TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ🔝

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ በተጭበረበረ ቼክ 14 ሚሊየን 724 ሺህ ብር #ሊያወጣ ሲል ተያዘ። ተጠርጣሪው አቶ #ገመቹ_ጫላ በሚል ስም በባንኩ ቅርንጫፍ ባለፈው አርብ የባንክ ሂሳብ የከፈተ ነው።

ዛሬም ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በማምራት #በተጭበረበረ የአምበሳ አውቶብስ #ቼክ 14 ሚሊየን ብር 724 ሺህ በማውጣት አርብ እለት ወደ ከፈተው የባንክ ሂሳብ ለማዛወር ሲል ነው በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ተደርጎበት መያዙ ታውቋል ተጠርጣሪው በሰዓቱ ለባንኩ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊ 1 ሚሊየን ብር ጉርሻ በማቅረብ እንዲፈፀምለት ለማግባባት ሞክሮም እንደነበር ታውቋል።

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮ
ፎቶ፦ A (TIKVAH-ETH)
@tsgabwolde @tikahethiopia
#Update ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ በተጭበረበረ ቼክ 15 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ሊያወጡ ሲሉ የተያዙት ግለሰቦች ትላንት ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ አቶ #ገመቹ_ጫላ#መስፍን_ደረጀ እና #ኧሰቦ_ኦጆሞ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ነው የቀረቡት።

ሰኞ እለት አቶ ገመቹ ጫላ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻላ ቅርንጫፍ 14 ሚሊየን 724 ሺህ ብር በተጭበረበረ ቼክ ሊያወጡ ሲል በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

አቶ ገመቹ በሶስት ድርጅቶች እና አንድ ግለሰብ አካውንት ላይ ስማቸውን በመቀያየር ከንግድ ባንክ የተለያዩ ቅርንጫፎች 22 ሚሊየን 450 ሺህ ብር ያወጡ ሲሆን፥ ሰኞ ዕለት ደግሞ 14 ሚሊየን 724 ሺህ ብር ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ግለሰቡ በራሴ ጠበቃ ለማቆም በቂ ገቢ የለኝም መንግስት ጠበቃ ያቁምልኝ በማለት ጠይቀዋል፤ ፖሊስ በበኩሉ በተለያየ ጊዜ አጭበርብረው ያወጡትን ገንዘብ ከእነሰነድ ማስረጃው ለችሎቱ አቅርቧል።

ግለሰቡ ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በማምራት በተጭበረበረ የአምበሳ አውቶብስ ቼክ 14 ሚሊየን ብር 724 ሺህ በማውጣት አርብ እለት ወደ ከፈቱት የባንክ ሂሳብ ለማዛወር ሲሞክሩ፥ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ክትትል ተደርጎባቸው መያዛቸውም ይታወሳል።

ተጠርጣሪው በሰዓቱ ለባንኩ ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሀላፊ 1 ሚሊየን ብር ጉርሻ በማቅረብ እንዲፈፀምላቸው ለማግባባት ሞክረው እንደነበርም ተመልክቷል።

ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበው ሰነድ በችሎት ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ እና በቂ ሀብትና ገቢ እንዳላቸው ባለመረጋገጡ 1ኛ እና 3ኛ ተጠርጣሪዎች የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ እንዲቆምላቸው እንዲሁም 2ኛ ተጠርጣሪ በግል ጠበቃው አቆማለሁ በማታለታቸው ጉዳዩን ለማየት ለአርብ ህዳር 14 ቀን 2011 ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia