#ሐምሌ19
የፀጥታ ኃይሎች ዝግጅት ምን ይመስላል ?
(ሀዋሳ - ቅዱስ ገብርኤል)
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ እና ፖሊስ መምሪያ ከነገ በስቲያ ሐምሌ 19 የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓልን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የበዓሉን ታዳሚዎች ደህንነት ለማረጋገጥ አስተማማኝ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።
የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በሠላም፣ በፍቅርና በመተሳሰብ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ እንዲከበር የህብረተሰቡ ሚና ወሳኝ መሆኑ ገልጿል።
በተለይም በከተማዋ በሚገኙ ሆቴሎች እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥብቅ ፍተሻ በማድረግ ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተጠቁሟል።
ሀዋሳ ከነገ በስቲያ በሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ንግስ በዓል እጅግ በጣም ከፍተኛ የሰው ቁጥር ታስተናግዳላቸው ተብሎ ይጠበቃል።
@tikvahethiopia

(ቁልቢ ገብርኤል)
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ ፤ በዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ላይ የሚታደሙ ምዕመናንን እና እንግዶችን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አስተማማኝ ዝግጅት መደረጉን አሳውቋል።
ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ የምስራቅ እና የምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፣ የሐረሪ ክልል ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ተቀናጅተው በቂ ዝግጅት አድርገዋል።
የንግስ በዓሉ ታዳሚዎች መጨናነቅ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ በተለይ የደብሩ መግቢያና መውጫ በሮች አካባቢ የኪስ ቦርሳቸውን ፣ ሞባይላቸውን እና ሌሎች ንብረቶቻቸውን በጥንቃቄ እንዲይዙ ፖሊስ አሳስቧል።
አሽከርካሪዎች ወደ ንግስ በዓሉ ሲመጡ #ከኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_መለያ ወይንም ከህጋዊው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በስተቀር ሌላ ለፖለቲካ ማራመጃ የሚሆን ዓርማና ምልክት ይዞ መገኘት እንደማይቻል አሳስቧል።
በንግስ በዓል ላይ ሶስት ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ እና የወንጀል ድርጊት ተጠርጣሪዎች ሲያዙ ውሳኔ ለመስጠት ዐቃቤ ህግና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት ተቋቁሟል።
የበዓሉ ታዳሚዎች አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥማቸው በስልክ ቁጥር 0256665056 መጠቆም እንደሚችሉ ፖሊስ ገልጿል።
የአካባቢው የመሬቱ አቀማመጥ ዳገታማ፣ ቁልቁለታማና ጠመዝማዛ በመሆኑ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግና ደንብ አክብረው በማሽከርከር ከአደጋ እንዲጠበቁ ተብሏል።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከጨለንቆ ከተማ እስከ ቀርሳ ከተማ ባለው ዋናው የተሸከርካሪ መንገድ ላይ ከባድ መኪና ማለፍ የተከለከለ መሆኑን ፖሊስ አሳስቧል።
#ENA

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሐምሌ19
በየዓመቱ ሐምሌ19 የሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግሥ በአል በደመቀና በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የምስራቅ ሐረረርጌ ዞን ፖሊስ ገልጿል።
በበዓለ ንግሱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ከአገር ውስጥና ከወጭ የመጡ ምዕመናን እና ሌሎች አንግዶች ታድመው ነበር።
በዘንድሮ ንግስ በዓል የስርቆት ወንጀል በፈፀመ ተጠርጣሪ ላይ በስፍራው የተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የሁለት አመት እስራት መወሰኑን ፖሊስ ገልጿል።
ዘንድሮ የተፈፀመው ስርቆት ወንጀል ከባለፉት ዓመታት ከተፈፀሙ የወንጀል ድርጊት እጅግ ማነሱን የፖሊስ ሪፖርት አመልክቷል።
በመንገድ ትራፊክ በኩልም ምንም ዓይነት የትራፊክ አደጋ አልደረሰም።
በሌላ በኩል ፤ በሀዋሳ ሐምሌ19 የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል።
በዓሉ ከወትሮው በተለየ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተገኘበት ነው።
በበዓሉ በርካታ ቁጥር ያላቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮች እንዲሁም ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር የመጡ ጎብኚዎች፣ ታላላቅ የሀይማኖት አባቶች እና የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ የክልልና የሐዋሳ ከተማ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው የተከበረው።
እንደ ፖሊስ ሪፖርት በዓሉ ያለአንዳች የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሯል።
ከወንጀል ጋር በተያያዘ አንዲት የበዓሉ ታዳሚ ላይ የሞባይል ስርቆት የፈጸመ ተጠርጣሪ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ በጊዜያዊነት በተቋቋመው ችሎት ማስረጃ ቀርቦበት የ2 ዓመት እስራት ቅጣት ተላልፎበታል። የተሰረቀውን ሞባይል ለግለሰቧ ማስመለስ መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።
Photo Credit : የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ENA