብሰባ ጎን ለጎን የሚከናወኑ አነስተኛ ውይይቶች ላይ የተሳተፉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብዙዎችን ማስደነቃቸውን ምንጮች ዘግበዋል። በተለይ የአሜሪካ ልዑካን በከፍተኛ ባለሥልጣኑ 'ድንኳን ሰበራ' እጅግ መደነቃቸውን ከፈረንሳይ የሚወጡ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
ሚኒስትር ዛሪፍ በትዊተር ገፃቸው ላይ 'ከፈረንሳይ ፕሬዝደንት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ገንቢ የሆነ ውይይት አካሂደናል' ሲሉ ፅፈዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የቡድን 7 ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት ከኢማኑዔል ማኽሮን ጋር መምከራቸው አይዘነጋም።
አሜሪካ እና ኢራን አሁን ላይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኙ መሆኑ የሰውየውን ድንገተኛ ጉብኝት 'ነገሩ ወዴት እና እንዴት ነው?' አድርጎታል።
ፈረንሳይ፤ ኢራን ከአሜሪካ እና ሌሎች አውሮጳ ሃገራት ጋር ያላትን የሻከረ ግንኙት ለማለሳለስ ብትታርም ኢራን 'የበላችበትን ሳህን ሰባሪ' እየሆነች አስቸግራለች። በተለይ በቅርቡ ከነዳጅ ተሸካሚ መርከቦች ጋር በተያያዘ የተፈጠረው ክስተት ኢራንን 'ነገር ተንኳሽ' አስብሏታል።
የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ሚኒስትር ዛሪፍ ከአሜሪካ ጋር ተስማምተን ነው እንዲጎበኙን ያደረግነው ቢሉም የዩናይትድ ስቴትስ ሰዎች ግን በጉብኝቱ እጅግ መደነቃቸውን አልደበቁም። የቡድን 7 ሃገራት - ብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጃፓን እና ዩናይትድ ስቴትስ፤ ቅዳሜ እና አሁድ 45ኛ ስብሰባቸውን አከናውነዋል።
Via #BBC

#update በሐዋሳ ከተማ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሞተር ቢስክሌቶች ከዛሬ ጀምሮ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ተፈቅዷ፡፡ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና የከተማዋ ፖሊስ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ኮማንደር ታደለ ዋሪዮ እንደገለጹት በከተማዋ ከአንድ ወር በፊት በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ላይ የታገደው እንቅስቃሴ ሕጋዊ ለሆኑት ተነስቷል። እንደ ኮማንደር ታደለ ገለፃ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የከተማዋ ፀጥታ እየተሻሻለ በመምጣቱና አንፃራዊ ሰላም በመስፈኑ ኮማንድ ፖስቱ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ሞተር ቢስክሌቶች ብቻ በከተማዋ እንዲንቀሳቀሱ ወስኗል፡፡
የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መስፍን ዴቢሶ በበኩላቸው በከተማዋ መንቀሳቀስ የሚችሉት ሞተር ቢስክሌቶች የሰሌዳ ቁጥርና የሶስተኛ ወገን ያላቸው፣ ቦሎ የለጠፉ እንዲሁም አሽከርካሪዎቹ መንጃ ፈቃድ ያላቸው ብቻ ይሆናሉ ብለዋል፡፡ ለፀጥታ ሥራ ልዩ ፈቃድ ከተሰጣቸው ሞተር ቢስክሌቶች ውጭ ሌሎች ሞተር ቢስክሌቶች ከንጋቱ 12፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉም አስታውቀዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-26-4

#update የቤኒሻንጉልና አማራ ክልል የጋራ ኮማድ ፖስት ባለፈው ሚያዚያ ከመተከል ዞን ተነስቶ ወደ አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተዛመተው ግጭት የተጠረጠሩ 169 ሰዎችንና ከ870 በላይ ቀስቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ የኮምንድ ፖስቱ ሰብሳቢ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የወረዳ አመራሮች እና የፀጥታ ኃይሎች ይገኙበታል።ኮማንድ ፖስቱ ፣በሁለቱ ክልሎች የጋራ ወሰኖች ላይ ባለፈው ሐምሌ ሥስት፣ የተከሰተውን ግጭት ለማብረድ፣የማረጋጋት ሥራ ከጀመረ ወዲህ 3ሺ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀዬአቸው ከመመለስ አንስቶ በርካታ የተዘረፉ ንብረቶችንም ማስመለሱን ገልጿል፡፡
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ሙገሳን እያገኙ ነዉ!
ካፍ በሚያዘጋጀው የዉስጥ ዉድድሮች አብዛኞቹ ጨዋታዎች የተመልካች ድርቅ እየመታቸዉ በዝግ በሚመስል መልኩ መካሄዳቸውን ቀጥሏል።
እንደሚታወቀው በክረምቱ በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ጥቂት ከሚባሉ ጨዋታዎች በስተቀር አብዛኞቹ በባዶ መካሄዳቸው ይታወቃል ይህም የካፍ አመራሮች ላይ ጥያቄ አስነስቶ ነበር።
ይህ ጉዳይ እየቀጠለ በመሄድ ክለቦች ላይ የራሱን የሆነ ተፅዕኖ አሳድሯል። በሳምንቱ መጨረሻ በተካሄዱ የሻምፒዮንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን የማጣሪያ ጨዋታዎች ይህ ነገር ተስተዉሏል።
አፍሪካን ሶከር በድህረ ገፁ እንደዘገበው የኢትዮጵያን ክለቦች መቐለ 70 እንደርታ እና ፋሲል ከነማ በተጫወቱበት ጨዋታዎች ላይ የኢትዮጵያን እግርኳስ ደጋፊዎች አርአያ መሆን እንደሚችሉ አስፍሯል።
የካኖ ስፖርት አሰልጣኝ በበኩላቸው ክለቡ በእንዲህ አይነት የድጋፍ ድባብ እና ብዙ ቁጥር ባለው ተመልካች ዉስጥ ሲጫወቱ የመጀመሪያቸው መሆኑን ገልፀዋል።
አፍሪካን ሶከር በድህረ ገፁ ብዙ የእግርኳስ አፍቃሪያን በስታዲየም በመገኘት የተመለከቱትን ጨዋታዎች ሲጠቅስ የኢትዮጵያን ክለቦች ግምባር ቀደም ቦታዉን ሲይዙ ታሪካዊዉን የጋና ክለብ አሻንቲ ኮቶኮን ደጋፊዎችንም አካቷል።
Via African Soccer
ስፖርታዊ ጉዳዮችን ይከታተሉ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
@tikvahethsport