TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.36K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በአማራ ክልል በቁጥጥር ሥር የዋሉ ታራሚዎች "ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት" እንደሚፈጸምባቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። ይኸ የተገለጸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሉ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የእንባ ጠባቂ ተቋም ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ካደረገው ጉብኝት በኋላ ነው። ቋሚ ኮሚቴው "ታራሚዎች ያለበቂ ምክንያት ከአንድ ማረሚያ ቤት ወደ ሌላ #ከማዘዋወር ባለፈ አሁንም በክልሉ አንዳንድ ማረሚያ ቤቶች ዘንድ በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመ እንደሆነ" ማረጋገጫ ማግኘቱን ምክር ቤቱ ባሰራጨው መረጃ አስታውቋል። በታራሚዎች ላይ የሰብዓዊ መብት #ጥሰት ይፈፀምባቸዋል የተባሉ ማረሚያ ቤቶች ግን አልተገለጹም።

Via የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia